✏️ #የነብዩን_ቃል_ፈፅሜ_እዛዉ_እሞታለሁ
✍አሚር ሰይድ
ለእምነቱ ጥልቅ ፍቅር የነበረው ጀግና ወህብ ቢን ከብሻህ (ረ.ዐ) የነብዩ ﷺ ክቡር ሱሀባ መቃብር የሚገኘው በቻይና ነው፡፡ ነብዩﷺ ወህብን ወደ ቻይና ሄዶ ኢስላምን እንዲሰብክ ታላቅ የሆነ ተልዕኮን አሸክመው ላኩት፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ ዘመን አንድ ሰው ከመዲና ተነስቶ ቻይና ለመድረስ አንድ ዓመት ያህል ይፈጅበት ነበር፡፡ ወህብ ኢብን ከብሻህ (ረ.ዐ) ቻይና ከደረሰ በኋላ ኢስላምን እያሥፋፋ ለረዥም ዘመን ቆይቶ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ናፍቆት በጣም ስለበረታበት ዓይናቸውን ለማየት ወደ መዲና ተመለሰ፡፡ አንድ ዓመት ከፈጀ የመከራ ጉዞ በኋላም መዲና ደረስ፡፡ ሆኖም ግን ምን ያደርጋል! ናፍቆት እንዳንገበገበውና ዓይናቸውን ለማየት እንደጓጓ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሳያያቸው ቀረ። ሞተው ነበር የደረሰው😔
አለቀሰ አዘነ ተከዘ ከዱንያ ያጣዉ ነገር ትልቅ ሆኖ ተሰማዉ....ምንም እንኳ ናፍቆቱና ሰቀቀኑ ቢበረታበትም እንደገና ወደ ቻይና መመለስ ነበረበትና ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ምክንያቱም ይህንን የተቀደሰ ዓላማ እንዲያራምድ ኃላፊነት የሰጡት የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንደመሆናቸው ትዕዛዛቸው መከበር ነበረበት፡፡ ወሀብ ኢብን ከብሻህ(ረ.ዐ) ቻይና ደርሶ እምነቱን እያስፋፋ እያለ እዚያው አረፈ፡፡ በዚህም ተግባሩ በቻይና የመጀመሪያው የአላህ
መልዕክተኛ ﷺ አምባሳደር የመሆንን ደረጃ ተጎናፀፈ።
ፈራሽ የሆነው አካሉ በቻይና ቢቀበርም የማትሞተው ነፍሱ ግን ከአላህ መልዕክተኛ ትዕዛዝ ስር ነበር...ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ቢሞቱም ግን ፍቅራቸዉን ሁባቸውን ይገለፀዉ ከአላህ የመጣዉን ኢስላምን ሀይማኖት ነብዩ ﷺ ባዘዙት መሰረት ኢስላምን እያስፋፋ እዛዉ ቻይና ተቀበረ
ፍቅር ማለት ይህ ነዉ ....የወጣት ነሺዳ የሴት ማጥመጃ ነሺዳ እያዳመጡ ነቢይን እወዳለሁ ማለት እራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ ሱሀቦቹ ሀቢቡና ሙሀመድን ከራሳቸዉ በላይ አስበልጠዉ ይወዱ ነበር ﷺ💚💛❤️
እኛም እንደሱሀቦቹ ያለ ወኔ ልብ ባይኖረንም በምንችለዉ ዉዴታችንን እንግለፅ በተመቸን አጋጣሚ ሶሉ አለነቢይ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚💛❤️💞💞💚💛❤️
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group