በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ተሽከርካሪን ደርቦ ማቆም 1 ሺህ ብር ያስቀጣል‼️
በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ቤቶች መከፈትን ተከትሎ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ፤ በመዲናዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዙሪያ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ደርቦ ማቆም በጥብቅ እንደሚከለከልና እንደሚያስቀጣ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታወቀ።
በትምህርት ቤቶች መግቢያና መውጫ ሰዓት በዋና መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ደርቦ ማቆም 1 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ አስታውቀዋል።
ወላጆች ተሽከርካሪን መንገድ ላይ ለጥቂት ሰከንዶች ብቻ አቁመው ተማሪዎችን ማውረድ የሚችሉ ሲሆን፤ ነገር ግን ተሽከርካሪን ለደቂቃዎች በአካባቢው ማቆምም ሆነ አቁሞ መውረድ ፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
የትራፊክ መጨናነቅን ለማስቀረት ሲባል፤ በግል ተሽከርካሪ ወደ ትምህርት ቤት ይጓጓዙ የነበሩ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው የሰርቪስ ተሽከርካሪዎች እንዲጓዙ ከትምህርት ቤቶች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ ማኅበረሰቡን ለማስተናገድ ከ 500 እስከ 1,000 የሚደርሱ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች ስምሪት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ከትምህርት ቤት አመራሮች እና ከወላጅ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት አጥፊዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።
@darashMedia