መዶሻዉስ🤷♀
በፋኢዛ✍
አስተማሪ ነዉ ብዬ ያሰብኩትን የቅዳሜ ፅሁፍ አቅርቤላችሇለሁ
@mornin_bot ላይ ሀሳባችሁን አድርሱኝ፡፡
ዛሬ ቀኔ ነዉ ! ለህይወቴ መበላሸት ተጠያቂ የሆነዉን ክፉ ፣ አረመኔ ሰዉ ሲሞት የማይበት ያ በአሳደጉኝ እጆቹ አፍኖ ወንድነቱን የተወጣብኝ..፣ ያ ከልቤ ማይጠፋ ጥቅርሻ ሰቅጣጭ በደል የፈፀመብኝ ፣ ያ ከህይወቴ ላይ ሞቴን የቀዳልኝ ፣ አዎ የእናቴ ባል የእኔ አባት የሆነዉ ሴሰኛ ሰዉ ያ ሰዉ ሲሞት የማይበት ቀን ነዉ፡፡
ታዉቃላችሁ? ገና እንጭጭ ደ10 አመት ህፃን ነበርኩ ገና አፍላ ተጫዉቼ ያልጠገብኩ.....ልሙጥ ደረት ያለኝ .....ብቅ ያላለ ዳሌ የማይስብ ገላ ፣ በፍቅር ሚታቀፍ እንጅ ስሜት የሚያረካ ሰዉነት ያልነበረኝ ህፃን ...ምንም ክፉ የማላስብ ሜሉ ነይ ሲሉኝ የምሄድ
... ሜሉ ሂጅ ሲሉኝ የምመለስ አፍላ! አባቴን በጣም እወደዉ ነበር የመጀመሪያም የመጨረሻም ልጅ ስለነበርኩ መሬት አይንካሽ እያለ ይንከባከበኝ ነበር ....እማዬ ወደ ሰባት አመቴ እያለ በሞት ተለይቻትም ስለነበር አባዬ ሀገሬ ነበር ....ምን ዋጋ አለዉ! አባትነቱን ክዶ በልጅነት ገላዬ ተጫወተብኝ ! ደፈረኝ ! የወንድነት ርካሽ ፍሳሹን ሰጠኝ ፣ እማዬን አቅፎ የተኛበት አልጋ ላይ አፍኖ ስሜቱን ተወጣብኝ!!!
ዘበጥያ ከወረደ 14 አመት ከምናምን ወር አልፎታል ሊፈታ ጥቂት ቀርቶት ነበር ግን በቋፍ ዉስጥ ገብቶ ሞቱን መጠበቅ ከጀመረ አመታት ተቆጠሩ ፡፡ ዛሬ ፓሊሱ ደዉሎ የመጨረሻ ላየዉ እፈልግ እንደሁ ጠየቀኝ ....ላየዉ ወሰንኩ ያ ሴሰኛ ቆሻሻ ሰዉ ጣር ላይ ሁኖ ማየት ፈለኩ፡፡
"are you serious " ስትለኝ ከሰመመኔ ነቃሁ ፡፡ (ሊዱ ናት ጓደኛዬ እንድታካሂደኝ ጠይቄያት ነበር....)
"ሊዱ አስተያየት እንድትሰጭኝ አይደለም ወስኛለሁ አብረሽኝ መሄድ ከፈለግሽ ትችያለሽ ካልፈለግሽ ቻዉ!"
"Don't say it of course I will but, Oh God! " ( ከአማረኛ የነጭ ቋንቋ ይቀናታል )
ከቤት ወተን በራይድ ሄድን .....በሃሳብ እየዋለልኩኝ ከእስረኞቹ ሀኪም ቤት ደረስን፡፡ ፓሊሱ ከሩቅ ሲያየኝ መጣ ..." ሜሉዬ ተረጋግተሽ ግቢ ና አናግሪዉ " ብሎ ትካሻዬን ቸብ ቸብ አድርጎኝ አባቴ ወደተኛበት ክፍል ወሰደኝ ....አግሬ አልታዘዝ ሲለኝ ታወቀኝ ...ሁለት ትዝታወች በአንዴ ድርግም አሉብኝ ፡፡ አባዬ እያልኩ ስሮጥ ከእማዬ ሲከልለኝ .....ሜሉዬ የማናት ? ሲለኝ የአባቷ ስለዉ ...ስታድጊ ምርጥ ሞዴል ትሄኛለሽ የከቴ ልጅኮ ከመልአኮች የሚወዳደር መልክ አላት እያለ ድፍን ኢትዮጽያ ያወራል ሲለኝ ...አቅፎ ሲያስተኛኝ ......የዛ ቀን ማታ ?አባዬ ምንድን ነዉ እያልኩት ልብሴን ሲቀደዉ .... ሲደፍረኝ .....በደም ተጨማልቄ ስጮህ ...
