ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Send a gift, to show appreciation for ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቴሌግራም ቻናል!


“ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ። ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ። አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀፀላ መንግሥቱ። አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፡ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።”

ትርጉም፦
ድንግል ሆይ የስሙ ምልክት እና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ ከሚያበራ ወርቅ ይልቅ እንደ እንቁ የጠራ ንፅህና ያለሽ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጂለታለሽ እርሱም ላንቺ ይሰግዳል

(ማኅሌተ ጽጌ)


“አንተ ለሕይወትህ ካቀድከው የተሻለ እግዚአብሔር እንደሚያቅድልህ ታውቃለህ? አንተ ስለአንተ ልትሳሳት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር ግን አይሳሳትም። አንተ ስለሕይወትህ ስታቅድ ልትሳሳት ወይም ያነሰውን ልታስብ ትችላለህ፤ እግዚአብሔር ግን ለአንተ የሚገባውንና የተሻለውን በፍጹም ትክክለኛነት ያዘጋጅልሃል።”

ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ


እግዚአብሔር ይመስገን ከ25 የቻናላችን ቤተሰቦች 86,845 ብር ደርሶልን ያሰብነው ተሳክቶልናል።

ልብሰ ተክህኖውን ገዝተን ለቤተክርስቲያኑ ስናስረክብ በፎቶ የተደገፈ መረጃ እና በትክክል ስለመድረሱ በቻናላችን ስም ደብዳቤ የምንቀበል ይሆናል።


እግዚአብሔር እየረዳን ከ23 የቻናላችን ቤተሰቦች 80,500 ደርሰናል 5,000 ብር ይቀረናል። ይህቺን ቀሪዋን ሙሉልኝና ልጨርስ!




#ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ።

ቅድስት አርሴማ በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም የምትኖር፣ በውበቷ የታወቀች ድንግል ነበረች። ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ሥዕሏን ሲያይ ልቡ ተማረከና ሚስት ሊያደርጋት ፈለገ፤ አሽከሮቹንም ሊያመጧት ላከ። እርሷና እመምኔቷ አጋታ ከሌሎች ደናግል ጋር ድንግልናቸውን ለመጠበቅ እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ፤ ከዚያም በድብቅ ሸሽተው ወደ አርማንያ ደረሱ።

ሆኖም ዲዮቅልጥያኖስ እዚያ እንዳሉ ሰምቶ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ መልእክት ላከ። ደናግሉ ይህን ሲሰሙ ወደ ሌላ ቦታ ተሰወሩ፤ ነገር ግን ተወነጀሉ፤ አርሴማም እምቢ ብትልም እየተጎተተች ወደ ንጉሡ ቀረበች። እመምኔቷ አጋታ ደግሞ "ሰማያዊ ሙሽራሽን ክርስቶስን አትተዪ" ብላ አጸናቻት።

ንጉሡ ሊይዛት ሲጠጋ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና መሬት ላይ ጣለችው። በጦርነት የታወቀ ጀግና ሆኖ ሳለ በአንዲት ወጣት ሴት መሸነፉ አሳፈረው። በንዴትም አርሴማን በሰይፍ አስቆረጣት፤ ከዚያም አጋታንና ደናግሉን ሁሉ እንዲሁም አብረዋቸው የመጡትን ሁሉ ገደለ። ሁሉም የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጁ።

ከዚያ በኋላ ንጉሡ በክፉ መንፈስ ተያዘ፤ መልኩም እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ መጥቶ ጸለየለትና ዳነ፤ እርሱም በክርስቶስ አመነ። የሰማዕታቱ አፅም ተሰብስቦ በተከበረ ቦታ ተቀበረ፤ ቤተ ክርስቲያንም ተሠራላቸው፤ በዚያም ብዙ ተአምራት ተገለጡ።

የሰማዕት ቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ከእኛ ጋር ይኹን!


እግዚአብሔር እየረዳን ከ23 የቻናላችን ቤተሰቦች 80,500 ደርሰናል 5,000 ብር ይቀረናል።


እግዚአብሔር እየረዳን ከ22 የቻናላችን ቤተሰቦች 79,850 ደርሰናል 5,650 ብር ይቀረናል።




21,300 ብር ይቀረኛል።


#ወርኃ_ጽጌ
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!


«ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት። ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡

የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በትእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ (በእንባ) ምላቸው።

ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡

ከመለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው። ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"

(ማር ይስሐቅ ሶርያዊ)


ሰው ኾኖ የማይበድል የለም፡፡ ይኽም በሌሎች ሰዎች ላይ እንዳንፈርድባቸው ይልቁንም ድካማቸውን እንድንረዳላቸው እና እንድንሸከማቸው ይረዳናል፡፡

አንድን ሕንጻ ለመገንባት የሚያገለግሉ ድንጋዮች አንድ ዓይነት አገልግሎት የላቸውም፡፡ አንዱ ለመሠረት ይኾናል፤ ሌላው ለማዕዘን ይኾናል፡፡ ለማዕዘን የሚኾነው ድንጋይ ለመሠረት አይኾንም፤ ለመሠረት የሚኾነውም ለማዕዘን አይኾንም፡፡ ይኽ በቤተ ክርስቲያን ዘንድም የሚሠራ ነው፡፡ በሰውነታችንም እንደዚኹ ነው፡፡ አንገት ጭንቅላትን ይሸከማል፤ እግርም ከእግር በላይ ያለውን የሰውነት አካል ይሸከማል፡፡ ኹሉም ብልቶቻችንም በየራሳቸው የቆሙ አይደሉም፤ የእያንዳንዱ ህልውና በሌላው የመሸከም ዓቅም የተመሠረተ ነው እንጂ፡፡ ሙሉ ሰውነትንም የሚገነቡት ለየብቻቸው ተነጣጥለው ሳይኾን አንድ ላይ ሲሸካከሙ ነው፡፡ ክርስቲያንም ወንድሙን እንዲኽ ሊሸከመው ይገባል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም” ያለን ስለዚኹ ነውና /ገላ.፮፡፪/፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)




ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

(ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)




እግዚአብሔር ሰዎችን ኹሉ ሲፈጥራቸው በመንፈሳዊ ማንነታቸው እኩል አድርጎ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ እያንዳንዱ ሰው በጎም ኾነ ክፉ ግብር ለመሥራት እኩል ዝንባሌ አለው፡፡ እግዚአብሔርን ለመታዘዝም ኾነ ላለመታዘዝ እኩል የመምረጥ ዕድል አለው፡፡ ከዚህ ውጪ በኾነ ነገር ግን ሰው ኹሉ እኩል አይደለም፡፡ አንዳንዱ እጅግ አስተዋይ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደከም ያለ ነው፡፡ አንዳንዱ በሰውነቱ ብርቱና ጤናማ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደካማና ሕመም የሚበዛበት ነው፡፡ አንዳንዱ ሰው መልከ መልካምና ማራኪ ነው፤ ሌላው ደግሞ አይደለም፡፡

ይህ ኹሉ ቢኾንም ግን በኾነ ነገር ስጦታው ያለው ሰው ስጦታው የሌለውን ሌላውን ሰው ሊንቀው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታን የሰጠን አንዳችን አንዳችንን እንድንጠቅም ነውና፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ከሌላው ወንድማችን የምንፈልገው ጥቅም እንዲኖር ያደረገው በመካከላችን መጠላላትና መለያየት እንዳይኖር ነው፤ እንድንፋቀርና አንድ እንድንኾን አስቦ ነውና፡፡

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና ዐዋቂ፥ ብርቱም ቢኾን በዚህ ቅር አይበልህ፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ከወንድምህ አስተዋይነትና ዐዋቂነት ብርታትም ትጠቀማለህና፡፡ በዚህ ብቻ ሳታቆምም ራስህን፡- “ስጦታዬ ምንድን ነው? ወንድሜን እኅቴን በምን ልጠቅም እችላለሁ?” ብለህ ጠይቅ፡፡ ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ፥ እንደ መለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን፥ በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ሌላውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)




ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

(ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ)

Показано 20 последних публикаций.