✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?
✅ ይህን ቃል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳንሰማው አንቀርም በተለይ አሁን ላይ ይህ ቃል ለብዝዎቻችን እምዛም አዲስ አይደለም ፤ በተለያዩ ሚዲያ ነክ በሆኑ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ቢዝነሶች አገልግሎታቸውን ሲያስተዋውቁ ከዝርዝራቸው መካከል "ዲጂታል ማርኬቲንግ" የሚል እናገኛለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግ አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ የማርኬቲንግ ዘዴ ነው" ሲባል እንሰማለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ዘመናዊዉን የማርኬቲንግ ዘርፍ ሊቀላቀሉ እና ቢዝነስዎን ሊያሳድጉ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘሉ የማነቃቂያ ጽሁፎችም አጋጥመውን ይሆናል ... ለመሆኑ ይህ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ከተለመደው የማርኬቲንግ ዘዴስ በምን ይለያል? እውነት ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስን ማሳደግ ይቻላል? በየትኛው ደረጃ ላይ ያሉ ቢዝነሶችስ ናቸው ዲጂታል ማርኬቲንግን መጠቀም የሚችሉት?
✅ እስቲ እነዚህን እና መሰል ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ዙርያ አጭር ዳሰሳ እናድርግ።ዝግጁ ናችሁ? ተከተሉኝ፦
✅ በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል ማርኬቲንግን በቀላሉ እንድንገነዘብ ስለማርኬቲንግ (Marketing) ጥቅል የሆነ ግንዛቤ እንውሰድ። ማርኬቲንግ (marketing) ማለት "በምርት እና አገልግሎቶች ላይ የገበያውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እሴትን (Value) የማጥናት ፣ የመፍጠር እና ለተጠቃሚው የማቅረብ ሂደት ነው። " ከዚህ ገለጻ እንደምንረዳው ማርኬቲንግ "ሂደት" (process) ነው። ይህ ሂደት :- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ይገዛሉ ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማጥናት እና መለየት ፣ ፍላጎታቸውን መረዳት እና ችግራቸውን ማዳመጥ ፣ ፍላጎታችውን ሊያሟላ ፤ ችግራቸውንም ሊፈታ የሚችል እሴትን አጥንቶ በምርቱ ወይም አገልግሎቱ ላይ ማከል ፣ ከዚያም ማስተዋወቅ ፣ ቀጥሎም ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መልኩ ለሽያጭ ማቅረብ እና ከሽያጩም በኋላ ሸማቹ ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ያለው ደንበኝነት ዘላቂ እንዲሆን መስራትን አቅፎ የያዘ ነው።
✅ ማርኬቲንግ ማለት በጥቅሉ ይህ ከሆነ፤ ዲጂታል ማርኬቲንግ፡ ዘመናዊ የሆነ አንድ የማርኬቲንግ አካል ሲሆን ፤ ይህም ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን( በዋናነት ኢንተርኔትን በመጠቀም) ደንበኞችን የማፈላለግ ፣ ምርት እና አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን በመፍጠር ደንበኝነታቸውን ዘላቂ የማድረግ ሂደት ነው።ይህ እንግዲህ በአጭሩ ስንገልጸው እንጂ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሰፊ እና የተለያዩ ዘርፎች ያሉት እራሱን የቻለ አንድ መስክ ነው።
✅ ማርኬቲንግ ለየትኛውም ቢዝነስ መሳካት ትልቅን ሚና ከሚጫወቱ መሳሪያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።ዲጂታል ማርኪቲንግ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ፤ ደንበኞችን ማፈላለግ እና ምርት እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ የመሰሉ የማርኬቲንግ ስራዎች እንደ ጋዜጣ እና መጽሔት ባሉ የህትመት ውጤቶች ፣ እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ የሚዲያ አውታሮች እንዲሁም በየመንገዱ በተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሰራ ነበር።ዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጣም በኋላ ቢሆን እነዚህ የማስተዋወቂያ መንገዶች ዛሬም ድረስ ይሰራባቸዋል።
✅ ኢንተርኔት እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ ጥቅም ላይ እየዋለ የመጣው ዲጂታል ማርኬቲንግ በተለመዱት የማርኬቲግ ዘዴዎች ለመስራት አስቸጋሪ የነበሩ የማርኬቲንግ ስራዎችን በቀላሉ እና እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመፈጸም በማርኬቲንግ ዘርፉ ላይ ከአሰራር ጀምሮ ትልቅን ለውጥ ፈጥሯል።
✅ ምንም እንኳን በኢንተርኔትን አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች ከዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ትልቁን ድራሻ ቢይዙም ፤ ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ስር የሚካተቱ የማርኬቲንግ ስራዎች አሉ።ለምሳሌ :- በሞባይል መተግበሪያዎች (mobile apps) እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክቶች (SMS) አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።ምክንያቱም ዲጂታል ማርኬቲንግ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው "አዳዳኢስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የሚሰራ የማርኬቲንግ ስራ ነው"።
✅ ዲጂታል ማርኬቲንግ "E-CRM" ላይ የተመሰረተ የንግድ አካሄድ ላይ የሚያተኩር ሲሆን "E-CRM (Electronic Customer Relationship Management)" ቃል በቃል ሲተረጎም "ኤሌክትሮኒክ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር" እንደማለት ሲሆን ፤ ይህም አንድ ቢዝነስ ወይም ድርጅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንበኞቹን መረጃ የሚያሰባስብበት እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና መስተጋብር የሚያስተዳድርበት ስርዓት ነው።
✅ ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!
🔴አድራሻ:-
✅ ስ.ቁ: 0929273364
✅ ዌብሳይት www.mctplc.com
✅ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
✅ በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✅ email: mct16plc@gmail.com
✅ Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
✅ ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
✅ የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!