በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ...
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ በሬክተር ስኬል የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ከታች የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡
👉 በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ፦ ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሦሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡
👉 በቤት ውስጥ ከሆኑ፦ በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
👉 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
👉 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ፦ የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሦሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሦሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ መክሯል፡፡