🔸ኢትዮጵያ ከሚገኙ 37 የንግድና የሕዝብ የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች ውስጥ የምልክት ቋንቋን በመሰናዷቸው ለማካተት የሚሞክሩት 5ቱ ብቻ ናቸው ተባለ።
🔸እነዚህ 5 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ቢሆኑ ታዲያ መረጃዎችን በተሟላ መልኩ መስማት ለተሳናቸው ተደራሽ የሚያደርጉ አይደሉም ያለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኋን ባለሥልጣን ይህም መስማት የተሳናቸውን ዜጎች ከመረጃ እያራቀ መሆኑን ጠቁሟል።
🔸መስማት የተሳናቸው ግለሰቦችም በመገናኛ ብዙኋን ትኩረት ባለማግኘታቸው የተነሳ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንዲሁም ፓለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚሰራጩ መረጃዎች መገለላቸው ሲገለፅ ይህም ህይወታቸውን እያከበደባቸው ስለመሆኑ ተነግሯል።
🔸ይህን ችግር ለመፍታት መገናኛ ብዙኋን መረጃዎችን ለሁሉም ዜጋ ለማድረስ የተጣለባቸውን ግዴታና ኋላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ያለው ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይህን ተፈፃሚ የማያደርጉትን በመከታተል በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
🔸በዚሁ መድረክ ላይ የተካፈሉ መገናኛ ብዙኋን እና የአካል ጉዳተኞች ተወካዮች አሁን በሥራ ላይ ካሉ የንግድና የሕዝብ መገናኛ ብዙኋን በተጨማሪ መስማት የተሳናቸው ላይ ብቻ አተኩሮ የሚሰራ የቴሌቪዢን ጣቢያ ሊቋቋም ይገባል ብለዋል።
መረጃዉ የአቤል አበበ ነዉ::
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews