ለ2017 ተመራቂ ተማሪዎች "Dereja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሥልጠና እየተሰጠ ነው
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ማበልጸጊያ ማዕከል ከደረጃ ዶት ኮም /Dereja.com/ እና ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው የ2017 ተመራቂ ተማሪዎች ከጥቅምት 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚቆይ የ "Dereja Academy Accelerator Program (DAAP)" ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የሥልጠናው የመጀመሪያ ክፍል ሰዋዊ ክሂሎት (Soft Skill) ማለትም ‹‹Self Discover››፣ ‹‹Building Self-image››፣ ‹‹Communication Skill›› እና ሌሎችም ርዕስ ጉዳዮች ዙሪያ ለስምንት ሳምንታት የሚሰጥ ነው፡፡ የሁለተኛው ክፍል ሥልጠና ድግሞ ሙያዊ ክሂሎት (Professional Skill) ላይ ያተኮረ ሲሆን በዚህም ‹‹Customer Service››፣ ‹‹Sales and Marketing››፣ ‹‹Finance and Accounting›› እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች የሚዳሰሱበትና ለአንድ ወር የሚቆይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ሥልጠናው ተማሪዎች በትምህርት ከሚያገኙት ዕውቀት በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት ቀጣሪ ድርጅቶች ከተቀጣሪዎች የሚፈልጉትን ዕውቀትና ከሂሎት የሚያስጨብጥና በሥራ ዓለም ተወዳዳሪና አሸናፊ እንዲሆኑ የሚስችሉ ግንዛቤዎችን የሚፈጥር እንደሆነም ታውቋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCAD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት