ስቃይ የሂደቱ አካል ነው
አንድ ሰው ጠንካራ አጥንትና ጡንቻ ለማዳበር በአካላዊ ህመም መሰቃየት እንዳለበት ሁሉ፣ ታላቅ ስሜታዊ እርጋታ፣ ጠንካራ ራስን የመሆን፣ ለሰው ያለውን ሀዘኔታ ለመጨመርና በአጠቃላይ ደስተኛ ሕይወት ለመገንባት በስሜታዊ ስቃይ ውስጥ ማለፍ አለበት፡፡
በጣም መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች በእይታችን ውስጥ የሚሆኑት በአብዛኛው በጣም በመጥፎ ጊዜያቶቻችን መጨረሻ ላይ ነው፡፡ እሴቶቻችንን ለመመልከትና ለምን እንድንወድቅ ያደረጉን እንደሚመስለን መጠየቅ የምንፈቅደው በጣም ከባድ ስቃይ ሲሰማን ብቻ ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ እንዴት ትርጉም እንደምናመጣ የመመልከት አላማ እንዲኖረን የሆነ አይነት ቀውስ እንፈልጋለን፡፡ ከዚያ ሁኔታውን ለመለወጥ እንሞክራለን፡፡
እና ምናልባት አንተም አሁን እንደዚያ አይነት ቦታ ላይ ትሆን ይሆናል፡፡
ምናልባት በሕይወትህ በጣም ከባድና አስቸጋሪ ነገር እየመጣና ከዚህ በፊት እውን፣ የተለመዱ እንዲሁም መልካም እንደሆኑ የምታስባቸው ነገሮች ሁሉ ተቃራኒውን እየሆኑብህ ይሆናል፡፡
ጥሩ ነው፡፡ ያ የመጀመሪያው ነው፡፡ በበቂ ሁኔታ ላለረጋግጥልህ አልችልም ግን ስቃይ የሂደቱ አንድ ክፍል ነው፡፡ እንዲሰማህ መሆኑ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን ህመም ለመሸፈን ሌላ ነገር የምታሳድድ ከሆነ፣ ራስህን ከፍ አድርገህ በማየትና በማይረባ አወንታዊ አስተሳሰብ ውስጥ መጥለቅህን ከቀጠልክ፣ በተለያዩ ሱሶች ወይም ድርጊቶች የበለጠ መያዝህን ከቀጠልክ፣ የእውነት ለመለወጥ የሚያስፈልግህን መነሳሳት በጭራሽ ማምጣት አትችልም፡፡
ብዙ ሰዎች የሆነ ህመም ወይም ንዴት ወይም ሀዘን ሲሰማቸው ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው በመተው የሚሰማቸውን ስሜት ማደንዘዝ ወይም መካድ ይጀምራሉ፡፡ ግባቸው በተቻለ ፍጥነት እንደገና ወደ “ጥሩ ስሜት መመለስ ነው፡፡ ያ ማለት እፅ መጠቀም ወይም ወደማይረቡ ጊዜ ማሳለፊያዎች መመለስ ቢሆንም ያንን ያደርጋሉ፡፡
የመረጥከውን ስቃይ መቋቋም ተማር፡፡ አዲስ እሴት ስትመርጥ ወደ ሕይወትህ አዲስ አይነት ስቃይ ለማስገባት እየመረጥክ ነው፡፡ ውደደው፡፡ አጣጥመው፡፡ እጆችህን ዘርግተህ ተቀበለው፡፡ ከዚያ ህመም እየተሰማህም ቢሆን ተራመድ፡፡
✍️ማርክ ማንሶን
የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence