Advanced Freshman


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


🔔ይህ ቻናል በ2017 freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::
📩For comment and ads :- @EEG12bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🥏 የግቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ስትማሩ እልኸኛ ልትሆኑ ይገባል። ለራሳችሁ ስትሉ እንዲሁም በተስፋ ለሚጠብቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ ስትሉ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ መታመን አለባችሁ

#️⃣ከምንም በላይ አዋዋላችሁ ላይ ጥንቃቄ አድርጉ!! ሰው ውሎውን ይመስላል ሲባል ተራ አባባል አይደለም ወደዳድችሁም ጠላችሁም ውሏችሁ ማንነታችሁን ይገነባል::

#️⃣ትክክለኛ መንገድ ላይ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ገጥማችሁ ከሆነ አሁኑኑ ግንኙነቱን አቋርጡት እና ለነጋቸው ዋጋ ከሚሰጡ እና ሳይኖራቸው ልጆቻቸውን ለማስተማር በሚለፉ ቤተሰባቸው ላብ ላይ ከማይቀልዱ ተማሪዎች ጋር ግጠሙ::

🔗በተለይ ሪሚዲያል እና fresh man ላይ በደንብ ትኩረት ሰጥታችሁ ተዘጋጁ ከዛ በኋላ በሚኖራችሁ ቆይታ ዘና ብላችሁ እየተማራችሁ ጎን ለጎን ቢዝነስ እየሰራችሁ ተመርቃችሁ ስትወጡ ቅጥር ሳትጠብቁ ቤተሰብ ላይም ጥገኛ ሳትሆኑ የራሳችሁን ነገር ራሳችሁን ችላችሁ መስራት ትችላላችሁ

ብልህ ሁኑ !!

ብዙ ነገር እየከበደ እየመጣ ነው እሱን ሁላችሁም በየቤታችሁ አስተውላችሁታል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ነገ እዚህ አለም ላይ ከፍ ብላችሁ ለመኖር ከፈለጋችሁ ዝቅ ብላችሁ እራሳችሁ ላይ ምትሰሩበት ሰዐት ላይ መሆናችሁን አስተውሉ

ማድረግ የምትችሉትን በሙሉ አድርጉ ከናንተ ምንም አይቅር የተረፈውን ለፈጣሪ ተዉለት

ከፊት ለሚጠብቃችሁ ፈተና ዝግጅት ያልጀመራችሁ ካሁኑ ጀምሩ በቂ ጊዜ አላችሁ አሁንም አልረፈደም!!


JOIN : @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️

6.1k 0 58 26 175

ዛሬ ለኢትዮጵያውያን የድል ቀን ነው!

አሜሪካም፣ አውሮጳም ድል ባለ ድግስ የነፃነት ቀናቸውን ያከብራሉ። የነፃነት እና የድል ቀን ይለያያል። ኢትዮጵያ የምታከብረው የድል በዓሏን ነው። የድል በዓልን ለማክበር መታደል ያስፈልጋል። መመረጥም ያስፈልጋል።

እንኳን ለ አድዋ የ ድል ቀን አደረሳችሁ።

ሀገራችንን ሰላም ያርግልን🙏

7.2k 0 1 15 129

#Ads

የግቢ ተማሪዎች ናችሁ?

💻ዛሬ በጣም ሊጠቅማችሁ የሚችል ነገር ይዘንላችሁ መተናል

🪃እንደሚታወቀው የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስትሆኑ ገንዘብ በጣም ያስፈልጋቿል::

💴እናም ግዜያቹን በማይጎዳ መልኩ የተለያዩ website ላይ ያሉ ፕሮጀችቶችን እየሰራችሁ ራሳችሁን በገንዘብ ምትችሉበትን መንገድ በነፃ አቅርበንላቿል::

እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመስራት ሚያስፈልጋችሁ ነገሮች:-

📞Smart phone or Pc
🌐Internet

🏑እያንዳንዱን step እኛ guide ስለምናደርጋችሁ  በደምብ የሚሰራ ሰው በጣም ተጠቃሚ ይሆናል::

ተቀላቀሉን
👇

@web_projects10
@web_projects10


ውድ የመጀመርያ አመት እና የሬሜዲያል ተማሪዎች የዩንቨርስቲ ቆይታቹ እንዴት ነው ከ10?
Опрос
  •   9.9
  •   9
  •   8
  •   7
  •   6
  •   5
  •   ከ5 በታች
  •   1
1106 голосов


ፍሬሽማን ተማሪዎች Final exam ተፈተናችሁ? ከየት ግቢ? ዘንድሮ በግብያቹ COC አለ?


