ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አዲስ ለተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ የመልካም ምኞት መግለጫ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀዳሚ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን ገናና ስም ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተርታም ይመደባል ፡፡ለዚህም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የነበረው አመራር ጥንካሬ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበራችሁ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ልቆ እንዲወጣ፣ ሰላሙ የተጠበቀና ለሃገሪቱ የሰላም አምባሳደር ምልክት መሆን እንዲችል ለተማሪዎችም እንደመፈክሩ የብሩህ ተስፋ ማዕከል መሆኑ እንዲመሰከርለት ስላደረጋችሁ፣ የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች ህብረት በሙሉ አቅማችሁ በመደገፍ ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
አዲስ ለተመደባችሁ ለዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ይህን ግዙፍ ሃገራዊ ተቋም ለመምራት ዕድል ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡
እንደተማሪዎች ህብረት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አብረናችሁ ለመስራት እና የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ተሰናድተናል። በተማሪዎች እና በአመራሩ መሀከል ድልድይ በመሆን ፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን በማስጠበቅ ፣ የተቋሙን ሰላም በማስቀጠል በበለጠ ለመትጋት እንደተሰናዳን መግለጽ እንሻለን።
በተለይም በአሁኑ ሰዓት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስገዝነት ለሚያደርገው ሽግግር የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚሻ የምንገነዘበው ነው። የትምህርት ዘርፉ ሪፎርምም ይኼንን ተልዕኮ ከግንዛቤ ያስገባ መሆኑን እናምናለን። የተማሪዎች ህብረትም የዩኒቨርስቲው ማህረበሰብ አስኳል እንደመሆኑ መጠን ከትላንት በተሻለ ትጋት ፤ ከአምናው በበለጠ ጥረት መስራት እንደሚገባንና የሚጠበቅብንን ለመከወን ፣ የተሰጠንን ተልዕኮ ለመተግበር እና ከተማሪዎች የሚነሱ ሀሳቦችን ለማስፈፀም ተግተን እንሰራለን፡፡
መልካም የስራ ዘመን ይሁንልን !
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት