🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
ቁ/278
ሐሙስ 6/9/1446 ዓ.ሂ
🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽
🔗
https://tinyurl.com/rr6ydwve▪️1/ ኒያ አድርጎ ቁርኣንን ቀርቶ አጅሩን ለሞተ ሰው ይሁን ማለት በሸሪዓ እንዴት ይታያል?
▪️2/ ከቤተሰብ ጋር ተሰባስበን ረመዷን ላይ ቁርኣን በተራ እንቀራለን በዚህም በቀን አንድ ጁዝ በመቅራት አንዴ እናኸትማለን ይህ እንዴት ይታያል? የተሻለ እውቀት ያላቸው እርማት ያደርጋሉ አጅነቢይ የለብንም ይህ እንዴት ይታያል? ወይስ በግል እየቀሩ ማኽተሙ ይሻላል?
▪️3/ ኢስቲንሻቅ ሲያደርግ ረስቶት ወደ ውስጥ ቢገባ ፆሙ ይበላሻልን?
▪️4/ ቅርብ ያለው መስጂድ ሙአዚን አንዳንዴ ወቅቱን አሳልፎ ነው አዛን የሚለው አንዳንዴ ደግሞ ቀደም ብሎ ነው አዛን የሚለው። ራቅ ያለው መስጂድ ሙአዚን በትክክል ይላል ግን ብዙ ጊዜ አልሰማውም እና በስልኬ አፕሊኬሽን አዉርጄ ስጠቀም ራቅ ካለው ከትክክለኛው ሙአዚን ጋር እኩል ይላል እና በስልኬ መጠቀም እችላለሁ ወይ?
በተለይ ከአፍጥርና ከስሁር ጋር ጥርጣሬ ፈጠረብኝ።
▪️5/ በረመዳን ወር ሙስሊም ያልሆኑ ጎረቤቶች በአጋጣሚ እቤት መተው ውሃ ቢጠጡ ምግብም ቢመገቡ ለነሱ እሄን መፍቀድ እንዴት ይታያል?
እንዲሁም በተመሳሳይ ጥያቄ
በረመዳን ወር ጧት ጧት አንባሻ ዳቦ እንሸጣለን የምንሸጠው ግን ለህፃናት ነው አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም ይገዙናል ለነሱ መሸጥ እንዴት ይታያል?
▪️6/ የሀይድ ደም የማየው በወር ሁለት ጊዜ ነው ባቆመ በ15 ቀን ድጋሚ ይመጣል በጣም ብዙ አመት ሆነኝ ህክምናም አድርጌለሁ ሊስተካከልልኝ አልቻለም ከረመዷን ውስጥ 15 ቀኑን ብቻ ነው የምፆመው በየአመቱ 15 ቀኑ ቀዷ ነው ምን ላድርግ? ዱአም አድርጉልኝ አላህ እንዲያስተካክልልኝ ለሶላቴም ይሁን ለሁሉም ነገር ተቸግርያለሁ።
▪️7/ ሀይዴ ረመዷን ሳይገባ ነው የመጣው ከ10 ቀን በላይ ሆነኝ አላቆመልኝም በቀን አንድ ጊዜ ትንሽ አለ ከ7 ቀን በኋላ ሀይድ አይደለም ታጥባችሁ ውዱእ እያደረጋችሁ ስገዱ ሲባል ሰምቼ በዛ መሰረት እየፆምኩም እየሰገድኩ ነው በዚሁ ልቀጥል? ብታብራሩልኝ።
🔹🔸🔹🔸🔹🔸
💥 በተጨማሪም የተለያዩ ፔጆቻችንን ለመቀላቀልና ዌብሳይታችንን ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
🌐
https://zadalmead.com/✔️
https://telegram.me/ahmedadem✔️
https://facebook.com/yenegew✔️
https://youtube.com/@Zadul-Mead✔️
https://x.com/zadul__mead✔️
https://instagram.com/zadulmeadአላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
🔅وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197