የ Senior ተማሪዎች ምክር ጤና ለምትፈልጉ ተማሪዎች

➕ጤና የምትፈልጉ ማለትም Medicine, pharmacy, Anesthesia, Veterinary medicine, Dentist, Optometry እና አሁን ያልጠቀስኳቸውን የጤና Fieldoch መግባት የምትፈልጉ ልጆች 

በጤና ዠርፍ እየተማሩ ያሉ ልጆች እነርሱ ካሳለፋቸው ነገሮች አንፃር በይበልጥ በ 3 ነገሮች ትኩረት እንድታደርጉ ይመክሯቿል


1️⃣ኛ ውጤት መስቀል አለባቹ

#️⃣ውጤት በተለይ ደግሞ ጤና ለመግባት ፍላጎት ያላቹ ልጆች የ First semester ውጤታቹ አሪፍ ሊሆን ይገባል ብቻ ባጭሩ ጤናን ካለ ውጤት ማግኘት ይከብዳል አሁን ላይ ባለው ሁኔታ እንደውም ሁሉም ግቢዎች ከነርስ ጀምሮ እስከ Medicine ድረስ ከፍተኛ ውጤት ይጠይቃሉ ውጤቱም በትንሹ 3.2 በላይ ሊሆን ይችላል Medicine እና ሌሎች የሚፈለጉ ዲፖርትመንቶች ደግሞ የሚጠይቁት ውጤት 3.8 በላይ ሊሆን ይችላል ይሄ ግቢ ከገባቹ በኃላ የምትሰሩት ውጤት ብቻ ነው የ Entrance ውጤታቹ ብዙም ላይረዳቹ ይችላል ቢበዛ ከ 30% ቢይዙት ነው አንዳንድ ግቢዎች ደግሞ እንደውም ላይዙትም ይችላሉ ስለዚህ ጤናን የምትፈልጉ ልጆች ካሁኑ ውጤት መስራት እንዳለባቹ አውቃቹ ትኩረታቹን ትምህርታቹ ላይ ብቻ አድርጉ፤ ይሄን ስንል ደግሞ ተጨናነቁ ማለታችን እንዳልሆነ መቼም ትረዱናላቹ::

🥈ኛ በደንብ አስቡበት

#️⃣ለምን ጤና መግባት ፈለጋቹ ቤተሰብ ስላላቹ ነው ወይስ ጥሩ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብላቹ ?? ይሄ ጉዳይ በደንብ ሊታሰብበት ይገባል ያው እንደምታውቁት ከሌሎቹ ፊልዶች አንፃር የጤና ፊልድ ጥረት የሚፈልጉና ብዙ ረዘም ያለ ጊዜ የሚውስዱ ስለሆኑ በግለትና በስሜት እንድትመርጧቸው አይመከርም ምክንያቱም በኃላ ላይ ፍላጎትና ጥረት ከሌላቹ ማማረራቹ አይቀርም ከባሰባቹ ደግሞ ትምህርቱን ጥሎ መውጣትም አለ::

🥉ኛ ማንንም አትስሙ
 
#️⃣አንዳንድ ለጤና ፍላጎት የሌላቸው እና ውጤት መስራት የማይችሉ ጀለሶቻቹ እነርሱ ጤና መግባት ስለማይችሉ ብቻ እናንተ የምትፈልጉትን ጤና የተለያዩ የወረዱ ሀሳቦችን እያነሱ ፍላጎታቹን ሊያጣጥሉባቹ ይችላል ስለዚህ be Wise 😎 አትስሟቸው።

ይቀጥላል ...

