ውድ የኢትዮ- ፓረንትሰ የተማሪዎች ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሙሉ
የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን እንደሚታወቀው
የሁለተኛው ወሰነ ትምህርት የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀመራል። የመማር ማስተማሩን ሂደት ይበልጥ የተሳለጠ ለማድረግ የሚከተሉትን የተማሪዎች ስነስርአት ክትትል እና ቁጥጥር ደንብ እና መመሪያዎች በደንብ በማጤንና ልጅዎን በቤት በማስረዳትም ለተግባራዊነቱ ሀላፊነትዎን
እንድትወጡልን በጥብቅ እያሳስብን በቀጣዮቹ ወሰነ ትምህርት በጋራ ጠንክሮ በመስራት ተማሪዎቻችንን በእውቀትና በስነምግባር የምንቀርፅበት እንደሆን ተስፋ አደርጋለሁ ።
ገርጂ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
የተማሪዎችስነስርአት ክትትል እና ቁጥጥር ደንብ እና መመሪያዎች
1. የትምህርት ሰዓትን በተመለከተ
ጊዜ አላቂ ሀብት ነው ስለዚህ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ማርፈድ የትምህርት ሰዓትን መስረቅ ነው፡፡ ደግሞም የስንፍና ምልክት ነው፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ቀናት ጠዋት እስከ 2፡15 በት/ቤት ግቢ ውስጥ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደወል ሲደወል ወዲያውኑ መሰለፍ አለባቸው፡፡ ከ 2፡20 ጀምሮ ባለው ጊዜ የሚመጡ ተማሪዎች አርፋጆች ይሆናሉ፡፡
2. አለባበስን በተመለከተ
ተማሪዎች የት/ቤቱን የተማሪ የደንብ ልብስ በአግባቡ ለብሶ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ተማሪዎች ሁልጊዜ ወደ ት/ቤት ሲመጡ ንፁህ የተማሪ የደንብ ልብስ ማድረግ አለባቸው፡፡ የደንብ ልብስን አግባብ ባልሆነ መልኩ ማሰፋት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
የፀጉርና የግል ንጽህናን መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ጥፍራቸውን በየጊዜው በአግባቡ መቁረጥ አለባቸው፡፡
ወንዶች ፀጉራቸው አጠር ብሎ በአግባቡ የተስተካከለ መሆን አለበት፡፡ ጆሮን መበሳትና የጆሮ ጉትቻ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ሴቶች በት/ቤት ውስጥ የጥፍር ቀለም፣ ትልልቅ የጆሮ ጉትቻ፣ የአንገት ሀብል፣ የእግር አልቦ፣ የእጅ አንባር፣ የፀጉር ጌጥ እና ማንኛውም የመዋቢያ ነገሮችን መጠቀም አይፈቀድላቸውም፡፡
3. መታወቂያ መያዝን በተመለከተ
ተማሪዎች መታወቂያቸውን ት/ቤት ሲመጡ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
ተማሪዎች በጥበቃና እንዲሁም በግቢ ውስጥ ማንኛውንም ሰራተኛ መታወቂያ እንዲያሣዩ ሲጠይቁ ወዲያውኑ የማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡
4 - የሰልፍ ሥነ-ስርዓትን በተመለከተ
ማንኛውም ተማሪ በሰልፍ ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝቶ የሚተላለፈውን መልዕክት መከታተልና ብሔራዊ መዝሙር ሀገራዊ ፍቅርን በሚያሳይ መልኩ መዘመር አለበት፡፡
5. የት/ትን ሰዓት በአግባቡ መጠቀምን በተመለከተ
በት/ት ሰዓት ከክፍል መውጣት የሚቻለው የመምህሩን ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡
6. ከት/ቤት መውጣትን በተመለከተ
ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከገቡ በኃላ የጤና ችግርን ጨምሮ አስገዳጅ የሚያስወጣ ሁኔታ ከተፈጠረ በር/መ/ሩ ወይም በዪኒት መሪ ፈቃድ ወላጅ እንዲወስድ ይደረጋል ፡፡
7. መቅረትን በተመለከተ
ተማሪዎች በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆኑ ችግሮች ከት/ት ሲቀሩ ወደ ት/ቤቱ በመደወል ፈቃድመጠየቅ አለባቸው፡፡
የክፍል ኃላፊ መምህር ለበላይ ኃላፊ እያስተላለፈና መረጃን በመያዝ እስከ አንድ ቀን ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከዚያ በላይ ላሉት የት/ትቀናት ፈቃድ መስጠት የሚችለው ር/መ/ሩ ወይም ም/ር/መ/ሩ ይሆናል፡፡
8. የአመጋገብ ስርአትን በተመለከተ
ተማሪዎች የእረፍት ሰዓት ቁርስና ምሳ በስርአቱ መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡
በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማስቲካ ማኘክ የተከለከለ ነው፡፡
ከረሜላና ቸኮላት የመሳሰሉ ጣፋጭ ነገሮችን ወደ ት/ቤት ይዞ መምጣት አይፈቀድም፡፡
9. የት/ቤቱን ንብረት አጠቃቀምን በተመለከተ
