#Breaking_News: በዲጂታል ንብረቶች ላይ የተጣለ አዲስ ማስጠንቀቂያ!
ብሄራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መግለጫ፣ በሀገራችን ማንኛውም አይነት የዲጂታል ንብረት (Digital Asset) ግብይት ላይ ከባድ ማዕቀብ ጥሏል።
እገዳው ምንን ያካትታል?
❌ ማንኛውንም አይነት ዲጂታል ንብረት መላላክ፣ መግዛት እና መገበያየት።
❌ እንደ Binance ባሉ አለም አቀፍ የዲጂታል መገበያያ መድረኮች (Exchanges) ላይ ንብረትን ማስቀመጥ።
ቀደም ሲል የነበረው ገደብ P2P ላይ ብቻ ያተኮረ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የባንኩ መግለጫ ማንኛውንም የዲጂታል ንብረት መጠቀም "ህገ-ወጥ" መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል።
⚠️ ለቻናላችን ቤተሰቦች የሚሰጥ ጥንቃቄ!
በኢትዮጵያ እነዚህን የውጭ መገበያያ መድረኮች (Exchanges) የመዝጋት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረዋል። ስለሆነም፦
• ስልኮች በማንኛውም ሰዓት ሊፈተሹ ስለሚችሉ፣ በነዚህ መድረኮች ላይ ያላችሁን መረጃ ፊት ለፊት (ቀጥታ) እንደማትጠቀሙ አረጋግጡ።
• አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ንብረታችሁን ከአደጋ ጠብቁ።