Christian νοῦς


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Telegram


1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥16
​እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።"
Proud to be ORTHODOX
https://t.me/christisnapologetics 👉 chat
https://t.me/+7TULVd08sQk4OTJk 👉study

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


ዛሬ🙈


በኀጢአታችሁ እንደምትሞቱ ነግሬአችኋለሁ፤ እኔ እርሱ ነኝ ስላችሁ እኔ እርሱ እንደ ሆንሁ ካላመናችሁ፣ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁና።”
ዮሐንስ 8፥24

በዚህ ክፍል ውስጥ ትርጕሞቻችን ሙሉ ለሙሉ ያልተረጐሙት ሐሳብ አለ፤ በተሻለ መንገድ እንዲህ መግለጽ እንችላለን፤ "እኔ እንደሆንሁ ካላመናችሁ፣ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁ።" ብዙ ጊዜ ዮሐንስ እንደሚያደርገው ቀላል ቃላቶችን ወስዶ ትልቅ ትርጕም ይሰጣቸዋል፤ በአዲስ መንገድ ኢየሱስን እንድናይ ያደርገናል። ኢየሱስ ራሱን እንዲህ ብሎ ይገልጻል "አኔ ነኝ" (ዘፀአት 3፥13-14 በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ያሉትን የኢየሱስን ሰባት የ"እኔ ነኝ" መግለጫዎችን ይመልከቱ)። እግዚአብሔር እጅግ ወድዶን በመካከላችን አማኑኤል (እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ) ሆኖ እንዴት ሊያድር ቻለ (ማቴዎስ 1፥23)? የእግዚአብሔርን የፍቅር ጥልቀት ሙሉ ለሙሉ ልንረዳው አንችልም፤ ነገር ግን ልናምን፣ ራሳችንን ልናዋርድ፣ ልንደሰትና "እኔ ነኝ" ላለው፣ ለጌታችን ክብርን ለማምጣት ልንኖር እንችላለን (ፊልጵስዩስ 2፥6-11)።
«ጌታችን፦ 'እኔ እንደ ሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ' በማለት የተናገረው ቃል፥ እሱ ከአብ ጋር አንድ ባሕርይ ያለው ፈጣሪ መሆኑን ያሳያል። በእሱ መለኮት የማያምን ሰው ከኃጢአቱ ሊጸዳ አይችልም፤ ምክንያቱም ሕይወት የሚገኘው ከፈጣሪ እንጂ ከፍጡር አይደለም።» (ተመልከት፦ St. Athanasius, Four Discourses Against the Arians)

ቅዱስ አትናቴዎስ ክርስቶስ ፍጡር ነው የሚለውን የአርዮስን ክህደት ሲመክት፣ የክርስቶስ «እኔ ነኝ» ማለት ሰብአዊ ወይም ፍጡራዊ ሳይሆን የባሕርይ አምላክነት መግለጫ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል።
«ቃሉ ሥጋ ሆነ ሲባል መለኮቱ ተለወጠ ማለት አይደለም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 'እኔ ነኝ' ባለ ጊዜ፥ የሚታየው ሥጋ ከማይታየው መለኮት ጋር ያለ መለየት፣ ያለ መለወጥ፣ ያለ መምታታት እና ያለ መለያየት በአንድ አካልና በአንድ ተዋሕዶ የጸና መሆኑን እንረዳለን።» (ተመልከት፦ St. Cyril of Alexandria, Commentary on the Gospel of John)

የእኛ የታመነ አባት ቅዱስ ቄርሎስ የተዋሕዶን ምሥጢር በዚህ ቃል ላይ ያጸናል። መለኮትና ትስብእት በአንድ በመዋሐዳቸው የክርስቶስ ቃል የፈጣሪ ቃል ነው።

መልካም ውሎ🤗


እንኳን አደረሳቹ




ዛሬ ጌታ ከፈቀደ ኦሪት ዘኁልቊ እንጀምራለን


እርሱም መልሶ፣ “እናቴና ወንድሞቼስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው” አላቸው።
ሉቃስ 8፥21

ኢየሱስ የመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቱን ያስተማረውን ግልጽና ቀላል እውነት እወድደዋለው። እንደ ኢየሱስ ቤተ ሰብ አባላት ለመታወቅ ትፈልጋላችሁ? የአባቱን ቃል ታዘዙ፤ የአባቱን ፈቃድ ኑሩ! ይህን ስታደርጉ ኢየሱስ በደስታ እንደ ቤተ ሰቡ ይቀበላችኋል፤ ሌሎችም እንዲከተሏችሁ ምሳሌ ያደርጋችኋል!

