ትንሳኤ ዘኢትኤል መማሪያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የአባቶቻችን እና የሀገራችን ታሪክና ጥበብ ግዕዝን, ስለጥንት ነገስታት ታሪክ፣ ስለዕፆች፣ መድሀኒቶች፣ መሰውሮች፣ የደመና ጥበብ ፣ቅርሶች፣ጥንታዊ የብራና መፅሐፍት፣ስነ ፈለክ ፣አክሲማሮስ፣ራዕየ ሳቤላ፣መፅሐፈ ጅማትርያ ፣መፅሐፈ ፓዝዮን፣መፅሐፈ ፀሐይ፣መፅሐፈ ልሳን፣መፅሐፈ ጥበብ፣የመላእክት ቋንቋ ወዘተ ... ለጓደኛ ያስተላልፉ ኢትኤልን ስለመረጣቹ አመሰግናለሁ ይቆየን.. 👳‍♂

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ቶንሲል በየጊዜው እየታመማችሁ ለተቸገራችሁ ፍቱን መድሐኒት በቀላሉ የሚገኝ እነሆ
ገቢር :3 የጠለንጅ ቀንበጥ ቀርጣችሁ በውሀ አጥባችሁ ጨምቃችሁ ለ1 ደቂቃ አፋችሁን መጉመጥመጥ ወይም ቢዋጥም ምንም ችግር አያመጣም እንደውም የደም ስርዓት ያስተካክላል መልካም ቀን @truth00011


የመንፈስ ቅዱስ ልዩ ጥበብ ነው ይሰራል እፁብ ድንቅ የሆነ ጥበብ ነው።

በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ጸሎት ፡ በእንተ ፡ ነገረ ፡ ምስጢር ፡ ወጥበብ ፡ ሩህ ፡ ሰዓራህ ፡ አናን ፡ ጋዶሌሽ ፡ ኖጃ ፡ መቶሐ ፡ ሐሽመል ፡ አዳም ፡ አርባፋኒም ፡ አርባ ፡ ከናፊም ፡  ወረጀሌሄም ፡ ረጀል ፡ ያሸራህ ፡ ከሐፍረጀል ፡ ኤጀል  .......... ቧሮጥ ፡ ኖጃላኤሽ ፡ ባራቅ ፡ ባዛቅ ፡ ተርሺሽ ፡ ሐውፈን ፡ በጦሀውፈን ፡ ጀበህም ፡ ወጆባላህም ፡ ወይራ ፡ ቆልማየም ፡ ረቢም ፡ ቆልሻዳይ ፡ ቆልመሐን ፡ ዕብን ፡ ሰንፔር ፡ ደሙጥኪስ ፡ አዳም ፡ ሐሽመሌሽ ፡ ኤሽኖጃ ፡ ቀሽታሸር   ይህበዓናን ፡ በዮም ፡ ቃለ ፡ መድብር ፡ ማሀዞሀ ፡  ረዝዱባር ፡
ሆማዱባር ፡ ቃሀዱባር ፡ ንገር ፡ ንገር ፡ ንገረኒ ፡ ወአርእየኒ ፡ ኲሎሙ ፡ ምስጢር ፡ ወጥበብ ፡ ሊተ ፡ ለገብርከ   እገሌ፡፡  ገቢሩ ፡ ጠዋት ፡ ተነስተህ ፡ በሸክላ  ........ ፡ ድገም ፡  በእሳት ፡ሰረገላ  ፡ይመጣሉ ፡ አትፍራ ፡ መላእክት ፡ ናቸው ፡ ደግ ፡ ነገረን ፡ ሁሉ ፡ ይነግሩሀል ፡ ያሳዩሀል ፡ ከሄዱ ፡ በኋላ ፡ ውሀውን ፡ በንጹህ ፡ ቦታ ፡ አፍስሰው፡፡