©️Race Tutorial

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


😀በነገራችን ላይ ዛሬ ልደቴ ነው! እስኪ መልካም ምኞታችሁን ግለፁልኝ😅

9.9k 0 4 38 603

🎓 ፍሬሽማን ተማሪዎች ምን ዲፓርትመንት ለምግባት እያሰባቹ እና እያጠናችሁ ነዉ?
Опрос
  •   Medicine ➕
  •   Pharmacy, Anesthesia, Radiology
  •   Law ⚖️
  •   Engineering
  •   Other natural
  •   Other social
467 голосов

15k 0 7 16 84



Репост из: Freshman exam
logical fallacies activities.doc
32.0Кб
Students Exercise Logic & Crit Thinking.pptx
169.1Кб
♻️EXERCISE ON INFORMAL FALLACY

❇️ ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎችን ባንድ ላይ የያዘች አጭር ፋይል ናት ተጠቀሙባት

🌐 Like👍 Share 📱📲

𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 
@freshman_materials ⭐️
@freshman_materials ⭐️


Take a lesson⚠️
ይህ በወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ሲገቡ ስልክ ይዘው የተያዙ ናቸው።

ስልክ ለፈተና አትጠቀሙ እሺ😊

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

12.8k 0 75 24 221

#DebreMarkosUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 28 እና 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-H የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-E የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ ሌሎቻችሁ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


#EthiopianDefenceUniversity

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት አሳውቀዋል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️

13.5k 0 30 18 104

#DebreBerhanUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 6 እና 7/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

https://tinyurl.com/dbu-rcp-2017 ሊንክ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ግቢ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


ሪሚድያል ተማሪዎቻቸውን ጠርተው የተቀበሉ ዩኒቨርሲቲዎች

1. ጂጅጋ ዩንቨርስቲ (ታህሳስ 14 እና 15)
2. ወልድያ ዩንቨርሲቲ( ጥር  19 እና 20 )
3. ሚዛን ቲፒ ዩንቨርሲቲ (ህዳር 11 እና 12 )
4. ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ (ህዳር 26 እና 27)
5. አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 2 )
6. ዲላ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 14 እና 15)
7. ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 7 እና8 )
8. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 7 እና 8)
9. ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 21 እና 22)
10. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 2,3 እና 4)
11. ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ጥር 5,6 እና 7)
12. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
13. ቦረና ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 22 እና 23)
14. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 3 እና 4)
15. አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
16. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  (ታህሳስ 20 እና 21)
17. ወሎ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 3 እና 4)
18. መቱ  ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
19. ራያ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 15 እና 16)
20. መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19 እና 20)
21. አክሱም ዩኒቨርስቲ (15 እና 16)
22. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 22  እና 23)
23. መቅደል አምባ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 13,14 እና 15)
24. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 14 )
25. አርሲ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19 እና 20)
26. ጂንካ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 13  እና 14)
27. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19  እና 20)
28. ወራቤ ዩንቨርስቲ (ጥር 21 እና 22)

ሪሚዲያል ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ግን ያልተቀበሉ ዩንቨርስቲዎች

1. ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ (ጥር 26 እና 27)
2. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ (ጥር 28 እና 29)
3. አምቦ ዩኒቨርስቲ (ጥር 29 እና 30)
4. ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ (ጥር 29 እና 30)
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 29 እና 30 )
6. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 30 እና የካቲት 1)
7. ቦንጋ ዩንቨርስቲ ( የካቲት 1 እና 2)
8. ዴቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ (የካቲት 3 እና 4)
9. እንጅባራ ዩንቨርስቲ (ጥር 26 እና 27)
10. ሰላሌ ዩንቨርስቲ (ጥር 28 እና 29)

#️⃣ ሪሜዲያል ተማሪዎቻቸውን እስከ አሁን ድረስ ያልጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች

1. ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ እና
2. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


ስለ አንዳንድ ዲፓርትመንቶች ማብራሪያ የሰጠንበትን post ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንክ ተጠቀሙ

👾Architecture ⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1322

🖊 Management⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1329

💻 Software engineering⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1334

🔨 Law⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1350

💊Radiology⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1354

👨‍⚕️Medicine⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1361
https://t.me/Advanced_Freshman/1384
https://t.me/Advanced_Freshman/1392

💵Economics⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1367

🎙Journalism⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1370

💻Computer science⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1374

💰Accounting and finance⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1377

ሁሌም ለላቀ ዉጤት

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


#MekelleUniversity

በ2017 ዓ.ም መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥር 30/2017 ዓ.ም እና የካቲት 1/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (አሪድ ካምፓስ) እንዲሁም የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲሓቂ ካምፓስ (ቢዝነስ ካምፓስ) በተገለፁት ቀናት ብቻ ሪፖርት አድርጉ ተብሏል፡፡

ለምዝገባ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️

12k 0 13 1 27

#DambiDolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ስምንት 3×4 የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


በዮኒቨርሲቲ ቆይታችሁ እነዚህ ነገሮች ብታረጉ ጥሩ ነው ❗️

💡....ዲያሪ መፃፍ .....

