"ደስታን አብሣሪ" ፌበን ኢዮብ “DESTAN ABSARI" FEBEN EYOB
#ቅዱስገብርኤል #ደስታንአብሣሪ #መዝሙር #ኦርቶዶክስተዋህዶ
ደስታን አብሣሪ
መልካም ቃል ተናጋሪ
ገብርኤል/ለጠሩህ ፈጥነህ የምትደርስ
ስምህ ከጭንቅ ደዌ 'ሚፈውስ
ከጥፋት ያዳንከኝ መልአክ
የምድንበትን ምሥራች ንገረኝ
በመንገዴ ቅደም ጽድቅን አስተምረኝ
አትለየኝ ከእኔ በመውጣት በመግባቴ
ከክፉ አድነኝ ገብርኤል አባቴ
አዝ . . .
'ባንተ ጥበቃ ነው ለዛሬ የደረስኩት
የመከራን ማዕበል አልፌ የቆምኩት
አንተን ተደግፌ ነገንም አልፈራ
ቀድመሀልና መንገዴን ልትመራ
አዝ ...