ማን ይቀስቅሰን?...
---
ደምስ ሰይፉ
እንደ ማሕበረሰብ አንቀላፍተናል… ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን… ለሞት የቀረበ እንቅልፍ… ችግሩ ማንቀላፋታችንን አናውቅም… ማንቀላፋታችንን ስላላወቅን የተኛንበትንም አናውቅም… ማንቀላፋታችን ደግሞ በሌባ አስደፍሮናል… ችግሩ መሰረቃችንን አናውቅም… ወይም ግድ የለንም… የተዘረፍነው ግን አማናዊነት ነው… እውነተኛውን ማንነት!!… ስንነቃ እንደምን እንደነግጥ ይሆን?...
---
“Race is a lazy byproduct of not knowing your true self” ― Shaun S. Lott
___
የሰውን ልጅ እጅግ ከሚያሳንሱ ነገሮች ዋነኛው ምናልባትም ትልቁ ጎሰኝነት ይመስለኛል... ጎሰኝነት ከሁዳድ ጋርዮሽ የመዳፍ ቁርስራሽ የሚያስመርጥ እብደት ነው... የሰው ልጅ የሁዳድ ጋርዮሽ Space ሲሆን የመዳፍ ቁርስራሹ ደግሞ መንደርተኝነቱን የሚታቀፍበት ጎሳዊ ቅርጫት ነው... ስፔስ ላይ ቅርጫትን አኑሮ ማሰብ ጣና ሃይቅ ላይ አንዲት የጤፍ ፍሬ አስቀምጦ ከማሰብም በላይ ከባድ ነው...
___
ስለ [Multi verses] የሚያትተው የ Parallel universe ቲዎሪ እስከዛሬ ከምናውቀው በላይ ሌሎች ብዙ ቨርሶች ስፔስ ላይ እንዳሉ ሲያትት ሺህ ምንተሺህ ፕላኔቶች ሕዋውን እንደሞሉ እንረዳለን... ከዚህ አንፃር የኛይቱ ምድር ስላለንባት ግዙፍ ትምሰል እንጂ ከሌሎቹ እልፍ አዕላፍ ፕላኔቶች ጋር ስትተያይ እዚህ ግባ የሚባል መጠን ልኬት የላትም...
___
የሰው ልጅ ግን ከምድርም፣ ከቨርሶችም ከራሱ ከስፔስም ይልቃል፤ በፈራሽ በስባሽ ሥጋ የማይመተር፣ በጊዜና ቦታ የማይሰፈር ታላቅ ማንነት ባለቤት ነውና... ይህን ጽሩይ ማንነት ግን ሁሉ አይረዳውም ሁሉ አይገነዘበውም፤ አብዛኛው በጠፊ ጥላው ላይ ተመስጧልና...
___
“You are here to enable the divine purpose of the Universe to unfold. That is how important you are!” ~ Eckhart Tolle
___
እውነታው የስብዕናችን ግዝፈት ልክ አልባነቱን አመልካች ቢሆንም በመንደርተኝነት መጨፈናችን ልክና ገደብ ከሌለው ሕዋ አንፃር የድቃቂ አቧራን ያህል ዓይን የማትቆረቁረውን ምድርን ወደ ሌሎች ብናኞች የመከፋፈል ክፋት ውስጥ ዶሎናል... ችግሩ በዚህ ቢቆም መልካም ነበር፤ ቅንስናሹ ውስጥ 'ሌሎች' እንዲኖሩ የምንፈቅድበት መስፈሪያ ደግሞ አለን... የኔ ወገን፣ የኔ ዘር፣ የኔ ምንትስ... ወዘተ የሚያስብል ህመም...
___
እርግጥ የቋንቋ መኖር እውነት ነው... የጎሳ መኖር ግን ቅዠት ነው፤ በምንም አታረጋግጠውም... ታዲያ እንዴት ነው እኛና ሌሎች ለማለት የምንጠቀመው?... አማራ፣ ኦሮሞ ወይም ሲዳማነት በላብራቶሪ ውስጥ የሚረጋገጥ ነገር የለውም... ደምህ [A፣ B ፣ AB እና O] የሚል የወል ስም እንጂ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ትግሬ፣ አልያም ወላይታ የሚያሰኝ ንጥረ ነገር የለውም... 'እኔ ምንትስ ነኝ፣ እከሌ እንዲያ ነው' ስትል ቋንቋን፣ በአንድ አካባቢ መገኘትንና ትውስታን መሰረት ከማድረግህ ውጪ ምን ተጨባጭ ማስረጃ አለህ?...
___
የፍልስፍና ፕሮፌሰሩ David Livingstone Smith, “Less Than Human: Why We Demean, Enslave, and Exterminate Others” በተሰኘ ተሸላሚ መጽሐፉ ስለ ዘረኝነት ሲጽፍ “The folk notion of race is very much an artificial construction.” ብሏል…
---
እንግዲህ ቋንቋ እውቀት ነው - ማንም ይማረዋል... አንድ አካባቢ መገኘትም አጋጣሚ ነው - ማን አውቆ ይመርጠዋል?... የቆዳ ቀለም ለየአህጉሩ የተሰጠ የአየር ሁኔታ ግልባጭ ነው - በቆዳው ውስጥ ያለውን የ melanin መጠን ማን መወሰን ይችላል?... እስኪ ንገረኝ - ‘ነኝ’ የምትለውን ነገድ የሆንከው በምንህ ነው?... ራስህን ከኔ የነጠልከው ምን ይዘህ ነው?... ልዩ ልዩ ቋንቋና ይትባሃል ፈጥረን ውበት ከመጨመራችን ውጭ በሰውነታችን መሃል 'ልዩነትን' የሚያሳይ ምን ነገር አለን?... ነገዴ ግንባሬ ላይ ተጽፎ ይሆን እንዴ?...
___
ወዳጆቼ... ይህ የመንደርተኝነት ህመም በዚህ ከቀጠለ የእግር መቆሚያ ሁሉ ሊያሳጣን ይችላል... ለአማናዊ ማንነቱ ኢትዮጵያዊ ዜግነት የማይመጥነውን፣ አፍሪካዊነት የማይስተካከለውን፣ ምድር እንኳ የማትፎካከረውን ለብቻው ዩኒቨርስ የሆነን ሰው እንዴት 'መንደርህን ፈልግ' ትሉታላችሁ?... “You are here on earth to unearth who on earth you are.” ― Eric Micha'el Leventhal
___
@bridgethoughts
@Human_Intelligence