Репост из: ከሰለፎች ኮቴ
ሰላም ላንቺ እህቴ...
ቀኑን እየፆምሽ አድካሚ የሆነ ስራ ወይም ትምህርት ላይ የምትውይ፣
ተሯሩጠሽ ወደ ቤት ተመልሰሽ ደግሞ የማፍጠሪያ ምግቦችን የምትሰሪ፣
ማታ ደግሞ የመመገቢያ እቃዎችን አጥበሽ ቤት አስተካክለሽ ወደ ተራዊህ የምትሄጂ፣
ወገብሽ የመሸከም አቅሙን ቢያጣም ከተራዊህ መልስ የተወሰነ ቁርዐን ለመቅራት የምትጥሪ፣
ከሱሁር ሰዐት በፊትም ቀድመሽ ተነስተሽ አላህ ያገራልሽን አይነት ዒባዳ ፈፅመሽ ስትጨርሺ ማብሰል ያለብሽን አብስለሽ፤ የቀዘቀዙትንም ምግቦችን አሙቀሽ፣ የተኛውን ቀስቅሰሽ ልክ እንደ ኢፍጣር ሰዐቱ ለሱሁርም ቤተሰቦችሽን የምትኻድሚ፣
ከፈጅር ቡሀላ ደግሞ ቁርዐን ቀርተሽ ድጋሚ ወደ ስራ(ትምህርት) እስከምትሄጂ ባለው ሰዐት ሌሎች የቤት ስራዎችን የምትሰሪ፣
አንቺ ብርቱዋ እህቴ የአላህ ሰላም እና እዝነት ያካብሽ፣ ከሆንሽው በላይ ጠንካራ ያድርግሽ፣ ጀሊል ዱንያ አኺራሽን ያሳምረው፤ በእያንዳንዱ አድካሚ የዱንያ እንቅስቃሴሽ ሁሉ አላህን ለማውሳት ያልሰነፈ ምላስሽን አላህ ሸር ከመናገር ይጠብቅልሽ፣ የቤተሰቦችሽን ዱዐና ምርቃት አላህ ይቀበልልሽ
አንቺ መልካም ሴት ዱንያ እንዳንቺ አይነት ምግባሩም መልኩም ያማረ ነገርን አብዝታ አልያዘችም፣ አንቺ ልዩ ነሽ ፣ አላህ ለኸይር የመረጠሽ ጠንካራ ባሪያው ነሽ፥ በርቺልኝ የኔ ውዷ እህት You got this👑
moon
✨