Ministry Of Education News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


📚Disclaimer: This is an unofficial channel created solely to share fast, timely educational information directly with students.
🔵ከ1-12 መፅሃፍት ለማግኘት: @STBookbot
🔴ለFreshman : @Freshman_Robot
«Buy Ads» @MoeAds_bot or https://telega.io/c/Tmhrt_minister

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🌟"ማትሪክ ፈተና" የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፈተናቸዉ ብቁ ለማድረግ የተከፈተ ቻናል ሲሆን በዉስጡ ፥

😊የማትሪክ ጥያቄዎች ከነመልሳቸዉ ፤
😊Model Exam Questions
😊Mid Exam Final Exam Questions
😊ከ9-12 በምዕራፍ የተከፍፈሉ አጫጭር ኖቶችን ፤ በPDF ፤ በDOCX ፤ በPPT
😊የአጠናን ስልቶች ፤
😊ትኩስ የትምህርት መረጃዎች

እንዲሁም ተማሪዎችን የሚጠቅሙ ማቴሪያሎች በሙሉ በነፃ የሚገኙበት ምርጥ የቴሌግራም ቻናል ነዉ! 😊

አሁኑኑ Join በማለት ጥናታችሁን አቀላጥፉ!
❤️https://t.me/+szBcUvcvedQzNGFk
❤️https://t.me/+szBcUvcvedQzNGFk


Репост из: Medical GateWay🎓
✈️MGW Freshman Tutorial 🟫

➡️በ2019 Freshman ለምትጀምሩ የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ከRemedial ያለፋችሁ እንዲሁም Grade 12 ተማሪዎች ይህ ለእናንተ ነው 🥰

🕊MGW, እጅግ ወሳኙንና ምርጡን የ Freshman Tutorial እና ባለውለታ እንጠቁማችሁ ፤ እናስተዋዉቃችሁ 🙌

ለመሆኑ ምን ምን ኮርሶች ይሰጣሉ ?

Natural Science Freshman Courses List for Our Tutorial.

⭐Logic and critical thinking
⭐Psychology
⭐Geography
⭐C.English
⭐Freshman Mathematics
⭐Physics
⭐Emerging Technology
⭐Anthropology
🔂History
✅Applied Mathematics-1 (For ASTU)
✅Chemistry (For ASTU)

Freshman Social Science Courses given at our classes:

✅Logic and Critical thinking
✅Psychology
✅Civics and Moral education
✅Global Trends
✅Entrepreneurship
✅Economics
✅Anthropology
✅Geography
✅Communicative English
✅Emerging Technology
✅Mathematics for Social

🤳Freshman አሪፍ Grade ሰርተው የሚፈልጉት Department እንዲገቡ በማስቻል ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፤  ሴሜስተሩን ሙሉ እኛጋር ናችሁ 🤗

🖱ይህንን ወሳኝ የመጀመሪያ ዓመት በFreshman ጥሩ GPA and Coc ሰቅላችሁ  ማለፍ ከፈለጋችሁ i.e We are your perfect choice 💯

ተቀላቀሉ እጅግ እጅግ ትወዱታላችሁ ፤ በጣም የሚገርም GPA ታስመዘግቡበታላችሁ 🥰

MGW, Freshman መማሪያ APPን ከ Playstore  ለማውረድ ይሄንን Link ተጠቀሙ ⬇️
💻https://play.google.com/store/apps/details?id=com.medical.tutorial.app

🔥ባለፈው ዓመት ከነበረን በውጤት የታጀበ አስገራሚ ቆይታ በጥቂቱ👇
https://t.me/MGW_Freshman_2019

📱ስለቱቶሪያል ለመጠየቅ
📞0704282565
📞0906014772

💬APP Support : @MGW_Support

እኛን ለመቀላቀል👇
https://t.me/MGW_Freshman
https://t.me/MGW_Freshman


#JimmaUniversity #Freshman

የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 4–5 2019 ዓ.ም. በተመደባችሁበት ካምፓስ ይካሄዳል። የተመደባችሁበትን መረጃ በJU Portal ይመልከቱ እና አስፈላጊ ሰነዶችን ይዘው ይምጡ።

