ልብና መስታወት
አንዳችም ሳይጨምር፣ አንዳችም ሳይቀንስ፣
በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፣
ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት ፤
መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት::
ልብ ግን አቃተው!
በመጣው ሲደሰት፣ በሄደው ሲከፋ፣
ውለታ ሲደምር፣ ቅያሜ ሲያጣፋ፣
ከሚስጥር ሆድ ዕቃው ነገር ሲያመሰኳ
ቀለም አልባ ሆነ ይቅርታችን መልኳ።
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!!
አንዳችም ሳይጨምር፣ አንዳችም ሳይቀንስ፣
በተሰጠው መጠን ለሁሉም ሲመልስ፣
ከትዝታ ገጹ ምንም ሳይጽፍበት ፤
መስታወት ብቻ ነው ኑሮን ያወቀበት::
ልብ ግን አቃተው!
በመጣው ሲደሰት፣ በሄደው ሲከፋ፣
ውለታ ሲደምር፣ ቅያሜ ሲያጣፋ፣
ከሚስጥር ሆድ ዕቃው ነገር ሲያመሰኳ
ቀለም አልባ ሆነ ይቅርታችን መልኳ።
ምንጭ -የመንፈስ ከፍታ
ደራሲ-ሩሚ
በረከት በላይነህ እንደተረጎመው!!