# ለጥንቃቄ ‼️‼️
“ የኢትዮ ቴሌኮም ነጻ ዳታ ሽልማት ለሁሉም አሮጌ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ” በሚል ሰሞኑን ነጻ ሜጋ ባይት ለማግኘት “ ሊንክ ጠቅ ያድርጉ ” የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ወደተለያዩ ግለሰቦች እየተላከና እየተዘዋወረ ነው፡፡
አንዳንድ ሊንኩን የከፈቱ ሰዎችም፣ “ ስንከፍተው መረጃዎት እየተበረበረ ነው ይላል፡፡ ጉድ ተሰርተናል ” ሲሉ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ብዙዎች ደግሞ ይህን ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮም ያውቀዋል ? በማለት እየጠየቁ ነው፡፡
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የሚዘዋወረውን መልዕክት ተቋሙ ያውቀዋል? ትክክለኛስ ነው? ሲል ኢትዮ ቴሌኮምን ጠይቋል፡፡
የተቋሙ ቺፍ ኮሚዩኒኬሽን ኢፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ምን ምላሽ ሰጡ ?
“ የኛ ቲምም ቼክ አድርጎታል፡፡ Phishing የሚሉት የማጭበርበር መልዕክቶችን የሚልኩ ናቸው፡፡
ታማኝ ከሆኑ ካምፓኒዎች የሚላኩ መልዕክቶችን በማስመስልና የሰዎችን መረጃ የሚወስዱ Phishing ብለን የምንጠራቸው የሳይበር ጥቃት መንገዶች ናቸው ብለዎል፡፡
መረጃው ያገኘነው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው።