ብርሃኑ ጁላ--የትርክት ጠለፋ ወይስ የማናለብኝነት መቀላመድ?
===================
የአብይ አህመድ አገዛዝ: በተጠለፉ: በተገደሉ (ወይም እራሱ በገደላቸው): እና ታፍነው ደብዛቸው በጠፋ ሰዎች ሥም ንግድ ከጀመረ ከራርሟል::
በየጊዜው: መግደል/መፍጀት: ማፈን: መሰወርና መዝረፍን ከመፈፀሙና ከማስፈፀሙም በላይ: የግድያ/የፍጅት: የጠለፋ: የአፈናና የዘረፋ ተግባር (ሳይፈፀምም ቢሆን "ተፈፀመ" የሚል) ትርክት በማሰራጨት: ተቃዋሚዎቹን ተወቃሽ በማድረግ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የጀመረው ገና ሥልጣን በያዘ ማግስት ነው::
ኢንጂነር ስመኘውንና ጀነራል ሰዓረን አስ/ገድሎ: ገዳዮቹ የለውጡ ተቃዋሚዎች ናቸው አለ::
አምባቸውና ባልደረቦቹን አስ/ገድሎ: ገዳዩ አሳምነው ፅጌና ቡድኑ ነው አለ::
በአብዮት አደባባይ የግድያ ሙከራ ሊፈፀምብኝ ነበር ብሎ ይህንንም የሞከሩት: "ወያኔ" እና "ሸኔ" ናቸው በማለት ብዙ ተጋሩና ኦሮሞዎችን ለግድያ: ለእስርና ለእንግልት ዳረገ::
ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድሎ: ገዳዮቹ "ትግርኛና ኦሮሚኛ ተናጋሪዎች" ("ወያኔ" እና "ሸኔ") ናቸው አለን::
ቀጠለና 17 ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታገቱ: አጋቹም "ሸኔ" ነው አለ:: ከቀናት በኃላ: የመንግሥት ቃልአቀባዩ ንጉሱ ጥላሁን በቴሌቭዥን ቀርቦ: "መንግሥት 26ቱን (ከ17ቱ ማለት ነው!😲😂😲) አስፈትቷል: የሚቀሩትንም ለማስለቀቅ እየተንቀሳቀሰ ነው" አለ::
ከአንድ ወይም ከ2 ሳምንት በኃላ: አብይ እራሱ: ፓርላማ ቀርቦ "የተጠለፈ ሰው የለም" ብሎ ተናገረ::
ያም ሆኖ: 17ቱን ተማሪዎች አግታችኃል በሚል ከአስር በላይ የሚጠጉ ወጣቶችን ከደንቢዶሎም: ከፊንፊኔም ይዘው ወደ እስር ቤት ጨመሩ::
እነዚህ ወጣቶች በገላን እስር ቤት ያለክስና ፍርድ ሲማቅቁ ቆይተው: ኃላ ላይ ፍርድ ቤት አቁሞ: ያለምንም ማስረጃ ("ምስክሮቹ" በችሎት ቆመው "የምናውቀው ነገር የለም" እያሉም ጭምር) ወጣቶቹን እስከ 12 ዓመት የሚደርስ እስራት አስፈረደባቸው:: ተከሳሾቹ ይግባኝ ብለው: እስከ ሰበር አቤቱታ ድረስ ሂደውም: ሰሚ አጥተው: ይኸው እስከዛሬም ድረስ በእስር ይማቅቃሉ::
ሰሞኑን ደሞ: እንደ ወታደር ጦርነት መዋጋት (እንደ አዛዥም ማዋጋት) ሲያቅተው በሚዲያ የውሸት ወሬ በመንዛት ላይ የተሰማራው ብርሃኑ ጅሉ: "ተማሪዎቹን የጠለፈው ጫላ አሻግሬ የተባለ የአማራ ተወላጅ ነው:: እሱም ተገድሏል" ብሎት አረፈው::
አንድ ነገር ግልፅ ይሁን:- ማንም ሰላማዊ ዜጋ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል መያዝ: መታገትና መሰወር የለበትም:: ይህ: መብትን ከመፃረር አልፎ: ወንጀልም ስለሆነ በብርቱ ሊወገዝ ይገባዋል:: ታጋቾች ሊፈቱና ወደ ቤተሰቦቻቸው ሊቀላቀሉ ይገባል::
ማንም ግለሰብ የፖለቲኮ-ወታደራዊ ተገዳዳሪዎች ሰለባ ሊሆን አይገባውም::
በመሠረቱ: ሰዎችን ከእገታ መጠበቅ: ከታገቱም ማስለቀቅ የመንግሥት ኃላፊነት ነው:: ይሄን ማድረግ የሕዝብን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የሕግ ማስከበር ግዴታው አካል ነው:: ይሄን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣም ተጠያቂነቱ የመንግሥት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል::
በእነዚህ ተጠለፉ በተባሉ ተማሪዎች ጉዳይ ላይም ተፈፃሚነት ሊኖረው የሚገባው መርህና ሕግ ይኸው ነው::
ሆኖም: እስከዛሬ ድረስ: የታገቱት ተማሪዎች ዝርዝር (ንጉሱ ጥላሁን "ተለቀዋል" ያላቸውን ጨምሮ): የተማሪነት ሁኔታ (status): የቤተሰብ/የመኖሪያ አድራሻ: ስላሉበት ሁኔታ (ካሉ): ወዘተ: በመንግሥትም ሆነ በዩኒቨርስቲው አስተዳደር በኢፋ የተሰጠ መረጃ የለም::
እስከዛሬ ድረስ: የእገታ ትርክትና ተለዋዋጮቹ የትርክቱ ተጠቂዎች እንጂ: የታጋቾች ማንነት ከሕዝብና ከመገናኛ ብዙሃን እንደ ተሰወረ ነው::
አብይ በፓርላማ አልተፈፀመም ያለውን ጉዳይ: የወቅቱ የመንግሥት ቃል-አቀባይ ንጉሱ ጥላሁን ("ታጋቾችን አስለቅቀናልና" እገታው ከሽፏል) ያለንን ጉዳይ: ያም ሆኖ ከአስር በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአጋችነት ተከሰው በሃሰተኛ የፍርድ ሂደት ለእስር በተዳረጉበት ጉዳይ: አሁን ብርሃኑ ጁላ መጥቶ: አጋቹ እኮ "የአማራ ተወላጅ የሆነ ጫላ አሻግሬ ነው" ማለቱ ምን ማለት ነው?
