አንድ ቀን፤ ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ የእውነት እና የህሊና ጥያቄ ብቻ ይሆናል፡፡ ትርጉም ያለው ነገር እንፈልጋለን፡፡ ምን አይነት ሰው ልሁን ? እንዴት ያለ ኑሮ ልክ ያደርገኛል ማለታችን የነፍሳችን ዓላማ ነው፡፡ ምዕመኑ አምልኮውን፣ መሪዎችም አገዛዛቸውን ይጠይቃሉ፡፡ መምህራን ከሚናገሩት፣ ነጋዴዎችም ከትርፋቸው ወዲያ ስላለው ነገር ማሰባቸው አይቀርም፡፡ ሁላችንም የገዛ ራሳችንን ጽድቅ ለመፈጸም የማንሻገረው ወንዝ አጠገብ እንቆማለን፡፡ ዳሩ ግን ብልጠት የመሰለን ስግብግብነት ከላያችን እስኪራገፍ ድረስ ብዙ ነፍስ [ነፍሶች] ሸቀጥ ሆነው ያልፋሉ፡፡ ደግሞ ከበሰለው ኋላ፣ ካለፈው ያልተማረ፣ ጥሬ ትውልድ ከማሕፀን በር ላይ ይገኛል፡፡
©Book For All