መልካም ቀን

https://kedusbible.com


Репост из: 𝓷𝓪𝓻𝓭𝓸𝓼 🍫


በዚህ በምናከናውነው የቸርነት ሥራ አንዳች ነቀፋ እንዳይገኝብን እንጠነቀቃለን። ምክንያቱም ዐላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን፣ በሰውም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው።
2 ቆሮንቶስ 8፥20-21

ርዳታ የሚያስፈልጋቸው በተለይም በክርስትና ቤተሰብ ውስጥ ያሉትን ልንረዳና ልናግዝ ያስፈልጋል። ቸርነት የእግዚአብሔር የፍቅር ስጦታ ምን ያህል ልባችንን እንደ ነካ ማሳያ ነው። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ይህን የሚመሩ ሰዎች የሐዋርያው ጳውሎስን ምሳሌነትና ጥሪን በጥንቃቄ መከተል አለባቸው። መንፈሳዊ መሪዎች ሌሎችን በኢየሱስ ስም ለመባረክ በእግዚአብሔር ልጆች የሚሰበሰብን ገንዘብ የሚይዙበት መንገድ እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት። በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን በሰውም ፊት ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ መሸከም ያለባቸውን ሸክም ሊሸከሙ ይገባል።

መልካም ቀን🥰

https://kedusbible.com


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ሰዎች፣ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሽኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፣ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
ኢሳይያስ 8፥19

በምንኖርበት ዘመን ብዙ ሰዎች ብዙ የአፈ ታሪክ እምነቶችንና መንፈሳዊነትን በመደባለቅ የራሳቸውን ትንሽ ኢየሱስ በመክተት የውሸት ክርስትናን ሠርተዋል። ብዙ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና መልእክት ግልጽና ቀጥተኛ እንደ ሆነ አያውቁም። ሁሉን ቻዩ ያህዌ ብቻ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ብቸኛ እውነተኛውንና ሕያውን እግዚአብሔር ብቻ ማምለክ አለብን (2 ነገሥት 19፥19፤ ነህምያ 9፥6፤ ማቴዎስ 4፥10)። ሊታመን የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። ሌሎች መንፈሳዊ ኀይሎች አሉ። ነገር ግን እነዚህ ኀይሎች ወደ ውድቀት፣ ሞትና ጥፋት ያመራሉ። ኢየሱስ፣ በሥጋ የተገለጠው አምላክ (ዮሐንስ 1፥14-18፤ ዕብራውያን 1፥1-3)፣ በመስቀል ላይ ሁሉንም ክፉ ኀይሎች አሸንፏል (ቈላስይስ 2፥13-15)። በርሱ ሕይወትን ስለምናገኝ እግዚአብሔርን፣ ያህዌን፣ ታላቁ የእስራኤል "እኔ፣ እኔ ነኝ"ን፣ ሁሉን ቻዩን አምላክ እንፈልጋለን። ሌሎቹ ሁሉ ውሸቶች ናቸው። ከአምላካችን ብቻ ምሪትን ልንፈልግ ይገባል!

