ተፈጸመ
የኢየሱስ የመስቀል ላይ የመጨረሻ ቃል “ተፈጸመ” የሚል ነበር ። ይህ ኃይለ ቃል የሚያመለክተው በመከራውና በሞቱ የኃጢአት ዕዳ ሙሉ በሙሉ መከፈሉን ነው። ኢየሱስ “ተፈጸመ” ሲል ለደህንነታችን አስፈላጊ የሆነውን ሥራ ጨርሷል። ነገር ግን በመስቀል ላይ መሞቱ ፍጻሜ ብቻ አልነበረም፣ በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል ያለው የአዲስ ኪዳን መጀመሪያ ነበር።
በእሱ መስዋዕትነት፣ ይቅርታ፣ ቤዛነት እና የዘላለም ህይወት ቃል ኪዳን ተሰጥቶናል። ብዙ ሰዎች ከጊዜያዊ ነገሮች ፍጻሜ ለማግኘት ላይ ታች ይላሉ ፣ ነገር ግን እውነተኛ ዘላለማዊ እፎይታ የሚገኘው ክርስቶስ የከፈለልን ዋጋ በመቀበል ሕይወታችን ለርሱ በመስጠት ውስጥ ነው።
ይህ የአለም ሁሉ መድኃኒት በመስቀል ላይ ባደረገው መስዋዕትነት በመከራው የተገለጠውን የፍቅሩን ጥልቀት በመረዳት ልንከፍለው የማይቻለንን ታላቅ የሃጢያት እዳ ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ማጠናቀቁን በማወቅ የተቸረንን የዘላለም ነፃነት እና ተስፋ ልባችን ከፍተን ዛሬ እንቀበል ።ልንረዳህ ዝግጁ ነን!
ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ “ተፈጸመ፡” አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። (ዮሐ 19:30 )
#ያ_መሲሕ
#እነሆ_ያመሲሕ
#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ
Follow 👇👇
@Naol_Tube0