ኦቪድ የተባለው ድርጅት የዛሬ አመት ገደማ በሸጣቸው ቤቶች ላይ ቅሬታ ያላቸው ቤት ገዢዎች ለመሠረት ሚድያ ተከታታይ መረጃ ሲልኩ ነበር
የቅሬታቸው መሰረትም ቃል በተገባላቸው መሰረት የቤቶቹ ግንባታ እየተካሄደ አይደለም የሚል ነበር፣ ለዚህም የሳይቶቹ የምስል እና የቪድዮ ማስረጃ አለ።
ይሁንና በዚህ ያልተደሰቱት ኦቪዶች ሁለት ነገር አደረጉ: አንደኛው የመሠረት ሚድያ ፕላስ (Meseret Media+) የዩትዩብ ቻናል ሞኒታይዜሽንን ሪፖርት አርገው አዘጉ፣ በሌላ በኩል እኔን አናገሩ።
ቻናሉን ማዘጋታቸው ትክክል እንዳልሆነ ነግሬያቸው (እንዳዘጉ የተናገሩበት የድምፅ ቅጂ/ሪከርድ ሙሉው አለ) በዜናው ላይ ማንኛውም አይነት ቅሬታ እና ትክክል አይደለም ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ ላኩት እና አጣርተን ስህተት ከሆነ ሌላ የእርምት ዜና እንሰራለን አልኩ።
እሺ ተባብለን ከጨረስን በሗላ ግን "በአምስት ቀን ውስጥ የመረጃዎቻችሁን ምንጭ አምጡ፣ ወይም እንከሳለን" ብለው ማስፈራርያ መሰል 'ድንፋታ' በኢሜይል ላኩ 🙂
ማስፈራርያው መሠረት ሚድያ ላይ እና ኢትዮ ፎረም ላይ እንደሆነ በሶሻል ሚድያ ገፆቻቸው ፅፈው አየሁ።
የሚገርመው ዜናው መሠረት ሚድያ ላይ ከወጣ በኋላ ቤት ገዢዎችን ጠርተው መዘግየት የተፈጠረው በአዲሱ 'ሴት ባክ' ህግ ወዘተ እንደሆነ እና በቅርቡ ግንባታ እንደሚጀመር ራሳቸው ተናግረዋል።
ዜናው ውሸት ነው ብለው ካሰቡ ቀላሉ ማስረጃ በዜናው ላይ የተጠቀሱትን የጉለሌ እና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሳይቶቻቸውን በምስል እና ቪድዮ አስደግፈው አቅርበው የመሠረት ሚድያ ዜናን ውሸት ማጋለጥ ነበር፣ ግን አላረጉም።
ሁሉ በእጃቸው እና በደጃቸው የሆነ መስሏቸው ይሁን መንግስት አዲስ አበባ ሊያገኝ ያልቻላቸውን ጋዜጠኞች በዚህ በባለቤትነቱ ዙርያ ብዙ ህዝብ ጥያቄ በሚያቀርብበት ድርጅት በኩል ድምፅ ማፈን የሚችል መስሎት አይታወቅም ይህን ተግባር ፈፅሟል።
አንድ ነገር ማለት ይቻላል... በዚህ ዘመን የህዝብን እውነት እና የሚድያን ስራ ማፈን አይቻልም። የፈለገ ያህል ሀብት ያለህ የቢዝነስ ድርጅት ሁን፣ ቱባ ባለስልጣን ሁን።
You are selling properties to the public so you remain in the public eye, and no authority can silence criticism or dissenting voices.
The voice of the people cannot be suppressed!
@EliasMeseret