#በዓለ_ጥምቀት_ቅዳሜ_እሑድ_ቢውል
ጾመ ጋድ_ይጾማል
ብዙዎቻችን ስለ ጾመ ጋድ ስናስብ በዓለ ልደትና በዓል ጥምቀት ረቡዕ እና አርብ ከዋሉ ብቻ የሚጾም አድርገን እንወስዳለን። ጾመ ጋድ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። በልደትና በጥምቀት ዋዜማ ላይ ይጾማል። ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው። በዓላቱ ረቡዕና አርብ ቢውሉ የዚያ ለውጥ ማክሰኞና ሐሙስን ጾመን በዕለቱ ጥሉላትን እንመገባለንና እንዲህ ተብሏል አንድም ገሀድ ይባላል መገለጫ ማለት ነው በልደቱ አምላክ ሰው ሆኖ በጥምቀቱ ደግሞ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አይተነዋልና
ወደ መነሻ ሀሳባችን ስንመለስ በቤተ ክርስቲያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ በሆነው ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ ስለ አጽዋማት በሚናገርበት ሐተታው ጾመ ጋድ ከረቡዕና ከአርብ ውጭ ባሉት ቀናት ቢውሉ ዋዜማው እንደሚጾም « ሥርዓት አንድ ጊዜ ከተሠራ አይፈርስምና አንድም አንድ ጊዜ ሲጾም አንድ ጊዜ ሲቀር እንዳይረሳ » በማለት በዓመት በዓመት ጾመ ጋድ እንዳለ ይነግረናል
የሰንበታቱን (የቅዳሜና የእሑድን) ለየት የሚያደርገው ደግሞ ለምሳሌ ልክ ዘንድሮው በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ ሰዓት እንደሌሎች የአጽዋማት ዕለታት እህል ሳንቀምስ ባንውልም ከጥሉላት ምግቦች ግን ተከልክለን መቆየት እንዳለብን ይደነግጋል። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም በዚሁ ላይ ሲጨምሩ በዓለ ጥምቀት ቅዳሜ ወይም እሑድ እንዲሁም ሰኞ ቢውል ቀድሞ ባለው ዕለተ አርብ የጾማችንን ሰዓት ከፍ አድርገን በመቆየት የጾመ ጋድን ጾም ደርበን እንድንጾም ያስተምራሉ።
ጥር - 9-2017 ዓ,ም
◈⊰───── © እሱዬ ይማም
✝ኦርቶዶክስ ተዋህዶ✝
#መልካም_እለት
https://t.me/OrtoPicturehttps://t.me/OrtoPicturehttps://t.me/OrtoPicture