HULUM MEREJA


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Криптовалюты


Welcome to Hulum Mereja – your trusted source for the latest in Cryptocurrency, Blockchain, Technology, and Global News updates.
Stay informed

Buy ads: https://telega.io/c/Hulumereja123

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Криптовалюты
Статистика
Фильтр публикаций


ቡና‼️
ቡና የተፈጥሮ እርጅናን እንደሚከላከል ጥናት አመላከተ‼️
የጥዋት ቡናዎ ከእንቅልፍ የመቀስቀሻ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ የሚወስዱት የእርጅና መከላከያ ሊሆን እንደሚችል አዲስ ጥናት አመልክቷል።

ከለንደን የንግስት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ እና ከፍራንሲስ ክሪክ ኢንስቲትዩት የተገኙ አዳዲስ የምርምር ውጤቶች እንዳመለከቱት ካፌይን (Caffeine) ኤኤምፒኬ (AMPK) የተባለ ኃይለኛ ሴሉላር መንገድን እንደሚያነቃቃ አረጋግጠዋል። ኤኤምፒኬ ሴሎች እራሳቸውን እንዲጠግኑ፣ እንዲያድጉ እና ጭንቀትን እንዲቋቋሙ የሚያግዝ ባዮሎጂያዊ የነዳጅ መለኪያ ዓይነት ነው ተብሎለታል።

በእርሾ ሴሎች ላይ ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ካፌይን የኤኤምፒኬን መቀየሪያ እንደሚያበራ ነው። ይህ ደግሞ ከእርጅና ጋር የተገናኘ ሌላ ተቆጣጣሪ የሆነውን ቶር (TOR) የተባለውን ንጥረ ነገር በቀጥታ ይቆጣጠራል ተብሏል። ይኸው የኤኤምፒኬ-ቶር መንገድ በሰው ልጆች ላይም የሚገኝ ሲሆን፣ እንደ ሜትፎርሚን (metformin) ያሉ የእድሜ ማራዘሚያ መድኃኒቶችም ይህንኑ መንገድ ዒላማ ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡

ምንም እንኳን ይህ ገና በቅድመ-ደረጃ ላይ ያለ ሳይንስ ቢሆንም፣ ግኝቶቹ ካፌይን ለወደፊት አዳዲስ የእርጅና መከላከያ ሕክምናዎችን ለማነሳሳት እንደሚችል ይጠቁማሉ። እስከዚያው ድረስ፣ ቡና የመጠጣት ልምድዎ ለሴሎችዎ ትንሽ የእርጅና መከላከያ ጥቅም እየሰጠ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ አመላክቷል።


ቤተሰብ binance በድጋሚ የjuly ወር red pocket giveawy አዘጋጅቷል

ይሄም giveawy እንደ ባለፈው ነው
እድላቹን ሞክሩ

LINK👇👇👇



https://app.binance.com/uni-qr/Q23kDLdf?utm_medium=web_share_copy


"አሌክሳንደር ግራሃም ቤል"

"ሄሎ" ማለት ምን ማለት ነው?
እዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት ግርሃም ቤል እና ማርጋሬት ሄሎ ናቸው ግርሃም ቤል ስልክን የፈጠረ የሳይንስ ሊቅ ነው:: የመጀመርያውን የስልክ ጥሪ ሙከራ ሲያደርግ በስልኩ የሌላኛው ጫፍ ሚስቱ ማርጋሬት ሄሎ ነበረች ስልኩን ስታነሳው የመጀመርያው ቃል "ሄሎ" ብሎ ስሟን መጥራት ነበር:: ከዚህ ወዲያ ነበር የስልክ ጥሪ መጀመርያው "ሄሎ" ሆኖ የቀረው አለም ቀኑን ሙሉ በቢሊዮን ጊዜ ስሟን ሲያነሳ ይውላል - ስም ካስጠሩ አልቀር እንዲህ ነው እንጂ🤷🏾

Respect


Good MORNING


ኤለን መስክ 54ተኛ ዓመቱን ይዟል !
Happy birth day bro


አውሮፕላኑ ምን ገጠመው❓❗👇
በሙምባይ የአስቸኳይ ጊዜ ማረፊያ ያደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን 7 ተሳፋሪዎች ታመዋል ተባለ‼️
ከዓለም ዓቀፍ መረጃዎች እንደተዘገበው ከሆነ ከዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም (June 28, 2025) ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 አውሮፕላን ወደ ሙምባይ ሲበር በካቢን ውስጥ የነበረው ግፊት በመቀነሱ ምክንያት ድንገተኛ አደጋ አጋጥሞታል ተብሏል።