፨ስመ ጋኔን ወፈውሱ፨
የአየሩ ጋኔን አርጋፎር ይባላል፣ የውሃ ጋኔን፤ የገደል ጋኔን ሙርጃን ይባላል፣ የአመዱ ጋኔን የመቃብር ጠባቂ ጋኔን ዱማ ከልከሊዎስ ይባላል የከተማ የዱር ጋኔን ሌጌዎን ይባላል፣ የቤት የማጀት የጉፍ ጋኔን ገብሮ ስንዝሮ ወግዶ ደም ቀለቡ አረንጓዴ ልብሱ ደም ቀሚሱ ይባላሉ።
  እዚህን ማሰርያ ጸሎተ ቆጵርያኖስ፣ መርበብተ ሰሎሞን፣ መጽሔተ ሰሎሞን፣ ከዳዊት እግዚአብሔር ያበርህ ሊተ፣ ዘየኃድርን በረድኤተ ልዑል፣ ሶበ ጸዋክዎን፣ አምላኬ ነጽረኒ፣ እግዚአብሔር አምላከ መድኃኒትየን፣ ይኄይስ ተአምኖን፣ ተፈሥሑ ጻድቃንን፣ ንዑሳነ እምአኃውየን፥ ከነብያት ጸሎተ ሙሴን፣ ጸሎተ ሐናን፣ ኅቡዕ ስም ሐሮፓሮስን ይህን እህል ሳይቀምሱ ውሃ ሳይጠጡ ቢጸልዩ ሁሉ ይለቃል ድውይ ሁሉ ይፈወሳል በአምላክ ኃይል በሥልጣነ እግዚአብሔር ይድናል።
  ፨፨፨ @truth00011 ፨፨፨


+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል::  የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ?  እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
@truth00011


سحر

"أمديك، ديو ديو، يسوع."

  صل السحر في نصف الليل سبع مرات أو تسع وأربعين مرة على يدك اليسرى والليمونة، وباليد التي صليت عليها اضرب النافذة التي علقت فيها الملابس حتى تصل إلى الأرض سبع مرات.  دفن الليمون تحت الفرشا
ፍቱን ነው @truth00011




አዕዋፋት እና ካፈቾዎች።

(ክፍል - ፩)

(ዙፋን ክፍሌ)
--------


-------
ከፋ(ካፋ፥ካፈቾ) ከጥንታውያን የጎንጋ ቤተሰብ (Gonga Families) ከሚባሉት ሕዝቦች(ከፋ፣ሸካ-እናርያ ፣ሽናሻና ጃንጀሮ)
መካከል አንዱ ነው። ጎንጋ ባሁኑ ጊዜ በአገራችን የተለያዩ ክፍሎችና አቅጣጫዎች ተበታትኖ ይገኛል። ከፋና ሸካ ባገራችን ደቡብ ምዕራብ ይገኛሉ። ዛሬ ስለ ከፋዎች ነው ልነግራችሁ ያሰብኩት።

ስለ ከፋዎች እና ስለ አዕዋፎቻቸው።
ከፋዎች እና ተፈጥሮ ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ከዛፉ ከወፉ ፣ ከወንዙ ፣ ከላሙ ከበሬው ይግባባሉ። ቋንቋ አላቸው።
በሬዎቻቸውና ላሞቻቸው ስም አላቸው። ስም አወጣጡም ብዙውን ጊዜ የከብቱ የቆዳ ቀለም ላይ በመመስረት (ቦቃ፣መጋላ..ወዘተ አይነት) ነው።

በስም ጠርተው ብለው
መዳፍ ሲዘረጉ ስሙ የተጠራው ከብት ሰተት ብሎ ሲመጣ ማየት
አጀብ ያሰኛል። አንዳዴ ከብቱ ጌታውን ሲያይ ብቻ ስሙ ሳይጠራ ይመጣል። የመጣውን ከብት(ላም/በሬ) አሞሌ ያስልሱታል።አሞሌ ቢያጡ ግራዋ ቀጥፈው ያበሏቸዋል(ግራዋ ከብቶችን የማይማረረው ለምንድነው? ምሬቱን ይሆን ሚወዱት? ተፈጥሮወጥተው የሆነ ምላስ የላትም? ይኸው ይመስለኛል የስሙርነቷና
የመቀጠሏ ምስጢር።) ግራዋም ከታጣ ከብቱ ትናንት የበላበት እጅ ነውና ባዶ መዳፍ ይልሳል።