https://kedusbible.com




እንኳን አደረሳቹ ወንዶች አላቹ ሙልሙል ጋግሬላቹ ነበር🙄


የሉቃስ ወንጌል Luke 9
28፤ከዚህም፡ቃል፡በዃላ፡ስምንት፡ቀን፡ያኽል፡ቈይቶ፡ጴጥሮስንና፡ዮሐንስን፡ያዕቆብንም፡ይዞ፡ሊጸልይ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ።
29፤ሲጸልይምየፊቱመልክተለወጠ፤ልብሱም፡ተብለጭልጮ፡ነጭ፡ኾነ።
30፤እንሆም፥ኹለት፡ሰዎች፡እነርሱም፡ሙሴና፡ኤልያስ፡ከርሱ፡ጋራ፡ይነጋገሩ፡ነበር፤
31፤በክብርም፡ታይተው፡በኢየሩሳሌም፡ሊፈጽም፡ስላለው፡ስለ፡መውጣቱ፡ይናገሩ፡ነበር።
32፤ነገር፡ግን፥ጴጥሮስንና፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩት፡እንቅልፍ፡ከበደባቸው፤ነቅተው፡ግን፡ክብሩንና፡ከርሱ፡
ጋራ፡ቆመው፡የነበሩትን፡ኹለት፡ሰዎች፡አዩ።
33፤ከርሱም፡ሲለ፟ዩ፥ጴጥሮስ፡ኢየሱስን፦አቤቱ፥በዚህ፡መኾን፡ለእኛ፡መልካም፡ነውና፥አንድ፡ለአንተ፡
አንድም፡ለሙሴ፡አንድም፡ለኤልያስ፡ሦስት፡ዳሶች፡እንሥራ፡አለው፤የሚለውንም፡አያውቅም፡ነበር።
34፤ይህንም፡ሲናገር፡ደመና፡መጣና፡ጋረዳቸው፤ወደ፡ደመናውም፡ሲገቡ፡ሳሉ፡ፈሩ።
35፤ከደመናውም፦የመረጥኹት፡ልጄ፡ይህ፡ነው፥ርሱን፡ስሙት፡የሚል፡ድምፅ፡መጣ።
36፤ድምፁም፡ከመጣ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ብቻውን፡ኾኖ፡ተገኘ።እነርሱም፡ዝም፡አሉ፥ካዩትም፡ነገር፡በዚያ፡ወራት፡ምንም፡ለማንም፡አላወሩም።


የዚ ቤት ሰው የት እየገባነው 918 የገባው🙄


​​ቡሄ ምን ማለት ነዉ ?
ደብረ ታቦር ማለትስ
?

በምዕምዕናን ዘንድ ቡሄ ተብሎም ይታወቃል። ቡሄ ማለት ብርሃኑ የደመቀ የጎላ ማለት ነው ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር ጌታችንን ብርሃነ መለኮት ጋር መጋለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ ነው።

ደብረ ታቦር ማለት የታቦር ታራራ ማለት ነው ተራራው ከገሊላ ባህር በስተምሥራቃዊ በደቡብ በኩል ይገኛል ፤ መሳ 4-6 14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል

ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱ በጠየቀችው ጊዜ አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎች ኤልያስ ነው ሌሎችም ሙሴ ወይም ከነብያት አንዱ ነው ብለውት ነብር

እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጰጥሮስ   አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ  ብሎ መልሶለታል ይህ በሆነ በስድስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሦስቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ ብዋላ ብርሀነ መለኮቱን ገለጣቸው ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሄረ ሕያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ብርሃንን አሳየኝ ብሎት  ነብር (ዘጸ 33፦17-23)

ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ  ጰጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያወ እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነብያት አንዱ አለመሆኑና የዘለዓለም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተማሯችዋል።(ማቴ17:2)

        መልካም የቡሄ በዓል 
    እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ❤


ለእኔ፣ መኖር ክርስቶስ ነው፤ ሞትም ማትረፍ ነው።
ፊልጵስዩስ 1፥21

እውነቱ ቀላል በሆነው ልክ ጣፋጭ ነው፤ ኢየሱስ ሕይወታችን ከሆነ፣ ሕይወታችን ማብቂያ የለውም። ሞት ሕይወትን ከእኛ አይነጥቀንም። ነገር ግን ወደ ኢየሱስ መገኘት ይመራናል።

መልካም ውሎ🤗
https://kedusbible.com


ዛሬ እናነባለን ዘሌዋውያንን እንጨርሳለን😉


ምናልባትም፣ “ይህን ሀብት ያፈራሁት በጕልበቴና በእጄ ብርታት ነው” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል። ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለ ሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ዐስበው።
ዘዳግም 8፥17-18

የእኛ የሆነ ግን ያልተሰጠን ምን አለ? ምንም! በእግዚአብሔር ቸርነት፣ ባልተጠበቀ ባርኮት፣ ትምህርት በሚሰጥ ፈተና፣ በመግቦታዊ ዕድል ወይም በጤና መልኩ ያገኘነው ነው። በፍርድ ዙፋን ፊት ስንሆን፣ ጸጋ ለመቀበል መሠረት አድርገን የምናቀርበው ምክንያት ምንድን ነው? እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሰጠንን ከፍቅሩ የመነጨውን ለጋስ ስጦታ ብቻ ነው። ይህ ጸጋ ንጹሕ፣ ቅዱስና ሙሉ አድርጎናል! ያለን ወይም ያሳካነው አልያም የገዛነው ምንም ነገር ከራሳችን እንደ ሆነ እንድናስብ በቂ ምክንያት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። የእግዚአብሔር ቸርነት፣ ጸጋ፣ ምሕረትና ፍቅር የሰማይን ትልቁን ስጦታ ወደ እኛ አምጥተዋል።

