ከሳርቤት አደባባይ_መካኒሳ_ፉሪ ሀና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የስራ ሂደት ገምግመናል።
18 ኪ.ሜ የሚሸፍነው ይህ የኮሪደር ልማት ስራ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለል የመንገድ ደረጃውን ማሻሻል፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች፣ የህጻናት መጫዎቻዎች፣ ሰፊ የእግረኛ መንገድ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ግንባታቸዉ ሳይጠናቀቅ የቆዩ ህንጻዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት የማስገባት እና ነባር ህንፃዎችን የማደስ ስራዎችን ያካተተ ነዉ።
በከተማ ደረጃ ከጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ በተጨማሪ የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማም ማህበረሰቡን በማስተባበር ተጨማሪ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአቃቂ ቃሊቲ ከተጀመረው ጋር የሚገጥም ይሆናል።
በዛሬው ጉብኝታችን አንዳንድ ቅሬታ የቀረበባቸዉ ጉዳዮችን በቦታዉ በመገኘት ከባለ ጉዳዩቹ ጋር ተመካክረን የፈታን ሲሆን፣ ስራው በፍጥነት እና በጥራት እንዲከናወን ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እየደገፋችሁ ያላችሁ ማህበረታትን እና የአካባቢውን ነዋሪዎች በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
@subitime