ሕገ ወጥ የሥራ
አታባረው ነገር ግን እንዲለቅ አድርገው!
መርሕ
📌 አሰሪው ሥራውን ለማከናወን በሚያስችለው መንገድ ሁሉ ሠራተኛውን ከአንድ የሥራ ቦታም ሆነ የሥራ መደብ በማዘዋወር ማሰራትን የሚከለክለው ድንጋጌ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ዓ.ም ላይ የለም።
📌 በሕጉ ላይ ስለ ዝውውር በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ ከሌለ ድርጅቶች አንድን ሠራተኛ ከአንድ የሥራ መደብ ወይም የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ወም ቦታ ሲያዘዋውሩ መሠረት ሚያደርጉት በድርጅቱና በሠራተኞች መካከል የተደረገውን የሕብረት ስምምነት መሠረት በማድረግ ነው።
ዝውውር ሁለት ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ።
☝️ከአንድ የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ የሚደረግ ዝውውር
👉አንድን ሠራተኛ ይሰራበት ከነበረው የሥራ መደብ ወደ ሌላ የሥራ መደብ ቀድሞ ይከፈለው የነበረውን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ባልቀነስ ሁኔታ የሚደረግ ዝውውር ነው።
የደመወዝና ጥቅማጥቅም ለውጥ ካለ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ እንጂ ዝውውር ሊባል አይችልም።
✌️ ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ የሚደረግ ዝውውር
👉 አንድን ሠራተኛ በመደበኛነት ተቀጥሮ ይሰራበት ከነበረበት የሥራ ቦታ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ ቀድሞ ይሰራበት በነበረው የሥራ መደብ ይከፈለው የነበረውን ደመወዝና ጥቅማጥቅም ባልቀነስ ሁኔታ የሚደረግ ዝውውር ነው።
ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው ሚባለው መቼ ነው?
📌 ዝውውሩ የተደረገው የሠራተኛው መደብ ባልሆነ እና ተመሳሳይነት በሌለው የሥራ መደብ ከሆነ፤
📌 አሰሪው ሠራተኛውን ያዘዋወረው ለድርጅቱ ጥቅም ሳይሆን ሆን ብሎ ለመጉዳት በማሰብ ያደረገው ዝውውር እንደሆነ፤
📌 ሠራተኛው የተዘዋወረው በአሰሪውና በድርጅቱ መካከል ከተደረገው የሕብረት ስምምነት ውጪ እንደሆነ፤
📌 አሰሪው ሠራተኛውን አዘዋውሬሃለውኝ ባለበት ደብዳቤ ላይ ምክንያቱን በግልጽ ያላስቀመጠ እንደሆነ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ነው።
ምን ማድረግ ይጠበቅበዎታል?
📌 የዝውውር ደብዳቤው እንደደረሰዎት በዝውውሩ ያላመኑበት እንደሆነ ወዲያውኑ ክስ በማቅረብ ዝውውርዎትን ያሳግዱ፤
📌 ዝውውርዎትን በተመለከተ ለጊዜው ዕግድ ያልተሰጠ እንደሆነ ወደ ተዘዋወሩበት የሥራ መደብም ሆነ ቦታ በመገኘት በሥራ ገበታዎት ላይ ይገኙ፤ ምክንያቱም በተከታታይ 05 የሥራ ቀናት የሥራ ገበታ ላይ አለመገኘት ከሥራ ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት ለአሰሪው ከበቂ በላይ ምክንያት ይሆነዋልና።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