በዚህም ምክንያት ሰባት ተሳፋሪዎች መታመማቸው ተገልጿል።

አውሮፕላኑ በአየር ላይ እያለ የውስጥ ግፊቱ በመቀነሱ፣ ድንገተኛ ማረፊያ ለማድረግ ተገዷል ነው የተባለው።

በደረሰው የአየር ግፊት መቀነስ ሳቢያ የታመሙት ሰባት ተሳፋሪዎች ወደ ሙምባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

ከመካከላቸውም አንዱ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እንደተደረገለት መረጃዎች ያመለክታሉ።

የአደጋው መንስኤ በምርመራ ላይ ሲሆን፣ የአየር መንገዱ ባለስልጣናት እስካሁን ዝርዝር መረጃዎችን አልሰጡም ተብሏል።

ይህ ክስተት ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሌሎች አየር መንገዶች ላይ ከተከሰቱ ተመሳሳይ የአየር ግፊት መቀነስ ችግሮች ጋር የሚመሳሰል መሆኑ ተጠቁሟል።

መናኸሪያ ሬዲዮ


የአለም ሶስተኛው ሀብታም ሰው የአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ከነገ ጀምሮ ለሶስት ቀን በሚቆይ ድግስ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያገባ ነው፡፡በጣልያኗ ቬኒስ ከተማ በሚደረገው ድግስ ላይ የአለም ዝነኞች የተጠሩ ሲሆን ከነዚህም መሀከል ኢቫንካ ትራምፕ ፥ ካርዳሺያንስ ፥ ኦፕራ ዊንፍሬ እና ሌሎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡እንግዶቹም ዛሬ በግል ጀቶች እና በቅንጡ ጀልባዎች ወደ ቬኒስ ሲገቡ ውለዋል፡፡ቤዞስ ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር ከ25 አመት ትዳር በኋላ ሲፋቱ 35 ቢሊየን ዶላር ድርሻዋን ወስዳ ራሷን የቻለች ትልቅ ቢሊየነር ሆናለች፡፡ሰውየው አሁን ላይ 220 ቢሊየን ዶላር ሀብት አለው፡፡


💚💛❤️ መልካም ቀን 💚💛❤️

በጥዋት ተነስተህ አትበሳጭ፣ ባለፈው ነገር አትማረር፣ አትናደድ ይልቁም ዛሬ ለተሰጠህ ህይወት ፈጣሪህን አመስግን።
በህይወት መኖርህ በራሱ ትልቅ ተስፋ ነው። አንተ ጥረትህን ቀጥል ፈጣሪ ሁሉን በጊዜው ያደርጋል።

#እንዳትረሳ ፦ ስለሌለክ ነገሮች እያሰብክ ፈጣሪን አታማር ይልቁንም ስላለክ ብዙ ነገሮች በማሰብ ደስ ይበልክ ፈጣሪንም አመስግን።

〰〰〰መልካም ቀን〰〰〰〰


😁😁


መስራት ባለብህ ሰአት ካልሰራክ 💪
መሳቅ ባለብህ ሰአት ታለቅሳለክ😭


የግዙፉ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለቤት ናይጀሪያዊው ቢሊየነር ሃጂ መሐመድ አሊ ዳንጎቴ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ላቆመው ገበሬ የሚሆን ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ በ3 ቢሊዮን ዶላር ሊገነቡ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰምተናል።

ይህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ፈቀቅ ከሚያደርጉት ፕሮጀክቶች አንዱና ብቸኛው ፋብሪካ ነው።
ፋብሪካው ቁጥር 2 ህዳሴ የሚል ስም ሲጠራ በ3 አመት ውስጥ ተገንብቶ የሚያልቅ ነው።


Репост из: BRICS News
BREAKING: 🇮🇱🇮🇷 Israel and Iran agree to a full ceasefire starting in 6 hours.

@BRICSNews


JUST IN: 🇺🇸🇮🇷 Bitcoin reclaims $104,000 as President Trump calls for peace with Iran.


ፕሬዚደንት ትራምፕ “እንኳን ደስ ያለሽ አለም ፣ ጊዜው የሰላም ነው ።" ብሏል


ትራምፕ ለኢራን ጥቃት ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላቸውም።(CNN)


ኢራን በሶሪያ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር በሞርታር ደበደበች
*

የኢ
ራን መንግሥት በኳታር በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ካደረሰ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማምሻውን በሶሪያ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈርም በሞርታር ደብድቧል።

በሶሪያ ምዕራብ ሀሳካ ግዛት በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በአካባቢው ጥብቅ የፀጥታ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን የኢራኑ መህር ዜና አገልግሎት ዘግቧል።


አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል

አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይል በከፊል የተቋረጠው ከዋናው ግሪድ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው፡፡