⚡️Natural Students --Institute Of Technology

⚡️Social Students --- College of Agriculture

⚡️Veternary Medicine --Jimma University

በዚህ Portal
👉 https://portal.ju.edu.et
Admission Number በማስገባት Dormitory, Cafeteria እና Section ማየት ትችላለችሁ ::

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister

13.6k 0 115 30 47

ለ2019 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁና #ለቃል_ፈተና የተመረጣችሁ ፈተናው መስከረም 21/ 2019 ዓ.ም በኮሌጁ ውስጥ ይሰጣል።

➻ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ያመለከታቸሁ ጠዋት እና ከሰዓት

➻ በአጠቃላይ ነርሲንግ ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ መስከረም 21/2019 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።

ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ አመልካቾች ዝርዝራችሁን በኮሌጁ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻ ማየት ትችላላችሁ።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister

20k 0 11 28 66

#DebreMarkosUniversity

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ለፕሬዝዳንት እና ለሦስት ምክትል ፕሬዝዳንት የአመራርነት ሥራ መደቦች ላይ ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡

ለውድድር ክፍት የሆኑ የአመራርነት ሥራ መደቦች፦
➻ ፕሬዝዳንት
➻ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት

ከላይ በተያያዘው ምስል የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የስራ ቀናት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንጻ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 106 ወይም በአዲስ አበባ በሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም.pdf
332.0Кб
የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦
- ጀማሪ መምህር፣
- መለስተኛ መምህር፣
- መምህር፣
- ከፍተኛ መምህር፣
- ተባባሪ መሪ መምህር፣
- መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው።

በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው።

ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል።

መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል።

በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።

ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው።

በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል።

አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል።

በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል።

በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል።

የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል።

አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል።

በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል።

በተጨማሪም፦

👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።

👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።

👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር።

👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር።

👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር።

👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር።

👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር።

👉
ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር።

የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል።

በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል።

ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል።

የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


የመምህራን የደረጃ ዕድገት አዲስ መመሪያ ተደነገገ!

​በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መምህራን የደረጃ ዕድገት ለማግኘት ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች መካከል ቢያንስ 50% እና ከዚያ በላይ ማሳለፋቸው በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ ደነገገ።

​በተጨማሪም የመምህራን ሥራ ምዘናና ዕድገት በሚከተሉት ዋና ዋና መስፈርቶች ላይ የተመሠረተ ይሆናል፦

📧​የተማሪዎች የትምህርት ውጤት

📧​ተተግብረው ውጤት ያመጡ ጥናትና ምርምሮች

📧​ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የተደረገ እገዛ የሚሉት እንደሆኑ ሪፖርተር በዛሬ እትሙ አስነብቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


#ጥቆማ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም (Alternative Teachers' Training Program) ለዘጠኝ ወራት ሰልጥነውና ውል ፈርመው በተለያዩ ክልሎች በመምህርነት ለማገልገል የሚፈልጉ አመልካቾችን ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም #ወጪያቸውን_ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የስልጠና ዘርፎች
➻ Biology
➻ Chemistry
➻ Mathematics
➻ Physics
➻ History
➻ Geography
➻ Citizenship
➻ Economics
➻ Agriculture
➻ Performing & Visual Arts
➻ English Language
➻ Information Communication Technology

የማመልከቻ መስፈርቶች፦
● አመልካቾች ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው እና የመውጫ ፈተና ያለፉ
● ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የኦፊሺያል ትራንሰከሪፕት ማስላክ የሚችሉ
● በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያላቸው
● ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኝነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 25/2019 ዓ.ም

ያመልክቱ 👇
https://forms.gle/PhDzQiRbRjkrRcRp8

ከላይ በተገለፀው ሊንክ ላይ በመግባት አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላትና የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በማያያዝ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ለሴት አመልካቾች እንዲሁም የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት ለማይፈልጉ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


#ጥቆማ

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የስልጠና ዘርፎችን በማካተት ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን የስልጠና መስኮች የሚያስተዋውቅበት የመረጃ ሳምንት ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ሆኗል።

ተቋሙ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች፦
➻ በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች
➻ በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች
➻ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) (ደረጃ 8) በሁለት ፕሮግራሞች

በኢንስቲትዩቱ የሚሰጠው ስልጠና 50 በመቶ የንድፈ-ሃሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ እንደሆነ ተገልጿል።

ተቋሙ በ16 የሳተላይት ካምፓሶች እና በሁለት ማዕከላት አማካኝነት ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


📎2019 Remedial  Discussion  groups.

