ለመረጃ ያህል ስለጋራ መኖሪያ ቤቶች
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ እና ፍላጎት ለመመለስ የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በመዘርጋት የተለያየ የገቢ መጠን ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመክፈል አቅም ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት በመገንባት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
👉 በመንግስት አስተባባሪነት በ10/90፣በ20/80 እና በ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶችን ተገንብተው በ14 ዙሮች ከ300 ሺህ በላይ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፤
👉 ቤቶች የሚገነቡት ከባንክ በተገኘ የቦንድ ብድር ሲሆን ተቋሙ ቀደም ሲል የነበረበትን 56 ቢሊዮን ብር እዳ ለማቃለል በተደረገ ጥረት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ተመላሽ ተደርጓል፤
👉 ተመዝጋቢዎች የሚቆጥቡት ብር ቤቱ ሲደርሳቸው የሚከፍሉት እንዳይቸገሩ እንጂ ቤቶችን ለመገንባት የሚውል አይደለም፤
👉 እያደገ የመጣውን የመኖርያ ቤት ችግር ለመፍታት ሌሎች ተጨማሪ አማራጮች ተቀይሰው መተግበር ጀምረዋል፤
👉 ከ5ሺህ ቤቶች በላይ በተገጣጣሚ ቴክኖሎጂ እየተገነቡ ይገኛሉ፤
👉 የቤት አቅርቦቱን ለማስፋት በተደረገ ጥረት 60ሺ ቤቶች በግሉ ባለሀብት እንዲለሙ ተደርጓል፤
👉 በመንግስት እና በግል ዘርፍ አጋርነት ከ120 ሺ በላይ ቤቶች ግንባታ ስራ ተጀምሯል፤
👉 በበጎ ፈቃድ ባለሀብቶችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከ35ሺ በላይ ቤቶችን በመንግስት እና የግል ባለሀብቱን በማስተባበር ተገንብቶ በዝቅተኛ ኑሮ ላሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተላልፈዋል፤
👉 ፍላጎት እና አቅም ያላቸውን በ20/80 እና በ40/60 ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ 4,318 ነዋሪዎችን በ54 ማህበራት በማደራጀት ወደ ግንባታ እንዲገቡ ተደርጓል፤
👉 በተመጣጣኝ ዋጋ ለኪራይ የሚቀርቡ ቤቶችንም ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
👉 ተመዝግበው የቤት ባለቤት ለመሆን የሚጠባበቁ ነዋሪዎችን በአጭር ጊዜ የቤት ባለቤት ለማድረግ የቤት ልማት አማራጮች በማስፋትና በመተግበር ከምን ጊዜውም በላይ እየተጋ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
@Etstocks