አሁን ላይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

ለተፈጠረው ችግር ደንበኞችን ይቅርታ የጠየቀው አገልግሎቱ÷ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል


🎙ሳዲዮ ማኔ ሳውዲ አረቢያ ሄዶ ለመጫወት በአለም ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎቸ የሚወዱት የእግር ኳስ ችሎታው እያለ አውሮፓን የለቀቀው ለምን እንደሆነ ሲጠየቅ እንዲህ ሲል መለሰ።

ሳዲዮ ማኔ:🗣 "በመጀመሪያ የአውሮፓ እግር ኳስን እወዳለሁ, እና እኔ ዛሬ ባለኝ ተጫዋች እንድሆን ስላደረገኝ ሁልጊዜ አመስጋኝ እሆናለሁ ነኝም. እንደ እውነቱ አውሮፓን መልቀቅ የመጀመሪያ እቅዴ አልነበረም እውነታው ግን, እዚያ ያገኘሁት የገንዘብ ድጋፍ ወደ ቤት እና ወደ ሃገሬ ለመመለስ የምፈልገውን አይነት ተፅእኖ ለመፍጠር በቂ አልነበረም.

በሳውዲ አረቢያ የመጫወት እድል ሲመጣ በማገኘው ሂሳብ ለህዝቤ የበለጠ ለመስራት ጥሩ መንገድ አድርጌው አስቤ ነበር. አሁን የማገኘው ገቢ በሀገሬ የተቸገሩትን በእውነት እንድረዳ አስችሎኛል። ያለኝን ነገር ተጠቅሜ በሌሎች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት ለእኔ በጣም አስፈላጊው ነገር ይህ ነው።
🇸🇳 ልበ ቅኑ ማኔ💝

Football Era


200,000 ብር iPhone 17?! 😱📱

አዲስ የ iPhone ወሬ!

ይህ የወጣው ምስል የ iPhone 17 ነው እየተባለ ሲሆን፣

በኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት አካባቢ (በፈረንጆቹ September ወር) ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ አዲስ iPhone በአራት አይነት ዲዛይንና አይነት ይወጣል የተባለ ሲሆን፣

አስቀድሞም "ልዩ የሆኑ ነገሮች አሉበት
" እየተባለለት ነው።

በጣም የሚያስገርመው ግን ዋጋው ከ200 ሺህ ብር በላይ ሊሆን ይችላል መባሉ ነው! 🤯

እርስዎ የiPhone ስልክ ወዳጅና አድናቂ ኖት?

ይህን አዲስ ስልክ ለመግዛትስ አስበዋል?


3ኛው የአለም ጦርነት ቢነሳ ሁሉም የአውሮፓ አገራት በፍፁም የሩስያን የኑክሌር የጦር መሳሪያ መከላከል አይችሉም።

"የአውሮፓ አገራት እና አሜሪካን ያላቸውን የኑክሌር የጦር መሳሪያ አንድ ላይ ተደምሮ የሩስያ የኑክሌር የጦር መሳሪያ በብዛትም በአቅምም ይበልጣል።

ሩስያ ከእሜሪካ እና ከአውሮፓ የሚበልጥ ብዙ የኑክሌር መሳሪያ አላት።

ፈጣሪ የ3ኛው አለም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እና እንዳይጀመር እንዲያደርግ ፀሎት አደርጋለሁኝ ፤ነገር ግን አሜሪካና አውሮፓ በመካከለኛው ምስራቅ እያደረጉ ያሉትን ጦርነት ሩስያን እንዳይነካት መጠንቀቅ አለባቸው፣ ያለበለዚያ ሩስያ ወደ ጦርነቱ ትገባለች።

ሩስያ እና አሜሪካ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ቅደመ ማስጠንቀቅ ሲስተም አላቸው።ይህ ቅደመ ማስጠንቀቂያ ምልክት የኑክሌር የጦር መሳሪያ ፍንዳታ እንዳይጀምር ወይም እንዲቆም ልየታ ያደርጋል፤ ነገር ግን የአውሮፓ አገራት ይህ ሲስተም የላቸውም ።

የሩስያ የኑክሌር ሀይል አሜሪካ በሁለተኛው አለም ጦርነት ወቅት በጃፓን በሂሮሺማ እና በናጋሳኪ ከተሞች ከጣለችው የአቶሚክ ቦምቦች 10 እጥፍ ይበለጣል፤ ስለሆነም ሩስያ የኑክሌር ጦር መሳሪያን እንድትጠቀም ከተገደደች አንዳንድ አገሮች ከዚህ ምድር ላይ ድምጥማጣቸው ይጠፋል"

"ቭላድሚር ፑቲን"

Usefulexpression

@Hulumereja123

Показано 20 последних публикаций.