ፌደሬሽንን መሻር፣ ጦርነትና ዕልቂት ያመጣል እንጂ መፍትሔ አይሆንም፦ ታሪክም ይሄንን ያስረዳል።
=================
በ1962 (እኤአ): ኢትዮጵያ፣ ከኤርትራ ጋር የነበራትን የፌዴሬሽን ውል ሽራ፣ ኤርትራን በጉልበት 'አዋሃድኩ' ያለች ዕለት፣ የኤርትራ ኃይሎች፣ የትጥቅ ትግል ለመጀመር የመጀመርያውን ጥይት ተኮሱ። በዚህ ቀን፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ በኢምፓየሩ ውስጥ ሰፍኖ የነበረው አንፃራዊ ሰላም ደግሞ ላይጠራ ደፈረሰ። ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ በይፋ፣ በጠመንጃ አፈሙዝ ብቻ የሚነጋገሩበት የብረት ፖለቲካ ሆነ። የፖለቲካ ድልም፣ በደም የሚበየን ሆነ።
ገና በወጉ ያልተተገበረውን ፌደሬሽን በማፍረስ "አንድነትን አመጣን" ያሉት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን፣ የኢትዮጵያን የቁልቁለት ጉዞ አስጀመሩ። ለመቶ ሺህዎች እልቂት ምክንያት የሆነውን የጦርነት ወላፈን ለመመገብ፣ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ወጣቶች መማገድ ጀመሩ።
በ2018ም (እኤአ)፣ ገና በወጉ ያልተተገበረውን የኢትዮጵያ ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝም ለመሻር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በመንቀሳቀስ፣ እስከዚያ ወቅት ድረስ የነበረውን አንጻራዊ ሰላም በማናጋት፣ የዘር ማጥፋት ጦርነቶችን ለማድረግ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀመረ፣ አስጀመረ። "የአንድነት ጠበቃ ነን" የሚሉት የኢትዮ-አማራ ልሂቃንም" የዚህ ዘመቻ ፊታውራሪ በመሆን "ከመንግሥት ጎን ነን" እያሉ ፎከሩ። #አብይአህመድ ሥር ተኮልኩለው፣ ያንን ያረጀ፣ የነተበና የከሸፈ "የኣሃዳዊነት" ወግ፣ "መደመር" በሚል ካባ ሸፋፍነው፣ ፌደራሊዝሙንና ሕገ-መንግሥቱን ለመሻር፣ "የብሔር" ፖለቲካ የሚሉትን የብሔር-ተኮር ፍትህ ፖለቲካ (politics of ethno-national justice) ለማጥፋት፣ ለዚህም ሲባል "ብሔርተኞችን" (በመግደል) ለማጥፋት በሰፊው ተንቀሳቀሱ። የተነጣጠሩ የፖለቲካ ግድያዎችን፣ የጅምላ ፍጅትና እስርን፣ ማፈናቀልና የዘር-ማጽዳትን ፈጸሙ፣ አስፈጸሙ።
ይሄም አልበቃ ስላላቸው፣ ትግራይ ምርጫ ስላደረገ፣ "ሉዓላዊነታችን ተደፈረ፣ አንድነታችን አደጋ ተደቀነበት" እያሉ፣ የለየለት የዘር ማጥፋት ጦርነትን ለማድረግ፣ ከውጭ ኃይሎች ጋር ጭምር ተባብረው፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ ዘመቱ። የክፍለዘመኑን አውዳሚ ጦርነት ተገበሩ። በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብን ፈጁ።
ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝምን በመሻር "አንድነትን ለማምጣት" በሚል ሰበብ የመዘዙት ሰይፍ፣ የዘር ማጥፋት ጦርነትን፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቋንቋ ቋሚ አካል አደረጉ።
በመሆኑም፣ ዛሬም፣ አገሪቱ፣ በዘር ማጥፋት ጦርነቶች ማዕበል እየተናጠች ትገኛለች።
የሚገርመው፣ ባልጠበቁት መንገድ የዚህ ዓይነት ጦርነት ተጠቂ (ፈጻሚም) የሆኑት የኢትዮ-አማራ ልሂቃን፣ ዛሬም ከዚህ ጥፋት ለመታረም አለመቻላቸውና ዛሬም "የብሔር ፖለቲካን" እና ፌደራሊዝምን ማፍረስ፣ ቁልፍና ዋነኝ የፖለቲካ ማታገያ የትግል ርዕሰ-ገዳይ አድርገው መቀጠላቸው ነው።
ከዙህ በፊት ደጋግመን እንደተናገርነው፣ አንዴ የፌደራሊዝም ጎማዎች መሽከርከር ከጀመሩ በኋላ፣ ጎማውን ለማስቆም መሞከር፣ ሞካሪውን ጭዳ (cidhaa) ያደርጋል እንጂ መሽከርከሩን አያስቆመውም። Once the wheels of federalism has started to run, you may try to stop it at your own peril.
ሕብረ-ብሔራዊ ፌደራሊዝምን ለመሻር የተደረገው የቅርብ ዓመ ሙከራ፣ የመጨረሻ ውጤቱ፣ በሕብረ-ብሔራዊ ፌደሬሽን አማካኝነት ለመፍጠር የተሞከረውን ሕብረ-ብሔራዊ ትብብር፣ አጋርነት፣ እና ከብሔር ነፃ የሆነ (ethno-nationally secular) ወይም ሕብራዊ (plurinational) የሆነ ኢትዮጵያዊነት ድምጥማጡን አጥፍቶታል። የዘር ማጥፋት ጦርነትና የአገር ውድመት አስከትሏል።
ከዚህ አልፎም፣ ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለውን በሆነ ዓይነት መዋቅር (በፌደሬሽን፣ በኮንፌደሬሽን፣ ወዘተ) የመሰባሰብና የትብብር ተስፋ ለዘላለሙ አክስሟል። በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ የነበረ (ኖሮ የሚያውቅ ከነበረ) የኢትዮጵያዊነት ተስፋን ገድሎአል። መልሶ እንዳያንሰራራ አድርጎ ቀብሮታል።
Adios!