አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ወደ ክልል ወርደው የተሰሩ የትምባሆ ቁጥጥር ስራዎችን የመገምገም ተግባር ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡
ህዳር 26/2017 ዓ.ም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን እንደገና ለማደራጀትና በቀጣይ ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ለተለያዩ የፌደራል የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት የአስተዋወቀበትን መድረክ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በጋራ የሚሰሩ የትምባሆ ቁጥጥር ስራዎችን ክልል ድረስ ወርደው መጎብኘት እንዳለባቸው ጠቁመው ይህም ትኩረት ተሰጥቶ በቀጣይነት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የመንግስት ተቋማት በተለያዩ አደረጃጀቶች ምክንያት በመቀያየራቸውና ሰራተኞችም በተለያየ ምክንያት ስራቸውን ሲቀይሩ ከአስተባባሪ ኮሚቴው ሲወጡ በመቆየታቸው እንደገና ኮሚቴውን አዋቅሮና አጠናክሮ ማስቀጠል በማስፈለጉ መደረኩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይነት ኮሚቴው በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ መግባባት በመፍጠር አባላቱ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በተናጥል የጋራ መግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ እንደሚጠበቅ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል፡፡