መልካም ውሎ🤗
https://kedusbible.com


በዚያ ምሽት በአጋንንት የተያዙ ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም መናፍስትን በቃሉ አስወጣ፤ በሽተኞችንም ሁሉ ፈወሰ። በዚህም ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ፤ “እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ።”
ማቴዎስ 8፥16-17

በክፉና በኢፍትሓዊነት ስንሠቃይ ኢየሱስ ምን የሚሰማው ይመስላችኋል? ኢየሱስ ሰውነታችን በሽታ ወይም ችግር ሲኖርበት ሊነካን የሚፈልግ ይመስላችኋል? በመጀመሪያ ኢየሱስ በዚህ ምሽት የተገፉትንና የማይነኩትን ሲነካ ስንመለከተው ይገባናል። ሁለተኛ ደግሞ፣ ኢየሱስን በመስቀል ላይ በሥቃይ ውስጥ ሆኖ ስንመለከተው ስለ ሕመማችን፣ ስለ ሞታችንና ስለ ውርደታችን እንደሚያውቅና እንደሚጠነቀቅልን ርግጠኞች መሆን እንችላለን። ሦስተኛ ደግሞ፣ ወደ ፊት ዕንባዎቻችንን ሁሉ ከዐይናችን ያብሳል፤ ሥቃይንና ሞትን ለዘላለም ያቆማል። ከዚያም ለዘላለም ክብሩንና ደስታውን እንጋራለን። ሟች ሆነን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ የኢየሱስን ጸጋ እንተማመናለን። ነገር ግን የምናወቀው ከፊሉን ብቻ ነው። ነገር ግን በማይሞት ሥጋ የኢየሱስን የመጨረሻ ፈውስና ድነት ሙሉ ለሙሉ የምናጣጥምበትና የምናውቅበት አንድ ቀን ይመጣል (1 ቆሮንቶስ 13፥9-12፣ 1ቆሮንቶስ 15፥35-58)።


የእለቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት
ዕብራውያን12፡22
፤ነገር፡ግን፥ወደጽዮን፡ተራራና፡ወደሕያው፡እግዚአብሔር፡ከተማ፡ደርሳችዃል፥ወደ፡ሰማያዊቱም፡ኢየሩሳሌም፥በደስታም፡ወደተሰበሰቡት፡ወደ፡አእላፋት፡መላእክት፥

የሐዋርያ መልእክት
1ኛ ጴጥሮስ 1፡6-7፤በዚህም፡እጅግ፡ደስ፡ይላችዃል፥ነገር፡ግን፥በእሳት፡ምንም፡ቢፈተን፡ከሚጠፋው፡ወርቅ፡ይልቅ፡
አብልጦ፡የሚከብር፡የተፈተነ፡እምነታችኹ፥ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሲገለጥ፥ለምስጋናና፡ለክብር፡ለውዳሴም፡ይገኝ፡ዘንድ፡አኹን፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ቢያስፈልግ፡በልዩ፡ልዩ፡ፈተና፡ዐዝናችዃል።
8-9፤ርሱንምሳታዩትትወዱታላችኹ፤አኹንምምንምባታዩትበርሱአምናችኹ፥የእምነታችኹን፡ፍጻሜ፡ርሱም፡የነፍሳችኹን፡መዳን፡እየተቀበላችኹ፥በማይነገርና፡ክብር፡በሞላበት፡ሐሤት፡ደስ፡ይላችዃል።
10፤ለእናንተም፡ስለሚሰጠው፡ጸጋ፡ትንቢት፡የተናገሩት፡ነቢያት፡ስለዚህ፡መዳን፡ተግተው፡እየፈለጉ፡መረመሩት፤
11፤በእነርሱም፡የነበረ፡የክርስቶስ፡መንፈስ፥ስለክርስቶስ፡መከራ፡ከርሱም፡በዃላ፡ስለሚመጣው፡ክብር፡
አስቀድሞ፡እየመሰከረ፥በምን፡ወይም፡እንዴት፡ባለ፡ዘመን፡እንዳመለከተ፡ይመረምሩ፡ነበር።
12፤ለእነርሱም፡ከሰማይ፡በተላከ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ወንጌልን፡የሰበኩላችኹ፡ሰዎች፡አኹን፡ባወሩላችኹ፡ነገር፡
እናንተን፡እንጂ፡ራሳቸውን፡እንዳላገለገሉ፡ተገለጠላቸው፤ይህንም፡ነገር፡መላእክቱ፡ሊመለከቱ፡ይመኛሉ።
13፤ስለዚህ፥የልቡናችኹን፡ወገብ፡ታጥቃችኹና፡በመጠን፡ኖራችኹ፥ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሲገለጥ፡የምታገኙትን፡
ጸጋ፡ፈጽማችኹ፡ተስፋ፡አድርጉ።