ባለቤትየው ቁጭ ያለ እንደሆነም
የጌታውን ራስ ይልሳል(በላብ መልክ የወጣውን ጨውይሆናልን ..?)። አለ ጌታው የማይጠመድ በሬ ፥ የማይለጎም ፈረስ
፤ አለእመቤቷ የማትታለብ ላም አሉ።
ከፋ ተወልደው ያደጉ በሬዎች(በሬም እንደሰው ተወልዶ ያድጋልን? - አዎን!) ቋንቋ ያውቃሉ። ሲሏቸው ቀጥ ይላሉ።

በሬው እያረሰ ያዳለጠው፥የወደቀ እንደሆነ ገበሬው እንደሰው ይለዋል ። በሬውም
ይሰማል ይኼን። ያውቃል ይኼን።
ከተራራው፥ከጋራው - ከወጠጤው ከአውራው ፤ ከዛፉና ከሐረጉ -
ከጎባጣው ከዝርጉ ፤ ከ አድባርና ከደብሩ - ከአዝመራው ከመኸሩ ከክረምትና ከበጋው..ከዝናብና ፀሐዩ ፣ ከበልግና ከጸደዩ፥ከሰኔና ከነሐሴ ከመስከረምና አደዩ... ወዘተረፈ ያላቸውን ቁርኝትና ቋንቋ
ካነሳሁ ''...ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ '' እንዳያስብልብኝ ቶሎ ወደ ተነሳሁበት ልመለስ። ከፋና አዕዋፍ።

፩. ካፌ/ካፎ - ወፊት/ወፍ - ዖፍ*

በዘልማድም ይሁን ልብ ብለነው የ ወፎችን ዝማሬ እንሰማለን።ያዳመጥን ግን ያለጥርጥር ጥቂቶች ነን። በተለይ በሥነጥበብ ስራዎች ላይ ጎልቶ ሲነገር ስለሰማን ብቻ የወፎችን ዝማሬ ነገር
የምናውቅ ይመስለናል። ያብዛኞቻችን እውቀትና አድናቆት ግን የ 'ስማበለው'ና ለራሳችንም ሳይታወቀን (Unconsciously) ነው።

ይሄን ለመታዘብ እንዲሁ አበባን ፣ ጨረቃን ፣ የፀሐይ ጮራን...ወዘተ "እወዳለሁ" እያለ ፣ አስቁመህ ለነዚህ ነገሮች ያለው ፍቅር ከምን የመነጨና እንዴት ያለ እንደሆነ ፣ መደመሙስየትምህርት ድረስ እንደሆነ ሲጠየቅ ግራ የሚገባውን ሕብዝ** መመልከት ነው። ታዲያልህ ከፋዎችና ፣ የወፍና ፥ የወፍ ዝማሬ ነገር ያላቸው
ግኑኝነት የ 'ስማበለው'ና የዋዛ ባይሆን ነው ልነግርህ መነሳቴ።ከፋዎች ወፊት ከፋ እንደሆነች ያምናሉ። በፍጹም ያምናሉ።
በአፈታሪኮቻቸውም ሆነ ዛሬ ባሉት ከፋዎች ዘንድም ወፊት ቋንቋዋ ከፍኛ እንደሆነ ያምናሉ። ቢያንስ ከፋ ውስጥ ያለች ወፊት ከፋ ናት።በወፍ ያስተነብያሉ። ያስተነትናሉ። ይተነትናሉ ። ወፊትን ያምናሉ።መንገድ ሲወጡ ፣ ከዳኛ ዘንድ ነገር ሲኖራቸው ፤ የያዙትን እኩይ መክያ(በትር፣ጦር አንካሴ) ክረምት እንደሆን መሬቱ እንዳያዳልጣቸው እየተመረኮዙ ፤ በጋ እንደሆን እትከሻቸው
አጋድመው በሃሳብ ተውጠው ጭልጥ ብለው ዱሩን እየጣሱ ድንገት የዱር ወፍ ከሃሳባቸው ታናጥባቸዋለች...

