ሜሎስ ለአልአዛር
ዕውቀቱ ከሌለህ እረፍ
ራስህን ማወቅ አስፈላጊ ነው ግዴታ ነው፡፡ እንዳወራኸኝ አገራችሁ ደካማ የስነጽሑፍ ባህል ነው ያላት ድሮ ስለተጻፉ የሃይማኖት መጻሕፍት አይደለም የማወራው ስለዛሬ ነው አገርህን በሚመለከት እዚህ ላይብረሪ ብፈልግ አንድ ነገር አላገኘሁም ያሉት ጥቂቶቹ መጻሕፍት ፖለቲካ ብቻ ናቸው ሲመለስለኝ ፖለቲካ ብላችሁ የተበላላችሁት በባዶ ሜዳ ነው ስነጽሑፍ ራስህን ለማወቅ ይረዳሃል እንዴት አንድ ሰው ሊለውጠው የሚፈልገውን ሳያውቅ ሊለውጠው ይፈልጋል? ካላወቀውስ እንዴት ይፈልገዋል? ምኞታችሁ ከዕውቀት ውጪ ነው ከዕውቀት ውጪ ውሳኔ የሚሰጠው ልጅ ነው ልጅ የተለኮሰውን ክብሪት ልብላ ይልሃል አረቄው ውሃ ይመስላልና ልጠጣው ይልሃል ወዘተ ልጁ አረቄውን ቢጠጣው ደፋር ወይም ጎበዝ አይደለም ደንቆሮ ነው እንዲህ ያለ ነገር ሲያጋጥም የሚመጣልኝ ምክንያት አንድ ነው ሌሎችን ለመምሰል መፈለግ በሙሉ የአገራችሁ አብዮተኞች ኢሚቴተርስ ናቸው ዕውቀቱ ከሌለህ ታዲያ ነገሮችን እንዴት ታነቃንቃለህ ? እንደዚህ አይነት ሰዎች ዕውቀቱ ከሌላቸው ምኞቶቻቸውን በግድ እውን ማድረግ አለባቸውና እሱን በስራ ላይ ለማዋል የሚቀራቸው የመጨረሻ አማራጭ ሴራና ጉልበት ነው አይመስልህም ? በዚህ አይነት ሁኔታ የተገነባ ርዕዮተ ዓለም ነጭናጫ የሆነች ደህና ማህፀን የሌላት ቆንጆ ሴት ናት ሺህ ጊዜ ብተተኛት አንተም አትጠግብም እሷም አትወልድም ምንም አልነካትም ግን ረግባለች ብትወልድም የምትወልድልህ ልጆች አይምቧቹ እግር የላቸው አይጠግቡ አፍ የላቸው ልጆች አይደሉም ገና ስም የሚሰጣቸው ፍጡራን ናቸው ይሄን ስል "አገራቸው ውስጥ ያሉት ቤተ መጻሕፍት በጠቅላላ ሶስት ናቸው እንዴ ? ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ "
ከአዳም ረታ መረቅ መጽሐፍ የተወሰደ