ልደት እና ምስጋና!!!
ከፍጥረታቱ ሁሉ የሰውን ልጅ ልዩና ድንቅ አድርጎ በአምሳሉ የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር በልቦናው ባሰበልን ቀን ሁላችንን ወደ ምድር እንዳመጣ ሁሉ፥ እኔም በቅዱስ ፍቃዱ መስከረም 27 ቀን ይህችን ምድር ተቀላቀልኩ። በህይወቴ ላይ አዲስ አመት ጨምሯልና የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት የሆነው መድኃኔዓለም ስለቸርነቱ የተመሰገነ ይሁን።
በህይወቴ በተፈጠሩ ውጣ ውረዶች ሁሉ አብሮኝ ስለነበረ እና በድክመቴ ስላልተወኝ ፈጣሪዬን በአደባባይ ከፍ አድርጌ አመሰግነዋለሁ። ስለ ሚደንቅ ምህረቱ እና ስለ ፍጹም ፍቅሩም አባታችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
በለተያዩ አጋጣሚዎች የመልካም ልደት ምኞታችሁን ላደረሳችሁኝ ወዳጆቼ እና አክባሪዎቼ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ።