"ሙስና ፍትሃዊ የታክስ እና ቀረጥ ሥርዓትን ስለሚያዛባ በጋራ እንታገለዋለን" - የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ
ታህሳስ 8/ 2017 ( ገቢዎች ሚንስቴር )
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን 21ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀንን በጋራ አከብረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን ከሃገራችን ቁልፍ ሴክተሮች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሾች በመሆናቸው በነዚህ ተቋማት የሚሰጡ ማናቸውም አገልግሎቶች ከሙስና እና ከብልሹ አሰራሮች የጸዱ መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡
ሙስና ፍትሃዊ የታክስ እና የቀረጥ ሥርአትን ያዛባል ያሉት ሚኒስትሯ ይህንንም በጋራ እንታገለዋለን ሲሉ አክለዋል፡፡
የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ መስከረም ደበበ በበኩላቸው ከለውጡ ማግስት ሁለቱ ተቋማት ሙስናን ከመታገል አኳያ ትርጉም ያለው ሥራ መከናወኑን ገልፀው በዚሁም ጥሩ እምርታዎች መታየቱን ጠቅሰዋል፡፡ ለዚሁም ማሳያው ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ የመጣው የገቢ አፈጻጸም መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ደረሰ ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ለመስጠት የቴክኖሎጂ አማራጮችን መጠቀም ተገቢ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሽመልስ ሲሳይ
ፎቶ፡- የትናየት እነዳያፍሩ