ከሁለት አንድ ነው፦
✤"ዴ'ተ ገት ፥ ወድተ ገት ፤ ሻታህን! -በጀልኝ በል ፥ አማረ በል፥ ሰመረ በል -አትፍራ!"
ይኸንን ያለችው እንደሆነ ጮቤ ይረግጣል። ወፊት ከፈጣሪ ዘንድ የተላከች መላክተኛ እንደሆነች ያምናል። ወፊትን ሰምቶ ዝም
አይልም። የሱ መልስ አለ ፦
"ነ ኩቾ ጠባያ፤
ነ ቡሾ ቅታያ፤
ሻትያነ ዬርን ግበነሆ -
ጎጆ ይስፋሽ
ጫጩት አይሙትብሽ
አዎን አልፈራም እግዚአብሔርን እታመናለሁ " ይላታል ።

✤ "ሻት፥ሻት፥ሻት፥ሻት - ፍራ፥ፍራ፥ፍራ፥ፍራ"
ይኸን ያለችው እንደሆነ ከወጣበት መንገድ ይመለሳል። ይፈራል።ያሰበው እንደማይሳካ እንደማይቀና ያምናል። ወፊት ይኽን
ያለችው እሱ ምንም ሳያስብ ከሆነም ምን ሊመጣብኝ ይሆን እያለ ይሰጋል።
ከላይ ያልነውን ብስራትም ሆነ መርዶ ወፏ እየደጋገመች፤ ሰውዬው እየተራመደ ከሆነም እየተከተለች የምትለው ከሆነ
ሰውዬው ነገሩ/መልዕክቱ/ትንቢቱ ለርሱ መሆኑንና ቁርጥ ፥ ዕሙን መሆኑን ያምናል።

ክፍል - ፪ ይቀጥላል......
__
* ካፎ - ወፍ = ባለ ብዙ ሕብረ ቀለምና ስብጥር ዝርያ(በዛውም ስብጥር ዝማሬ) ያላቸውን ትንንሽ ወፎችን ለመወከል የተነገረ
ነው።


**ሕብዝ = ልባዌ (Consciousness) ለሌለው ሕዝብ የሚቀጸል ለበጣ ። ምንጭ :ኢትኤል


ዕፀ ወርቄ(ወርቅ በሜዳ)
=======================
አጋንንት ለሚጥለው ይህችን እንደሲጃራ ማጨስ።
ለደም ብዛት እና ለስኳር ግማሽ ማንኪያ ዱቄቷን በማር መዋጥ።
ለሥራይም ከዋጊኖስ ጋር ትወሰዳለች ይላል የአበው መዝገብ። ታስቀምጣለች ሆድንም ታጠራለች።ለለምፅ ለተለያዩ መድሐኒት ግብአትም ናት @truth00011