🎓 የካንፓስ ቆይታ በጣም የሚገርሙ moment ያሉበት ነው ።በቃ 3 or 5 የደስታ ዘመናት ... የሚገራርም ሰው ታያላችሁ ....የሚወዛገብ ፤ የሚወሳሰብ የሚፈላሰፍ ፤ ምንም ዲጭ የማይልበት  ፤ ተንከሲሲስ ፤ በጣም ጅል ፤ አራዳ ነኝ ባይ ገገማ ....ኧረ ምኑ ቅጡ ....በህይወታችን አዳዲስ ነገሮች ይከሰታሉ ። ነገር ግን እንረሳቸዋለን ቶሎ ቶሎ አዳዲስ ነገር ስለሚፈጠሩ ይረሳል ። እናንተ ደግሞ ከፈለጋችሁ መፃፍ ብታረጉት ፤ ወደፊት ፊልም የመስራት ዕቅድ ካላችሁ ሚገራርሙ ገፀባህራያት ታገኛላቹሁ....ብቻ በላይፋቹ የማታገኙት ዕድል ስለሆነ በርትታቹሁ?...አዳዲስ ነገር ሲኖር በወረቀት (ዲያሪ)  "ወይም ስልካቹም ላይ ቢሆን አስፍሩት ..! ትዝታዎቻቹ ናቸው እንዳትረሱት...ሙድ የተያዘባችሁ ሙድ የያዛችሁትን ...የሚያስቅ ፤ የሚያሳዝን፤ የሚያናድድ ብቻ ....ቸክችኩ ቢያንስ ልጆቻችሁ ትሰጧቹሃላቹ እነሱም ካምፓስ ሊገቡ ሲሉ ....በየቀኑ ሳይሆን የሆነ ነገር ሲፈጠር ፃፉት ...አሁን ምንም ላይመስላቹሁ ይችላል ግን አልፎ ስታዩት  የምርም ትደሰታላቹሁ .....

💡አዲስ ቋንቋ መማር ......❗️

📚 ዶርም የምትሰባሰቡት ከየአቅጣጫው ነው ። ብዙ የማታውቁትን የሚያቁ ይሄም አለ❓...  ያምሃል...!  የሚያስብሉ ዕውቀቶች ታገኛላችሁ ። አንዱ ደሞ ቋንቋ ነው ። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያለ ተናጋሪ ያላቸው እንደ ኦሮሚኛ ፣ሲዳመኛ ፣ትግረኛ፣ ሱማሌኛ ቋንቋዎች የሚችሉ ልጆች ዶርም ካገኛችሁ በቀን 5 ቃልም ቢሆን ቀስ እያላችሁ ተማሩ .....የምር ይጠቅማቹሃል ። ቋንቋ መልመድ ጥሩ ነው ። ሁላቹም ጋር አዲስ ቋንቋ ከሌለ ደሞ ጓደኞቻችሁን የምታስታውሱበት አለ ኣ በቃ ....አዲስ የባህርማዶ አንድ ቋንቋ በጋራ ተለማመዱ ...ስፓንሽ ወይ ደሞ ፈረንች ...የተመቻችሁ በጋራ በቀን ትንሽ ነገር አጥኑ ። የ3 or 5 አመት ጓደኞቻችሁን ስትለዮዎቸው ማስታወሻ ይሆናቹሃል ። ፈታ እያላችሁ ጠዋት ላይ 5 ቃላት ምናምን ሸምድዱ የምርም ጓደኝነታችሁ ለማጠንከር ያግዛቹሃል ።

💡መክሊታችሁን ማዳበር ......!

📚 የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተለያዩ መክሊቶች ተሰጥቶታል ። ታዲያ እናንተም የተፈጥሮ ስጦታችሁን በክበብ በመሳተፍ ማሳደግ አለባቹሁ፣ በገገሙ ትምህርት ብቻ ካንሰር ነው  የሚሆንባቹሁ ...ትወና የምትሞክሩ....ግጥም መጣጥፍ የምትሞክሩ ....ስዕል ....ሃይማኖታዊ ነገሮች የምትሞክሩ  ብቻ ግቢ ላይ ብዙ ክበቦች አሉ ...የሴቶች ...የበጎአድራጎት ...የሌለ የለም ....እና ተሳተፉ ማህበር  አለ ...ዕቁብ፣ ዕድር ሁላ አለ (ቀልዴ ነው ...) ....በቃ በዓል ግዜ ደስ ይላል ። የምትወዱት ከኖርማል ትምህርታቹ ላይ የሚደበል ...ዘፈን ከሆነ ...ስፓርት ከሆነ ...ኳስ ከሆነ .....ብቻ የምትወዱትን አንድ ነገር አዳብሯቹሁ ። ተገኙ .....በገገሙ ትምሮ ብቻ አይነፋም ...!


