የአጠያየቅ አደብ
~
ጥያቄ የእውቀት ቁልፍ ነው። ስርአት ሲያጣ ዋጋውን ያጣል። ብዙ ሰዎች ግን አጠያየቅ በራሱ ስርአት እንዳለው ይዘነጋሉ። ወይም ደንታ አይሰጣቸውም። በስርአት የመጠየቅ ፍላጎቱ ከሌለን ከነ ጭራሹ ጥያቄው ቢቀርብን መልካም ነው።
1- ሞገደኛ የሆነ፣ መፈታተን ያለበት፣ ሹፈት ያዘለ፣ ... አጠያየቅ ለጭቅጭቅ ስለሚጋብዝ እንዲሁም ራስንም ሌሎችንም ወንጀል ላይ ሊጥል ስለሚችል መራቅ ይገባል።
2- የቀረበን ትምህርት ተመርኩዘን ሌላ ነጥብ ውስጥ የምንጠይቅ ከሆነ በቅድሚያ የቀረበውን ትምህርት በሚገባ እንረዳ። ከፊት ያለውን በቅጡ ሳይረዱ ለሌላ ጥያቄ መቸኮል ደክሞ ማድከም ነው።
3- ጥያቄያችን በሌሎች ቀድሞ ተጠይቆ ተመልሶ ስለሚችል ኮሜንቶችን ወይም የቀደሙ የቅርብ ፖስቶችን ቃኘት ማድረግ ጥሩ ነው። ይሄ ጠያቂውንም ሌሎች ተከታታዮችንም ከማሰልቸት ያተርፋል።
4- ጥያቄያችን የተሳሳተ ጭብጥ እንዳያሲዝ ፍንትው፣ ቅልብጭ አድርገን ሳናዝረከርክ እናቅርብ። ጥያቄው በፅሑፍ የሚቀርብ ከሆነ ለማንበብ የማያስቸግር አድርገን እንፃፍ።
5- ጥያቄያችን ወይም የጥያቄው መልስ ለቦታው የማይመጥን፣ ፊትና የሚያስነሳ፣ በታዳሚውም ላይ ይሁን፣ በመላሹም ላይ ይሁን፣ በትምህርቱ ዘላቂነትም ላይ ይሁን ጥሩ ያልሆነ ውጤት የሚያስከትል ከሆነ ባደባባይ ሳይሆን በግል እንጠይቅ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor