“የጫካ እና የመሳሪያ ትግል የነገሰበት የሀገሪቱ የፖለቲካ ሰንኮፍ ለመጨረሻ ጊዜ ይነቀላል”፦ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
ባለፉት ጊዜያት የስልጣን ሽግግር በተቃርኖ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ተመስርቶ ይመጣ እንደነበር በብልፅግና ፓርቲ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊው ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ይናገራሉ።
ሀገሪቱ ያደረገቻቸው ያልተሳኩ የስልጣን ሽግግሮች የድህነት ቅነሳ ስራችን ውጤታማ እንዳይሆን፣ ከግጭት አዙሪት እንዳንወጣ፣ ስልጡን የፖለቲካ ምህዳር መገንባት እንዳንችል አድርጎናል።
ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በሚል የህዝብን ጥያቄ ይዘናል የሚሉ አካላት ጥያቄ የሚያነሱበትን መንገድ ኢቢሲ በአዲስ ቀን ሾው "የሀገር ጉዳይ" አድርጎ ተመልክቶታል።
በጉዳዩ ላይ ሃሳብ የሰጡት ዶ/ር ቢቂላ፥ በቀደሙት ጊዜያት የስልጣን ሽግግር በጎዳና ላይ ነውጥ፣ በትጥቅ ትግል፣ በመፈንቅለ መንግሥት፣ በተንኮል እና ሴራ የሚፈፀም እንደነበር ይጠቅሳሉ።
የፖለቲካ ምህዳሩ በሰላማዊ መንገድ ሃሳብን ሸጦ እና የህዝብ ይሁንታን አግኝቶ ስልጣን መያዝ ያልተለመደበት እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይህ ታሪክ መፋቅ እንዳለበት ብልፅግና ፓርቲ ያምናል የሚሉት ኃላፊው፤ ለዚህም ተፈፃሚነት ማናቸውንም እርምጃ እንደሚወሰድ ነው የሚገልፁት።