"Are you sure ? Do you still want to meet that man ? "
አዎ ! አዎ ! ይሄን ማድረግ አለብኝ ሊዱ ( አየር ሰብስቤ በሩን ከፈትኩት )
አየሁት አዎ ያ ሰይጣን ከስንጥር ከስቶ ከክሰል ተቁሮ አልጋዉ ላይ ተኝቶ ፈገግ ብሏል ፡፡ ፈገግታው አንዳች ሰይጣን ጫረብኝ ...ህመሜ ተነሳ መሳደብ ጀመርኩኝ!
አንተ አረመኔ ዉሻ ሊዱ አየሽዉ ዛሬም ፈገግ ይላል ! ልትሞት ስትል እንኳን ምናለ እንደሰዉ ንሰሀ ብትገባ ?ምናለ ይቅርታ ብትጠይቅ? አዉሬ ነህ ጨካኝ ላሳደካት ለኔ የማትራራ ሴሰኛ ነህ ጡት በሌለዉ ደረት የምትቀነዝር ፣በህፃን ገላ የምትሻፍድ ሊያዉም በልጅህ! ( ፈገግ እንዳለ ያየኛል ፈገግታው ህመሜን ሲጭረዉ የምናገረዉ ይበዛል) ሙት ! ሙት ! አንተ አረመኔ ሙት አንተ ሴሰኛ ! ሙትት ....
እጁን ዘረጋዉ ነይልኝ አለኝ እንጃ ምን እንደነካኝ በደመነፍስ መሳደቤን አቁሜ እጄን ሰጠሁት ከጣሩጋር እየተሟገተ ያወራኝ ጀመር....." አለሜ አላረጀሽም ዛሬም ግን ቆየሽብኝ ኮ !እኔን እኮ አትሄድም ብለዉኝ ነዉ..... አንቺ ለምን ቀረሽ? አንችንም ከልክለዉሽ ነዉ ኣ ? እነዚህ አረመኔዎች ስለተራራቅን የምንረሳሳ መስሏቸዉኮ ነዉ ...አለሜ ልሞት ነዉ መሰል ፡፡ ብዙ ብጠብቅሽም ሳላይሽ እንዳይወስደኝ አንድዬን ለምኜዉ ነበር ፡፡እናትዬ ቀንሽ ሲደርስ ትከተይኛለሽ እወድሻለሁ እሽ ዉድድ ነዉ የማ ......" እጁ ተዝለፍልፎ ከጄ ወደቀ ጭንቅላቴ ከብዶኝ እኔም ወደኩ አባቴን ብከተለዉ ብዬ ተመኘሁ .......
ዛሬ የአባቴ ሙት አመት ነዉ ፡፡ አባዬ ከእማዬ ከተቀላቀለ አመት ሞላዉ፡፡ ከቀብሩ ላይ እስር አበባ ለማስቀመጥ ልሄድ ነዉ ከመሄዴ በፊት ግን ግራ የገባችሁን ታሪኬን ላስረዳችሁ ፡፡ እኔ በአባቴ ተደፍሬያለሁ አዎ ግን አባቴ እኔን አልደፈረኝም ፡፡ እማ ከሞተች በሇላ አባዬ በጣም ታሞ ነበር አለሜ ሚላትን ሚስቱን ስላጣ ከሀዘኑና ከበሽታው ለማገገም አንድ አመት ፈጅቶበት ነበር ግን ተሻለዉ ተብሎ ከመጣ በሇላ ብዙ ነገሮችን ይረሳ ነበር ልጅ ስለነበርኩ አላስተዋልኩትም ነበር ፡፡ አዎ አባቴ የአልዛይመር በሽተኛ ሁኖ ነበር ያን ቀን ምሽትም ልጁን አልደፈረም ሚስቱ ጋር ተኛ እንጂ ፡፡ የእስር ቤቱ ሀኪም ሊያገኘኝ ብዙ ቢጥርም ፍቃደኛ አልሆንኩለትም ነበር ...አዎ ለአንድ ቀን ጥፋቱ የአስር አመት አባትነቱን ክጄ አመታትን ስረግመዉ ኖርኩ ፡፡ አባቴ በበሽታዉና በሚስቱ ናፍቆት ሲሰቃይ ሞተ ፡፡ በህይወት እያለ እዉነታዉን ባዉቅ ተመኘሁ ግን አልፏል አባቴ ወደ አፈሩ ተመልሷል፡፡ ግን ለእናንተ ይሄን ልናገር ወደድኩ ሁሉም ሰዉ ሚስማር ለምን ጣዉላዉን ወጋዉ ይላል ሁሉም ለተወጊዉ ጣዉላ ያግዛል ፡፡ ግን እናስብ ከሚስማሩ በላይ መዶሻ አለ፡፡ አዎ የበዳይም ተበዳይ አለ !!!!
ጉዞ ጀምሬያለሁ በህይወት እያለ የረገምኩትን አባቴን አፈር ሁኖ አበባ ልሰጠዉ እናንተ ግን አስቡበት !!!!!
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@fikerdertogada1╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
For any comment
@mornin_bot ❥❥________⚘_______❥❥
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍
😍 Join
@faiza_kiza 😍
😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