💡 የተለያዮ EVENT እና TOUR  እንዳትቀሩ ...

በግቢ ቆይታ ፍራንክ ባይኖራቹ ራሱ ተበዳድራቹ  ሀገር መጎብኘት አሪፍ ነው ። በቃ ceremony  ሲኖር ....ይሂዱ ባክህ አትበሉ ዳግም የሚገኝ ነገር አይደለም ጦቢያን የምር የምታውቁበት ነው ። ትምህርተ ጋር ካልተጋጨ በየ ግዜው  በአስተባሪዎች ጉዞ ይኖራል ። ስለዚህ.... አትቅሩ ...የመፅሀፍ ምረቃዎች ....አነቃቂ ንግሮች ...ትያአታራዊ ዝግጅቶች ይደረጋሉ .....አትቅሩ ....ታዋቂ ሰዎች በየግቢ እየመጡ በተለይ ወጣቶች የህይወት ልምዶቻቸውን ስለሚያጋሩ .....የምታደንቋቸው ሰዎች በየትኛው መንገድ ነው የተሳካላቸው ....የሚለው የህይወት ጉዞን ትማሩበታላቹሁ ...የፈታ ኢቨንቶችም አሉ በቃ ....ፈተና ሲያልቅ ምናምን ከች የሚሉ እና ሳትንዘላዘሉ ተሳተፉ ....እነ ሮፍናን ደግሰው መቼስ አይቀርም .....እነ እሸቱ መለሰ እየቀለዱ መቅረት ይከብዳል ....


⏰️ አዳዲስ ነገሮች ሞክሩ ...አትፍሩ

📚 አዳዲስ ነገሮች የማድረግ ዕድሉ ስለሚኖረን ምንአቧቱ በእናት ሆድ አይለመድ አትፍሩ ሞክሩ ....ታዲያ ሱስ ምናምን ሳይሆን አሪፍ የሚባሉ ነገሮች የፍቅር ህይወትም ቢሆን ትምህርትን በማይነካ መልኩ ቢደረግ አይከፋም (ታዲያ ለሴሚስተር የሚቆይ ሳይሆን የምር መሆኑኑን ካመናችሁ ..) ....በግ ተራም ቢሆን አንዳንዴ መሄዱ ለክፉ አይሰጥም (አመራችሁ ዴ ቀልዴ ነው..)  .....ሀገራቹ ሄዳቹሁ ለማውራትም ኮ መሞከሩ አይከፋም ።ግን ብዙ አትንዘላዘሉ ...ቸክሉ ...በቃ የሚያስደስታችሁን አዲስ ነገር ሞክሩ .....ብዙዎች ካንፓስ ሃይማኖተኛ ያረጋቸዋል አንዳንዶች ደሞ ...."ፈላስፈ አንዳነዶች ....ዘልዛላም ይሆናል ....አንዳንዴ ሳታስቡት ሃርድ ውስጥ ትገቡ ይሆናል ....ታዲያ ያን ግዜ አትጨናነቁ ...Normal ነው ። በተረፈ መልካም ካንፓስ!

💬በመጨረሻም ካንፓስ ላይ ቆይታቹሁ ልትደሰቱበት የሚችሉበትን የማትፀፀቱበትን ነገር ብቻ ከውኑ ። በቃ ያማረ የግቢ ቆይታ እንዲሆንላቹ ምኞቴ ነው ። ጥሩ ጥሩ ነገሮች ሊያውም የማይደገሙ ሲያጋጥማቹሁ አትለፉ እርግጥ ዋናው ጉዳያቹሁ ትምህርት ቢሆንም ...መደሰቱ መሳተፉ አይከፋም ። አይዞን በቆንጆ ሁኔታ ይታለፋል ።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️

12.5k 0 106 21 134

#BongaUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት የካትቲ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ስድስት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➭ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

Показано 20 последних публикаций.