መልካም ልደትአንዳንዴ ህይወቴን ባንተ ጫማ መሀል ከትቼ ሳረገዉ
ወይ አይጠብ አይሰፋኝ
ወይ በቅቶ አያረካኝ
እሱም እዚያ ማዶ
የኔም ልብ ሰርዶ
ያንተም ቅዝም ወዲያ
እንደተላለፍን ላንገናኝ🙈 ኤ.......ዲ........ያ
እንዲሁ ግርም አለኝ
አጃ....ኢብ ነዉ አቦ
አምላክን የሚያህል ከግዝፈቱ ጠቦ
ባጭር ቁመትና በሚጢጢ ደረት
ከማህፀን ወጥቶ ሲወለድ በበረት
አጃ.....ኢብ
ባለስልጣን ሳለ እንደ ሎሌ ወርዶ
በዳይን ለማዳን ዳኛዉ አገርድዶ
አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ..........
የምድርስ ድፍረቷ እንደምን ቻለችህ
ምን ቃል ብትነግራት ነዉ?.........
ጌታዋን አምላኳን በበረት ወስና ፀንታ ያቆየችህ
እንደምን ብትወደን
እንዴት ብታፈቅረን
እንዴት ብታከብረን
አረ እንደምን ብለህ ታናሽነት መረጥክ
አንድ የምትለዉን ልጅህንም ሰደድክ።
አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ
የትህትናህ ድንቁ
ምስጢርህ መርቀቁ
አለምን ከመፍጠር ሰ'ዉን የማዳንህ እጅጉን መድነቁ
መልካም ልደት ላንተ
ከክብሩ ወርዶ ለተንከራተተ
መልካም ልደት ለኔ
ከበረት ወጥቼ ለከበርኩኝ እኔ።።።።።።።።።
።።።።።።።።።
አጃኢብ🙈
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤❤
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizitawolde_poems@Tizitawolde_poems@Tizitawolde_poems@Tizitawolde_poems