እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት አስራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ዕለት የከበረ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከአደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሺህ ሰዎች ገደለ።
ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።
ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳወሩ የራሱንም ጠጕር ላጩ አሠሩትም ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሽህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር የከበረ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ ሚካኤል አማልጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
Lᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️ 🟡➪
@Name33O 🟡➪
@Name33O