ዴዚዴራታ
በዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፡፡ ከጸጥታ ሠላም ሊገኝ የሚችል መሆኑንም አትዘንጋ፡፡ ያለአግባብም ሳትበለጥ የተቻለህን ያህል ከሰዎች ሁሉ ጋር ስምምነት ይኑርህ፡፡ እውነት ነው ብለህ የያዝከውን ነገር በጥሞናና በግልፅ ከመናገር ወደኋላ አትበል፡፡ ሌሎች የሚናገሩትን ከመስማትም አትቦዝን፡፡ ሆነ ብሎ ለሚያዳምጣቸው ከዳተኞችም ሆነ ከደደቦች ቁም ነገር አይታጣም፡፡ እራስህን ከሌሎች ሰዎች ማመዛዘን ከያዝክ እብሪተኛና መንፈሰ መራራ ልትሆን ትችላለህ፡፡ ምክንያቱም ከሰዎች መካከል ካንተ የሚበልጡም የሚያንሱም አይታጡም፡፡ በምትሰራው ስራ መሳካትም ሆነ በወደፊት ውጥንህ ተደሰት፡፡ የምትሰራው ስራ ዝቅተኛም ቢሆን የኔ ነው ብለህ ያዘው፡፡ በዚህ ወረቱ ተለዋዋጭ በሆነ ዘመን የሚያዋጣው የአንድ ሙያ ባለቤት ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ አለም በሸፍጥ የተሞላ በመሆኑ ገንዘብን በሚመለከት ነገር ጥንቃቄ አይጉደልህ፡፡ ይህም ሲባል ሰው ሁሉ ክፉ ነው ብለህ በደፈናው አትገምት፡፡ ከፍተኛ ቁም ነገር ያለው ተግባር ለመፈፀም የሚጣጣሩ ብዙ ሰዎች መኖራቸውንና ህይወትም ብዙ ጀብዱ የሞላበት መሆኑን አትሳት፡፡ በራስህ ተማመን፡፡ በተለይም ፍቅር ማስመሰልን የሚጠላ መሆኑን እወቅ፡፡ እንዲያውም ፍቅር በዘፈቀደ የሚታለፍ ነገር አይደለም፡፡ በዚህ የመንፈስ ድርቀትና መሰልቸት የሚያጠቃው አለም እንደሜዳ ሳር ጠውልጎ የሚለመልም ፍቅር ብቻ ነው፡፡ የወጣትነት ወራት ፍላጎትህ ብዙ ዘመን ለተጠራቀመ የሽምግልና ምክር በለዘብታ ይገዛ፡፡ ሳታስበው ለሚያጋጥምህ መከራና ችግር ድጋፍ እንዲሆንህ የመንፈስ ፅናት ይኑርህ፡፡ .........
ቦልቲሞር ከሚገኘው የጥንቱ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በ፲፮፻፺፬ ተገኘ፡፡
By Max Ehrmann