Book Recommendation
አልተዘዋወረችም
ከአሌክስ አብርሃም
ሀገሬ ጨዋታ እና ተጫዋች ይበዛባታል እንደ ሀገር ልጅነታችንን አልጨረስንም ይሆን ? እስከምል ድረስ የሀገሬ ጨዋታ ወዳድነት ያስደምመኛል፡፡
የሰዓት መቁጠሪያ እጀታዎች ዞረው የተነሱበት ቦታ ላይ እያረፉ ጊዜን ቢጥቆሩም ጊዜ ግን ዞሮ አይመለስም እንደ ጅራታም ኮከብ ከሆነ ጨለማ ተነስቶ ወደ ሆነ ጨለማ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚምዘገዘግ መጨረሻም መጀመሪያም የሌለው ግትልትል ፉርጎ ነው፡፡ የትኛው ዘመን ላይ ነበርን ? ስንል የትኛው ፉርጎ ላይ ነበርን እንደማለት ነው፡፡
ባርነትም እንደ ነፃነት የሚናፍቅበት ጊዜ እንዳለ ማን ያውቃል ?
ሕፃናት ክብሪት ሲለኩሱ ድፍን ቤት እንደሚቃጠል አስበው አይደለም የጅል ድርጊት በአዋቂ ነፍስ የተደበቀ ሕፃንነት ነው ቀጥሎ ያለውን አለማስተዋል፡፡ የአንዱ ጨዋታ ለሌላው ሕይወት ነው፡፡
አበባም ይሁን ድንጋይ በግድ እስካሸከሙን ድረስ ያው ሸክም ነው
ለፋሽን ግድ የለኝም ለውበትም ያን ያህል አልጠነቀቅም ምቾታቸው ድሎቴ ነው፡፡ ውስጣቸው ኑሪያለሁ ከቤቴ ከሕይወቴ ከአገሬም በላይ ልብሶቼ ውስጥ ኖሬያለሁ ፣ መደበቂያዎቼ ነበሩ፡፡ የእኔ የራሴ ባንዲራዎች ነበሩ ልብሶች ተራ ነገር አይደሉም የግል ባንዲራዎቻችን ናቸው፡፡ ሀገር ባንዲራውን ሰው ልብሱን ከጣለ ምን ቀረው ? ሁለቱም አረጀ ብለን የምንወረውረው ልብስ ልብስ ብቻ አይደለም የዕድሜ አሻራችን ጭምር እንጂ፡፡ ካለነገሩ አይደለም የለበስነውን ልብስ ተመሳሳይ ሌሎች ለብሰውት ስናይ ውስጣችን በቅሬታ የሚሞላው ሌሎች ባንዲራችንን የነጠቁን ስለሚመስለን ነው፡፡
inbox me at https://t.me/yosefdibaba for the PDF file.