ተማሪዎች በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጪ የት/ቤቱን ንብረት በአግባቡ በመጠቀም የየዕለት ት/ታቸውን መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡
በዴስክ፤ በጠረጴዛ፤ በግድግዳና በጥቁር ሰሌዳ፤ እንዲሁም በሽንት ቤት ግድግዳ፣ በርና በመፅሀፍት ላይ መፃፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
10 - የተማሪዎች እርስ በርስ ግንኙነትን በተመለከተ
ተማሪዎች በት/ቤቱ ውስጥ ከማንኛውም ተማሪ ጋር መልካም ግንኙነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
መሳደብ (መዝለፍ)፣ መደባደብ፣ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ሴት ተማሪዎችን ከማንኛውም ጥቃት መከላከል ይገባል፡፡
11 - ሙሉ ትኩረት ለትምህርት መስጠትን በተመለከተ
ትምህርት የተማሪውን መሉ ትኩረት የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች የተቃራኒ ፆታ የፍቅር ጓደኝነት በት/ቤት ውስጥም ሆነ ከት/ቤት ውጪ እንዲመሰርቱ አይፈቀድም፡፡
12 - በት/ቤት ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎችንና የተለያዩ ጽሁፎችን በተመለከተ
በት/ቤት ውስጥ የተለጠፈ ማንኛውም ማስታወቂያ ማንበብ ተገቢ ሲሆን በላዩ ላይ መፃፍና መገንጠል ግን በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
13 - በግል ጥረትና ንብረት ብቻ መጠቀምን በተመለከተ
ሀ)ኩረጃ የጥገኝነት መገለጫ ነው፡፡ ተማሪዎች ባላቸው እውቀትና ክህሎት ሊተማመኑና ከትጋታቸው ብቻ በሚገኝ ውጤት ላይ ሊደገፉ ይገባል።
ማንኛውም ተማሪ ፈተና ሲኮርጅ በፈታኝ መምህሩ ቢያዝና ቢፈረምበት እንደጥፋቱ ሁኔታ ከፈተና ውጤቱ ላይ ከመቀነስ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ውጤት እስከመሰረዝ በሚያደርስ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል።
ለ) ስርቆት አስፀያፊ ተግባር ነው፡፡
የሌላን ተማሪ ወይንም የት/ቤቱን ንብረት ሳያስፈቅድ መውሰደ የስርቆት ተግባር እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
14 - ለመምህራን የሚገባውን ክብር መስጠትን በተመለከተ
ተማሪዎች የዕውቀት አባት/እናት የሆኑ መምህራንን ማክበር መታዘዝና በሚያሳዩአቸው መንገድ መመራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከመ/ራን ጋር የሚፈጠር ማንኛውም አለመግባባት ከመምህሩ ጋር በመወያየት፣ በዚህም ካልተፈታ ለት/ቤቱ አስተዳደር በማሳወቅ መፍታት ይቻላል፡፡
15 - ከሱስ የጸዳ ህይወትን በተመለከተ
ተማሪዎች በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥም ሆነ ከት/ቤት ቅጥር ግቢ ውጪ ከሱስ አምጪ ነገሮች የፀዳ ህይወት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
16 - የተማሪዎች አካላዊ ደህንነትን በተመለከተ
የተማሪዎች ደህንነት ላይ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አደገኛና ስለታም መሳሪያዎችን በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
17. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችንና ገንዘብን በተመለከተ
እንደሞባይል፣ I-pod, Lap top, Palm top, mp3 player, Walkaman, ሬድዮ የመሳሰሉትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በት/ቤት ውስጥ ይዞ መገኘት አይፈቀድም፡፡
ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ቁሳቁሶች በት/ቤቱ ውስጥ ይዘው ቢገኙ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃው በት/ቤቱ ይያዝና ወላጅ እንዲያመጡ ይደረጋል፡፡ ንብረቱ በትምህርት ቤቱ መመሪያ መሰረት የት/ት ዘመኑ እሰከሚያልቅ ድረስ በት/ቤቱ ተይዞ ይቆያል፡፡
ተማሪዎች ለትራንስፖርት ከሚሆን መጠን ያለፈ ገንዘብ ይዘው ወደ ት/ቤት መምጣት አይፈቀድላቸውም፡፡
ማሳሰቢያ
በክፍልም ሆነ በውጭ የሚፈጸሙ ጥፋቶች የግቢውን ማህበረሰብ ሁሉ የሚመለከተው ሲሆን ለአፈጻጸም ከተማሪው የክፍል መ/ር ጀምሮ ወደ ላይ በሚኖሩት የኃላፊነት እርከኖች ሪፖርት ይደረጋል፡፡
ምርመራን የሚያካትት ድርጊቶች ሲከሰቱ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚታይና የውሳኔ ሀሳብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
ከባድ የድሲፕሊን ጉድለት/ግድፈት/ ሲፈጸም በአንድ ጊዜም ቢሆን ከት/ቤት እስከመባረር ድረስ የሚያደርስ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