ሕይወት ፍትሀዊ ናት ብልህ ደስ ይለኝ ነበር...
ሕይወት ፈገግታ ብቻ ናት ብዬ ባወራልህ እመኝ ነበር።
..
ሕይወት ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለችም! አንዳንዴ እሾህና አሜኬላዋ ይበልጣል።
ካለ ምንም ምሕረት፣ ሰማዩ ጥቁር ለብሶ ካልታሰበበት አቅጣጫ የዶፍ መዓት ያወርድብሃል።
ሕይወት ምንጊዜም የራሷን መንገድ ትከተላለች።
በዚህ ሁሉ መከራና ማዕበል ውስጥ ግን ሙሉ በሙሉ በአንተ እጅ ላይ ያለው ብቸኛው ነገር፦
ለነገሮች የምትሰጠው ምላሽ(Reaction) ነው!
ጥግህን ይዘህ አንገትህን ደፍተህ ማልቀስ ትችላለህ።
ተስፋም ቆርጠህ እጅም መስጠት ትችላለህ።
ነገር ግን......
ወገብህን ጠበቅ አርገህ እንዲ ማለት ትችላለህ
❝I WON'T LET THIS BREAK ME❞
ምንም ያህል ቢጎዳህ ምንም ያህል ቢያቆስልህ
ሕይወት እንድታንበረክክህና እንድትሰብር መቼም ቢሆን አትፍቀድላት!
🔥
I WON'T LET THIS BREAK ME 🔥
✍ 𝔠𝔦𝔰𝔠𝔬
🚀
@Young_Hustlers_Lab