ነገሩስ በማንአለብኝነት የተደረገ ተራ መቀላመድ ነው? ወይስ ለወቅቱ የፖለቲካ/የጦርነት ዘመቻ ግብዓት እንዲሆን የታሰበ የትርክት ጠለፋ?
መቼም ብርሃኑ ጁላ በራሱ ተነሳሽነት እንዲህ ያለ የትርክት ጠለፋ ሥራ ላይ ይሰማራል ለማለት የሚደፍር የለም:: (መቀላመዱ እንኳን የሙሉ ጊዜ ሥራው ነውና ማንም ይሄን አይክድም::) ነገር ግን ይሄ የሰሞኑ ንግግር: ከመቀላመድ በላይ ስለሆነ ተገቢው አትኩሮት ሊሰጠው ይገባል:: ምንጩም እራሱ አብይየሚመራው የሥርዓቱ የፕሮፓጋንዳ ማሺንነው::
አሁን በብርሃኑ በኩል ሊባል የተፈለገው: በኢትዮጵያ ውስጥ: ከሰማይ በታች ለሚከሰት ነገር ሁሉ: የአማራ ክልል ታጣቂዎችን ተጠያቂ በማድረግ ሰፊ የጦርነት ዘመቻ (ከፕሮፓጋንዳ የማይዘል ቢሆንም) በክልሉ ሕዝብ ላይ ማድረግ ነው:: (ተመሳሳይ ዘመቻ በትግራይና በኦሮሚያ ሲካሄድ እንደነበር ልብ ይሏል::)
ያለ የሌለ ክስና ጥፋት በእነሱ ላይ በመለጠፍ አገዛዙ ለሚወስደው የግፍ እርምጃ ምክንያት (justification) ለመስጠት መሆኑነው::
እግረ-መንገዱንም ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በኦሮሚያ እየተደረገ ያለውን ውጊያ ከአማራ ክልል ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ጋር በማስተሳሰር ሁለቱንም ባንድ ቅርጫት ጨምሮ ለማጥቃት የሚጠቅም ትርክት መፈብረኩ ነው::
የሰሞኑ የብልጥግና ካድሬዎችና 'የሚዲያ ሠራዊት' አባላት ውይይትም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው::
የውይይታቸው አቅጣጫም: "ሸኔን የሚደግፈው/ከመጀመሪያውም የፈጠረው: የአማራ ክልል ታጣቂዎች ናቸው" የሚል ትርክት ላይ ያተኮረ የሶሻል ሚዲያ አጀንዳ መቅረፅ አለብን የሚል ነው::
ከዚህ በፊት: ከትግራይ ጋር በሚዋጉበት ወቅት "'ሸኔን' የሚደግፈው/የፈጠረው 'ወያኔ/ጁንታ' ነው"ሲሉ እንደነበር አይረሳም:: (እነ ግብፅና ሌሎች "ታሪካዊ ጠላቶች" ሲጨመሩበትማ: ይሄ "ሸኔ" ፈጣሪው አበዛዙ!!!😂😂)
የሆነ ሁኖ: በዚህ የተለመደ የብልጥግና (የትርክት ጠለፋ) ስልት የሚታለል ሞኝ የለም::
የኦሮሞ ሕዝብ: በዚህ የእገታ ትርክት መንስኤነት የጠፉ ነፍሶችን: የደረሱ እንግልቶችን: የተፈፀሙ ግፎችን አይረሳም::
ከተባለው የጠለፋ/እገታ ተግባር ጋር ግንኙነት በሌለው ሁኔታ (ልጃቸው ጫላ አሻግሬ የWBO አባል ስለሆነ በሚል ሰበብ) በቄያቸው ደጅ ላይ የተረሸኑትን ወላጆቹን መቼም አንረሳም::
Jaal Caalaa አሻግሬን የበላውን አገዛዝም (ብርሃኑ ጅሉ እንዳለው: ጏዱ ተሰውቶ ከሆነ) መቼም አንረሳውም:: አገዛዙን: ዛሬ እስከመጨረሻው እንፋለመዋለን: በሂደትም ሙሉ በሙሉ እንዳይመለስ አድርገን እንቀብረዋለን::
በመቀላመድም ይሁን በትርክት ጠለፋ ከጥፋት የሚድን የብልጥግና አገዛዝ አይኖርም::
ብርሃኑ ጁላም በመቀላመድና በትርክት ማምታታት የሚያስቆጥረው ድል የለም
** ********* ****
#Freedom!