👨‍🏫 Remedial Universty የደረሳችሁ ተማሪዎች በየግሩፖቻችሁ ገብታችሁ መተዋወቅ ይኖርባቹሃል። ትውውቃችሁን ግቢ ሳትገቡ በቴሌግራም ከጨረሳችሁ  ትምህርቱን በአንድነት ትወጣላችሁ❗️

🔸ስለጉዞ መረጃ :ግቢም ከገባችሁ በኋላ ፋይል ለመለዋወጥ እንዲሁም የRemedial  የሚድና ፋይናል ሁሉንም በአንድ  ለመለዋወጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው🔸

አስታዉሱ :መረጃ  የዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ  ስኬታማነት  ከሚወስንባቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛዉ ነው ❗️

✍️ለሁሉም ጓደኞቻችሁ ሼር
አድርጉላቸው
🔻

1.Bahirdar university 👇
https://t.me/BahirdarRemedial2019

2.Gonder university 👇
https://t.me/GonderRemedial2019

3.Wollo university 👇
https://t.me/WolloRemedial2019

4.Debremarkos university 👇
https://t.me/DebremarkosRemedial_2019

5.Debretabor university 👇
https://t.me/DebretaborRemedial2019

6.Woldia university 👇
https://t.me/WoldiaRemedial2019

7.Mekelle university 👇
https://t.me/MekelleRemedial2019

8.Wollega university👇
https://t.me/+Q809vPXbbUM1NjA0

9.Oda bultum 👇
https://t.me/+kn03I1TfVl1hYmQ0

10.Ambo university 👇
https://t.me/+m7b60REIh71iYWU0

11.Metu university 👇
https://t.me/+k8VIsj8Gt-4xMDc8

12.Bule hora university 👇
https://t.me/+AwowcM1VK2M1NDBk

13.Diredawa university 👇
https://t.me/+JG7dHAH3onAxMmNk

14.Selale university 👇
https://t.me/+DPv0Bgy8Of5hZjE0

15.Arbaminch university 👇
https://t.me/+OnkYs5Ktv7ExYWM8

16.Dilla university👇
@DillaRemedial2019

17.Wachamo university👇
@WachamoRemedial2019

18.Wolaita university👇
@WolaitaRemedial2019

19.Jinka university👇
https://t.me/+VpkfJt3MdfY4YzE0

20.Mizan tepi university👇
https://t.me/+L9i_Lguz_dJlOTFk

21.Bonga university👇
https://t.me/+7Be9c0riXSMzZDNk

22.Werabe university👇
https://t.me/+60mr4a_DNJI0NDFk

23.Jigjiga university👇
@JigjigaRemedial2019

24.Semera university👇
@SemraRemedial2019

25.Asossa university👇
https://t.me/+_mXPUIqkFJk0MDVk

26.wolkite university👇
@WolkiteRemedial2019

27. Debrebrehan university👇
@DebrebrehanRemedial2019

28. Haramaya university 👇
@HaramayaRemedial2019

29. Jimma university 👇
https://t.me/+eT9RGNGDo383OGFk

30. Madda walabu university👇
https://t.me/+byLRZcKqRFxiZWQ0

📣ለበለጠ ታዋቂ የRemedial ቻናል ተቀላቀሉ @Remedial_Hub ✔️

24.9k 0 179 18 87

ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
 
ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister

24.5k 0 138 27 46

🌟 መልካም ዜና  ለሪሜዲያል ተማሪዎች በሙሉ🌟

Remedial Hub Tutorial❗️

📚 በ 2019 ዓ.ም በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት ውስጥ በሪሜዲያል ፕሮግራም ለታቀፋችሁ የሪሜዲያል ተማሪዎች ፤ ስለ Remedial Hub Tutorial ሰምተዋል❓

📝 Remedial Hub Tutorial ጥራታቸውን የጠበቁ ፤ ለመረዳት ምቹ ና ግልፅ የሆነ በአማርኛ-እንግሊዝኛ የተብራሩ ኖቶችን ፥ እስከ 4k በሚደርስ የቪዲዮ ጥራት በ Animated ቪዲዮዎች እንዲሁም በ ቮይስ ና በ Diagram ማብራሪያ ለሪሜዲያል ተማሪዎች ቲቶርያል የሚሰጥ ድርጅት ነው።