በስመ አብ በል ጸሎት በእንተ አይነ ጥላ ወገርጋሪ ፡ ቆጅሽ ፡ ቆጅሽ ፡ ቆጅሽ ፡ ቆርሐሹ ፡ ቆርሐሹ ፡ ቆርሐሹ ፡ ሸርማሹ ፡ ሸርማሹ ፡ ሸርማሹ ፡ ኮርሸሹ ፡ ኮርሸሹ ኮርሸሹ ፡ አክሊስ ፡ መክሊስ ፡ አጥሊስ ፡ ፡ መጥሊስ ፡ አሊስ ፡ መሊስ ፡ ኦ ፡ እግዚእነ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡በኃይለ ፡ ዝንቱ ፡ አስማቲከ ፡ ዘአጠፋህከ ፡ ኃይለ ፡ ፅልመት ፡ ወፈትሐከ ፡ መዋህቅተ ፡ ዲያብሎስ ፡ ከማሁ ፡ ፍታሕ ፡ ማዕሠረ ፡ ሰይጣን ፡ ዘይትሜሰል ፡ አይነ ፡ ጥላ ፡ ወገርጋሪ ፡ አድክም ፡ ኃይሎሙ ፡ ወሠውር ፡ ጥበቦሙ ፡ አድህነኒ ፡ ሊተ ፡ ለገብርከ ፡ እገሌ፡፡ ይዐቅቡኒ ፡ ሚካኤል ፡ ወገብርኤል ፡ ሱራፌል ፡ ወኪሩቤል ፡ ዑራኤል ፡ ወሩፋኤል ፡ አፍኒን ፡ ወራጉኤል ፡ ወሳቁኤል ፡ ብርሃናኤል ፡ አጥልሻሻኤል ፡ ወያኑራኤል ፡ ቅምታኤል ፡ አድህኑኒ ፡ እም ፡ አይነ ፡ ጥላ ፡ ወገርጋሪ ፡ ጨምታፎስ ፡ ጨለምታፎስ፡ ገምታፎስ ፡ ገለምታፎስ  ፡ ይትፈታሕ ፡ ማዕሠረ ፡ እኩያን ፡ ቁራኛ ፡ ወተያያዥ ፡ አይነ  ጥላ ፡ ወገርጋሪ ፡ እምላዕለ ፡ ገብር፡፡ገቢሩ ፡ ዕፀ ፋርስ ፡ ቅጠል ፡ ላይ ፡ ፵፩ ጊዜ ደግሞ ፡ መታጠን ፡ ነው፡፡ አይነ ጥላ ያባርራል፡፡ ከዚያ ፡ በኋላ ፡ በቀይ ፡ ፅፈህ ፡ ያዝ ፡ ከአይነ ፡ ጥላ ፡ ይዐቅበከ ፡ይጠብቃል፡፡








ሰላም ለሁላችሁም ይሁን ውድ የትንሳኤ ዘኢትኤል መማማሪያ ተከታታዮች ወዳጆቼ የማከብራችሁ እንደምን አላችሁ ብርሀነ ልደቱን በሰላም አሳልፈን ፆሙን በበረከት በረድኤት ጎብኝቶን ለብርሀነ ትንሳኤው ደግሞ እንደቸርነቱ አድርሶናልና የአምላካችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን በእውነት እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በአሉ የሰላም የጤና የመደጋገፍ የመረዳዳት ይሁንላችሁ ።በፆሙም ከፆሙም ውጪ ቅር የተሰኛችሁብኝ ያስቀየምኋችሁ ሁሉ ይቅር እንድትሉኝ እናንተም ያስቀየማችሁትን ይቅር በሉ ያጠፋውትን ክሳለሁ በፀሎት አስቡኝ እግዚአብሔር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን


ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን
ሰቀሉህ ወይ 
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ
ሰቀሉህ ወይ /2/ 

የአዳም በደል አደረሰህ
አንተን ለመሰቀል 
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት
ቸሩ አባት/2/
አዝ
ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ
ብለህ ስለእኛ 
መሰቀል አሸክመው
አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ/2/ 
አዝ
እጅና እግርህን በብረት ተመታ
የዓለም ጌታ 
የሾህ አክሊል ደፍተህ
ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
አዝ
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው 
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ
አንተን ሊጎዱ/2/
አዝ 
በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል
ታላቅ በደል 
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው
ጠጣ ብለው/2/
አዝ
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ 
አንተ ይቅር በለን
በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ንሴብሖ

ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን /2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 

ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራም ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለም ቤዛ

ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆ እንደጠጣነው
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግነው
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


Репост из: ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
ክርስቲያኖች ሁላችሁ ኑ እናፅናናት

"ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። የተወደደ ልጇ በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር እንባን አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


Репост из: ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
"ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።"
(የሉቃስ ወንጌል 23:46)

"ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 27:50)

"ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።"
(የማርቆስ ወንጌል 15:37)

"ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ

ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
#አዝ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
#አዝ
አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም
#አዝ
እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

ሊቀ-መዘምራን
ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️


Репост из: ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት

በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ።

“ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)

Показано 20 последних публикаций.