ትምራን የሴቶችን ድምፅ በጥምረቱ በኩል ለማሰማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ተፈራረመች
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጽ/ቤት የሆነችው ትምራን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በጉባኤው ጽ/ቤት ተፈራረመች።
በመግባቢያ ስምምነት መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ትምራን ከጉባኤው ጋር በመቀናጀት በጋራ ጉዳይ ላይ ለመሥራት በመምጣቷ ለአመራሮቿ ምስጋና አቅርበው ያለንን የተቋማት ሀብት በማቀናጀት ውጤታማ ሥራ ለመሥራት አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።
አክለውም ትምራን የሴቶችን ድምፅ በጥምረቱ በኩል በማቀናጀት የሴቶችን የመምራት አቅም ለማሳደግ እና ሴቶች ተገቢውን የሓላፊነት እና የሥራ ደረጃ እንዲያገኙ የምትሠራ ድርጅት በመሆኗ፣ በጉባኤው በኩል አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግላት ተናግረዋል።
አያይዘውም ሴት እናት፣ ሚስት፣ እኅት እና ልጅ ነች የሚለው አባባል ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ፣ ሴቶችን መደገፍ እና ማብቃት የራስን አካል መደገፍ እና ማብቃት ነው፤ ሴቶች በሁሉም መስክ ትርጉም ያለው ውክልና እና ሓላፊነት ያገኙ ዘንድ በጥምረቱ በኩል የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
የትምራን ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ሶሎሞን በበኩላቸው፣ ትምራን የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ ትርጉም ባለው ደረጃ ማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሁሉንም የጥምረቱን አባላት በማሳተፍ፣ የሴቶችን አቅም በማጎልበት እና ድምፃቸው ከፍ ብሎ እንዲሰማ የምትሠራ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኗን ገልጸው፣ የሴቶች ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክር ሂደት እና ውጤት፣ በሀገር ልማት እና እድገት፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ፣ ወዘተ ሁሉ በተገቢው ሁኔታ ይታይ ዘንድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የምትሠራ ድርጅት እንደሆነች አብራርተዋል።
በተጨማሪም የሴቷ አጀንዳ ማለት የባለቤቷ፣ የአባቷ፣ የልጇ፣ የወንድሟ አጀንዳ በመሆኑ፣ የሴቶችን አጀንዳ መደገፍ የሁሉንም ማኅበረሰብ አጀንዳ እንደ መደገፍ የሚቆጠር ነው። በዛሬው ዕለት በተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ሴቶች በመሪነት፣ በሰላም ግንባታ፣ በሥራ፣ በትምህርት፣ ወዘተ መስኮች ያላቸው ተሳትፎ ትርጉም ያለው ይሆን ዘንድ አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
#TIMRAN@5