ዉሸታሞች ሲበዙ የሚዋሹበት ነገር ራሱ ይደበላለቃል
የአቅል ፍርድ - ነገረ ተንታ
✍️
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ የመውሊድ ምግብ ተመርዞ አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ቁጥሩ ከፍ ያለ የመውሊዱ ተሳታፊ ደግሞ መመረዛቸውን በሶሻል ሚዲያ ላይ መንሸራሸሩ እንዲሁም የወንጀል ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው የመውሊድ ስነስርዓቱን ሲቃወሙ የነበሩ ግለሰቦች ናቸው መባሉን ተከትሎ የተለያዩ ግለሰቦች ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል ።
✍️
የመጀመሪያው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ "Mohammed Seid" የተባሉ ከተንታ ወረዳ አስተዳደር ሲሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ መዋጮ የተዘጋጀ የመውሊድ ፕሮግራም መሆኑን ገልፀው የችግሩ ምክንያት ደግሞ የታረደው በሬ ህመምተኛ መሆኑ አስረድተዋል ።
❶ ምክንያቱ የታመመ በሬ ነው ተብሎ ከተረጋገጠ ግለሰቦችን ማሰሩ ለምን አስፈለገ ?
❷ ከአካባቢው በስልክ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት የተቀቀለውን የበሬ ስጋ ብቻ የተመገቡ ተሳታፊዎች ምንም አይነት የመመርዝ ጉዳት ያላጋጠማቸው ሲሆን በአንፃሩ ተጠርጣሪ ግለሰቧ ባመጣችው ዘይት የተሰራውን ወጥ የተመገቡ ግለሰቦች መመረዛቸውን ነግረውናል ። ስለዚህ ጉዳዩ ከበሬው ስጋ ሳይሆን ከዘይቱ ነው ወደሚል ድምዳሜ ያደርሰናል ።
✍️
ሁለተኛው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጠው አቶ ሙሐመድ አባተ ሲሆን የመውሊድ ፕሮግራም እንዳልሆነ እና የመመረዙ ምክንያት ከተለያዬ ቦታ የተሰበሰበ ምግብ መሆኑን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት አረጋግጧል ሲል ፅፏል።
❶ መሐመድ አባተ ከወረዳው ጤና ጽ/ቤት አገኘሁ ያለው መረጃ ከወረዳው አስተዳደር መረጃ ጋር እንዴት ሊጣርስ ቻለ ?
❷ በመሐመድ አባተ መረጃ መሰረት የምግብ መመረዙ ምክንያት ከተለያዬ ቦታ የተሰበሰበ ምግብ ሲሆን የወረዳው አስተዳደር ደግሞ የታረደው በሬ የታመመ በመሆኑ ነው ብሏል ። እንዴት ?
❸ ሙሐመድ አባተ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ገልፆ የሞቱት ግን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው በአራተኛው ቀን ነው ያለ ሲሆን በአንፃሩ የወረዳው መስተዳድር ሁለቱ ግለሰቦች የሞቱት የህክምና ቡድኑ በአካባቢው ሳይደርስ ነው በማለት ገልጿል። ለመሆኑ ሙሐመድ አባተ አምባሳደር ሐሰን ታጁን ለመወንጀል በዚህ ልክ መዋሸት ለምን አስፈለገው ?
❹ መሐመድ አባተ ጉዳዩን ሁለት ሳምንት ያለፈው ነው በማለት ለማጣጣል ሞክሯል ። በዕርግጥ ከአሁን በፊት ሻሸመኔ ላይ በዕድሜ የገፉ የመጅሊስ አመራሮች በአፍላ ወጣቶች በቡጢ እና በካልቾ ሲነረቱ የሚያሳይ ቪዲዮ ሶሻል ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ወቅት ካሚል ሸምሱ "ጉዳዩ ወር ያለፈው ነው ፤ የመቷቸው አህባሽ መስለዋቸው ነው " ማለቱን አንዘነጋውም ። እንግዲህ የህግ ምሩቅ የሆነው ካሚል ሸምሱ ይህንን ካለ ጓደኛው ሙሐመድ አባተ ከዚህ የከፋ ቢናገር ገርሞ አይገርምም ።
✍️
ሶስተኛው በጉዳዩ አስተያየት የሰጠው ፕሮፌሰር ቃልኪዳን [Kha Abate] ሲሆን የችግሩ ምክንያት "በአረም መርዝ ዕቃ ዘይት ቀንሰው ወጥ ተሰራ" በማለት ፅፏል።
✍️
እንደ አጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የምግብ ምረዛው ምክንያት በማለት የተለያዩ ሶስት ምክንያቶችን አስፍረዋል ። ይህም በጉዳዩ ላይ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ከህግ ተጠያቂነት ለማስመለጥ የታሰበ ነገር ሊኖር ይችላል የሚል እሳቤን ያጭራል ። በመሆኑም የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በጉዳዩ ላይ ያለ ምንም ጫና ለሚዲያዎች ማብራሪያ ቢሰጡ እንዲሁም የወሃብያው ወገን በህግ አፈፃፀም ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ተደርጎ ተገቢውን የህግ ማስከበር ሒደት እንዲከናወን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ‼️