100 ቢሊየን ብድር ለዲያስፖራ
================================
አሁን ባለው ሁኔታ ሃዋላ ወደ መደበኛው መስመር እየገባ ይመስላል። ያዝልቀው ነው የሚባለው። በአልን ምክንያት በማድረግ ባንኮቹ እያቀረቡ ባለው ቦነስ ምክንያት የመደበኛው መላኪያ ከጥቁሩ ገበያ ትርጉም ባለው ሁኔታ ልቋል። ይሁን እንጂ የባንኮቹ የመሸጫ ዋጋ ከመግዣው ስላነሰ ሁኔታዎች ካልተለወጡ ተረጋግቶ በዚህ የሚቀጥል አይመስልም።
ዙሩን እያከረረው ያለው ብሔራዊ ባንክ አሁን ደሞ ሌላ ማበረታቻ ይዞ መጥቷል። ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መደበኛውን የሃዋላ መስመር ለሚከተሉ የውጭ ነዋሪዎች በ31ዱ ባንኮች ለኢንቨስትመንት እና መኖሪያ ቤት መግዣ የሚውል 100ቢሊየን ብር ብድር አመቻችቻለሁ ብሏል።
ምን ይፈይዳል?
=================
- መንግስት ከዚህ ብድር ምናልባትም ወደ 1 ቢሊየን ዶላር ለመሰብሰብ ያስችለዋል።
- መመንዘሪያው ከተቀራረበለት ላኪው መደበኛውን መስመር። መጠቀሙ አይቀርም
- ዲያስፖራ ሁሌ ህልሙ ቤት መግዛት ነው። በዚህ ፈንድ አደጋ ላይ ያለው የሪል እስቴት ገበያ ይነቃቃል ይሆናል።
- በውጭ ለሚኖሩ ኢትየዬጵያዊያን በሃገራቸው ላይ የኢንቨስትመት እድል ይፈጥራል። የካፒታል ገበያውም ላይ ኢንቨስት የማድረግ እድል ይከፍታል።
ምን ችግር ሊያስከትል ይችላል?
=====================
- ብሄራዊ ባንክ በብድር ጣርያ አስሮ ያወረደውን የዋጋ ንረት የዚህ ብር ወደ ገበያ መግባት የዋጋ ንረትን መልሶ ሊያመጣበት ይችላል።
-የመኖርያ ቤት ዋጋን ሊያንር ይችላል።
የዕድሉ ተጠቃሚ እንዴት መሆን ይቻላል?
================================
- ብሔራዊ ባንክ ብሩን ለባንኮቹ በምን መልክ እንደሚደለድለው አላስታወቀም። ይሁን እንጂ ብሄራዊ ባንኩ በውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችን: ካላችሁበት ሆናችሁ በዲጂታል ዘዴ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈትና ማንቀሳቀስ፣ የምትችሉበት ፕላትፎርም አዘጋጅቶላችሁዋል። (
unite.et) አፑን በማውረድ የፈለጋችሁበት ባንክ የውጭ ምንዛሪ ወይም የብር አካውንት መክፈት ትችላላችሁ ሞክሩት።
Bet Addis 🇪🇹 Properties
https://t.me/BetAddisHome