❗#ጾመ_ፍልሰታን_ለምን_እንፆማለን?❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉ፆመ ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይጾማል።
#ፍልሰታ :- ፈለገ፣ ተሰደደ (ተገለጠ) ፣ መከፈት፣ መገለጥ፣ ከሚለው የግእዝ ስውር ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሳኤ ያመለክታል።
🔵👉የጾሙ ዋና ምክንያት ሐዋሪያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የጾሙት ፆም ነው።
🔴👉ታሪኩን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን :-
🔵👉እመቤታችን በጥር እሁድ በ21 ቀን አረፋለች ። ሐዋሪያት በአጎበር አድረገው ወደ ጌቴሴማኔ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን ብለው ተነሱ።
🔷👉ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው፣ እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ከዚህ በኃላ መላዕክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረዋታል።
🔴👉በ8 ወሩ በነሐሴ ሐዋርያት አስከሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎት እና በምህላ እሑድ ሥጋዋን ቀብረዋታል። ማስከኞ ተነስታለች። ከመትንሳኤ ወልድ/ እንደ ልጇ ትንሳኤ ያሰኘው ይህ ነው፡፡ በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይም ከ12 ቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ አልነበረም።
🔵👉ቅዱስ ቶማስም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት፣ ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ/ ከሚጓዝበት የደመና ጉዞ ላይም ለመውደቅ ወደደ ተበጠበጠ፣ ቀድሞ የልጇን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ፣ አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሳኤዬን ዕረገቴን አላዩም አንተ አይተሀል ፣ ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው።
🔴👉 ከዚህ በኃላ ቶማስ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት፣
ሞት በጥር በነሐሴ መቃበር ተው ይሄ ነገር አይመስለኝም አላቸው።
🔷👉 ቅዱስ ጴጥሮስም አንተማ ልማድህ ነው ፣ አንተ ብቻ ተጠራጥር አትቀርም አንተ እየተጠረጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው።
🔴👉እርሱም የያዘውን ያውቃልና ፀጥ ብሎ ይሰማቸዋል። ከዚህ በኃላ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፈተው አጣት፣ ደንግጦ ቆመ፤ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሰታለች፣ አረጋለች አላቸው የያዘውን ሰበን ሰጥቶአቸው ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል።
🔶👉 በዚህ ምክንያት በአመቱ ቶማስ ትንሳኤሽን፣ ዕረገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ቅዱሳን ሐዋሪያት ነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ ሱባኤ በጀመሩ በ14 ተኛው ቀን ትኩስ በድን አድርጎ ሰጣቸው ከቀበሯትም በኃላ በነሐሴ 16 ቀን በክብር ተነስታለች።
🔵👉 በዚህ ቀን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ እመቤታችንም ከልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህቺ ጊዜ ትፆማለች።
🔵⏩ እኛም ከእናታችን ከቅድስት ኪዳነ ምህረት በሱባኤውና በፆሙ ስንጠነክር የእሷ አማላጀነት የልጇ የመድሐኔዓለም ቸረነት ከመከራ ስጋና ከመከራ ነፍስ አድኖ ለንሰሀ ጥሪ እንደሚያበቃንና ቅዱስ ስጋውን እና ደሙን ለመቀበል እንደሚፈቅድልን አምነን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባናል ።
🙏🙏🙏