📚 ከቲቶርያሉ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ከግቢ ፈተናችሁ ጋ በቀጥታ የሚገናኙ ጥያቄዎችን ከነማብራሪያቸው በማቅረብ ፤ ለ ዩኒቨርሲቲ ና ለ ሀገር አቀፍ መመዘኛ ፈተና ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አስተዋዕፆው የጎላ ነው።

🔛 ተማሪዎች የሪሜዲያል ፕሮግራምን በስኬት አጠናቀው ወደ መጀመሪያ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለመሆን በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ፤ አስፈላጊ ና ጠቃሚ የሆኑ የንባብ ማቴሪያሎችን ና የፈተና መስሪያ ዘዴዎችን በ PDF ና በ Powerpoint ፋይል በማቅረብ እንዲሁም የአምና የሪሜዲያል ፈተናዎችን ከነማብራሪያቸው በመስራት ተማሪዎች አስፈላገውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ያደርጋል።

📚 Remedial Hub Tutorial  በ 2015 ዓ.ም ከተመሰረተበት አመት ጀምሮ በአጠቃላይ ከ 3 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ አስተምሮ ከ75% በላይ ተማሪዎች ጥሩ ወጤት አምጥተው ወደ አላማቸው ግብ አድርሶቸዋል ።

💻ባለፈው ዓመት ከነበረን አስገራሚ ቆይታ በጥቂቱ ለመመልከት 👇

https://t.me/+uwCwTxlnMb5lM2I0

🖱እንዴት እንመዝገብ ?

➖ ለመመዝገብ ይህንን Link ይጠቀሙ 👉🏽 @RemedialHubBot

📌 ለተጨማሪ መረጃ Official ቻናላችንን ይቀላቀሉ @Remedial_Hub


Study Schedule @Tmhrt_Minister Sample for highschool.pdf
972.9Кб
📝የጥናት ፕሮግራም ሰሌዳ

➖ይሄ Pdf በውስጡ
🔸 የጥናት ፕሮግራም
🔸 የየቀን ተግባራት (To do List) እና
🔸 የቀንና የማታ ውሎ (Day and Night Routines) በአንድ ላይ የያዘ ነው። እንደሚጠቅማችሁ ሙሉ ዕምነታችን ነው።

🔹ማስታወሻ: ውስጡ ያለውን የጥናት ፕሮግራም እናንተ በፈጋችሁት መንገድ መቀያየር ወይም ማስተካከል ትችላላችሁ።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


ማስታወቂያ

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ያለፋችሁ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው፤

1. ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤ ለምሳሌ፡- ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ ወዘተ፣
2. ለመኝታ አገልግሎት የሚያስፈልጉ አንሶላና ብርድ ልብስ፣
3. እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጣቸውን መሸኛና የትምህርት ውጤታቸውን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤
4. ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ትምህርት ሚኒስቴር 💠

🔴ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ!

✈️https://t.me/Tmhrt_Minister
✈️https://t.me/Tmhrt_Minister


🌟"ማትሪክ ፈተና" የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለፈተናቸዉ ብቁ ለማድረግ የተከፈተ ቻናል ሲሆን በዉስጡ ፥

😊የማትሪክ ጥያቄዎች ከነመልሳቸዉ ፤
😊Model Exam Questions
😊Mid Exam Final Exam Questions
😊ከ9-12 በምዕራፍ የተከፍፈሉ አጫጭር ኖቶችን ፤ በPDF ፤ በDOCX ፤ በPPT
😊የአጠናን ስልቶች ፤
😊ትኩስ የትምህርት መረጃዎች

እንዲሁም ተማሪዎችን የሚጠቅሙ ማቴሪያሎች በሙሉ በነፃ የሚገኙበት ምርጥ የቴሌግራም ቻናል ነዉ! 😊

አሁኑኑ Join በማለት ጥናታችሁን አቀላጥፉ!
❤️https://t.me/+szBcUvcvedQzNGFk
❤️https://t.me/+szBcUvcvedQzNGFk

Показано 16 последних публикаций.