ሐዋርያት ሥራ
ሐዋ ሥራ 4:13፤ጴጥሮስና፡ዮሐንስም፡በግልጥ፡እንደ፡ተናገሩ፡ባዩ፡ጊዜ፥መጽሐፍን፡የማያውቁና፡ያልተማሩ፡ሰዎች፡
እንደ፡ኾኑ፡አስተውለውአደነቁ፥ከኢየሱስም፡ጋራ፡እንደ፡ነበሩ፡ዐወቋቸው፤

ምስባክ
መዝ 27:6፤የልመናዬን፡ቃል፡ሰምቶኛልና፥እግዚአብሔር፡ይመስገን።

ቅዱስ ወንጌል
ሉቃስ ወንጌል 6:9-19 9፤ኢየሱስም፦እጠይቃችዃለኹ፤በሰንበት፡በጎ፡ማድረግ፡ተፈቅዷልን፡ወይስ፡ክፉ፧ነፍስ፡ማዳንን፡ወይስመግደል፧አላቸው።
10፤ኹላቸውንም፡ዙሪያውን፡አየና፡ሰውዬውን፦እጅኽን፡ዘርጋ፡አለው።ርሱም፡እንዲህ፡አደረገ፥እጁም፡እንደ፡ኹለተኛዪቱ፡ዳነች።
11፤እነርሱምቍጣሞላባቸው፥በኢየሱስም፡ምን፡እንዲያደርጉበት፡ርስ፡በርሳቸው፡ተባባሉ።
12፤በነዚህም፡ወራት፡ይጸልይ፡ዘንድ፡ወደ፡ተራራ፡ወጣ፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ሲጸልይ፡ዐደረ።
13፤በነጋም፡ጊዜ፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ጠራ፥ከነርሱም፡ዐሥራ፡ኹለት፡መረጠ፡ደግሞም፡ሐዋርያት፡ብሎ፡ሰየማቸው፤
14፤እነርሱም፥ጴጥሮስ፡ብሎ፡እንደ፡ገና፡የሰየመው፡ስምዖን፥ወንድሙም፡እንድርያስ፥ያዕቆብም፡ዮሐንስም፥ፊልጶስም፡በርተሎሜዎስም፥
15፤ማቴዎስም፡ቶማስም፥የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ቀናተኛ፡የሚባለው፡ስምዖንም፥
16፤የያዕቆብ፡ይሁዳም፥አሳልፎ፡የሰጠውም፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ፡ናቸው።
17፤ከነርሱም፡ጋራ፡ወርዶ፡በተካከለ፡ስፍራ፡ቆመ፥ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ወገን፡ብዙ፡ሕዝብ፡ነበረ፥ደግሞም፡ሊሰሙትና፡ከደዌያቸው፡ሊፈወሱ፡ከይሁዳ፡ዅሉ፡ከኢየሩሳሌምም፡ከጢሮስና፡ከሲዶና፡ባሕር፡
ዳርም፡የመጡ፡ብዙ፡ሰዎች፡ነበሩ፤
18፤ከርኩሳንም፡መናፍስት፡ይሠቃዩ፡የነበሩት፡ተፈወሱ፤
19፤ከርሱም፡ኀይል፡ወጥቶ፡ዅሉን፡ይፈውስ፡ነበርና፥ሕዝቡ፡ዅሉ፡ሊዳስሱት፡ይሹ፡ነበር።

ቅዳሴ
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጉድጓድ

መልካም የጌታ ቀን🥰

Показано 20 последних публикаций.