ፍቅሬን በ 4 መስመር:


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
ይቅርታዎን ፍቅሮን ሚስጥሮንና ፍላጎቶን እኛን በመቀላቀል በምናጋራቹ 4 መስመር ግጥሞች ሙሉ ስሜቶን ይግለጹ

️╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕╋▏|
#Just ዘና ፈታ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አንተ ለኔ አድርጎህ ልቤ ካልደረጀ
እንዳሰብኩት ሆኖ ኑሮዬ ካልበጀ
የጸለይኩት ጸሎት አንተን ካላመጣህ
እስኪ ልሳል ደሞ ከልቤ እንዲያሶጣህ
@fkren_be_4_mesmr


በገና ለገና ይሆን ይሁን እያልኩ
አንተን እንዳላጣ አይኖቼን ከጨፈንኩ
እንቅልፌን አጥቼ ሳልተኛ አድራለው
ካራራቀን ብዬ ህልሜን እፈራለው
@fkren_be_4_mesmr


ካንተ ጋር እያለው የምትሞቀኝ ጸሀይ
ላይኔ ጥሩ ሆኖ የሚታየኝ ሰማይ
አንተ ሳትኖር ጎኔ ላንተ እየወገኑ
ሁሉም ባዶ ይሆናል ከኔ ጋ ላይሆኑ
@fkren_be_4_mesmr


ትላንት አጥቼ ዛሬ አጊንቻለው
ብዙ ሰው እረስቶኝ እኔም ረስቻለው
እኔን የቸገረኝ የሆነኝ አበሳ
ያጣሁት መዳኒት አንቺን የሚያሥረሳ
@fkren_be_4_mesmr


ለልቤ መድሀኒት ያንተን ልብ ስሻ
ላኖርህ ሳልሽርህ እስከ መጨረሻ
ዳንኩ ስል ተነሳው አገገምኩኝ ካምና
ያንተም ጦር ሰበቀኝ ቆሰልኩ እንደገና
@fkren_be_4_mesmr


ሳልፈራ እንደ ልቤ በረርኩኝ በረርኩኝ
አንዱን እየለቀኩ አንዱን እየያዝኩኝ
አወይ የኔ ነገር የኔ መጨረሻ
ከኔው ቢጤ እንዳይሆን ልቡ ከማይረጋ
@fkren_be_4_mesmr


አካሌ እንዳልዛለ መስሎት እየኖረ
ልቤ እያዘነ ከፍቶት እያደረ
እየሳቀ ጥርሴ ባያስረሳኝ ኖሮ
አይሆንም ነበረ አይገፋም ኑሮ
@fkren_be_4_mesmr


ደና ነኝ እላለው መድከም የት አባቱ
ገደልኝ አልልም ሰበረኝ ናፍቆቱ
ልክ እንደ ጀግነ ሲዋሽልኝ አፌ
ደና ነኝ እላለው ፎቶህን ታቅፌ
@fkren_be_4_mesmr


ለሰው ማይወራ ሚስጥር እንዳልለው
እሷ እንዳታቅብኝ ከሷ እንዳልደብቀው
እንደተረታሁኝ ልቤ እንደ ደከመ
አይኔ ይናገራል ካፌ እየቀደመ
@fkren_be_4_mesmr


ናፍቆት ህመም ሆኖ አመመኝ በብርቱ
መከፋት ማዘኑ የቱ ይወራ ስንቱ
ህመም ማስያገሻ መዳኒት የሌለው
አወይ ናፍቆት ሞኙ ገድሎኝ እንዳያርፈው
@fkren_be_4_mesmr


የኔ ያልኩትን ሰው በፍቅር ያየሽው
እንደምን ብለሽ ሞትን ተመኘሽው
ማርያምን ብያለው ደግሜ አልምልም
እሱንማ ደፍረው ካዩብኝ አልምርም
@fkren_be_4_mesmr


ካደኝ ልቤ አንተን አንተን ይላል
ጉዴ ፈላ መልክህ ያታልላል
አታላዩን ውበት አጎናጽፎ
ስንቱን ጣለ ልቡናውን አልፎ
@fkren_be_4_mesmr


ማዶ ማዶ እያየ አይኔ ሊያይሽ ሳሳ
እንደራብሽኝ ዋልሽ ምነው ቀረሽሳ
ናፍቆት አንገብግቦ ካላዋለኝ ደጇ
የዛሬውስ አጀብ ማደሬንም እንጃ
@fkren_be_4_mesmr


ሆዴ ተረበሸ ፍቅርህ ትዝ እያለኝ
አይ ኑሮ ተስማማህ ወይ እስኪ ጠይቁልኝ
ጨነቀኝ ጠበበኝ ለማን ሰው ላዋየው
ሰው ካልደረሰበት እንደራሱ አያየው
@fkren_be_4_mesmr


ያሻው ቢያምር ቢጎላ መልኩ
አንቺ ነሽ ለኔ የልቤ ልኩ
ሚዛን የደፋሽ ለኩል ሚዛኔ
ሌላ እኔ አላይም አንቺ ነሽ የኔ
@fkren_be_4_mesmr


ስንቱን ነገር ቻልኩት ሲመጣ ካንቺማ
አይቼ እንዳላየው ሰምቼ እንዳልሰማ
ስታጠፊ በጀ አወይ የወደደ
ፍቅርሽ እያነጣኝ ሆዴ እየነደደ
@fkren_be_4_mesmr


ልብህ እንዳይመታ ሌላ ሄዋን ስታይ
እኔ ወድሀለው ከሚወዱህ በላይ
ከተመኙህ በላይ ካሉት አፈቀርንህ
የለም አትፈልግ እንደኔ ሚወድህ
@fkren_be_4_mesmr


የፍቅር ዳር ድረስ ልያዝህ አድርሰኝ
እስከድሜዬ ማምሻ ላፍታ ሳትለቀኝ
እስካሸልብ ድረስ ከማልነቃው እንቅልፍ
ያኑረኝ በፍቅር ዘላለም ካንተ እቅፍ
@fkren_be_4_mesmr


ለናፈቀ ደሞ አይንሽን ለሚሻ
ከሰመመን ሊድን ለመም ማስታገሻ
ቅርብ አደል አዳርሽ ቅርብ አደል ወይ ውሎ
ሳትነጠል ነፍሴ ድረሺልኝ ቶሎ
@fkren_be_4_mesmr


ልቤ ወዳጄ ሚስጥሬ ነበረ
ዛሬ እንዲ ሊከዳኝ አንተን ባፈቀረ
አንድ ያለኝ ወዳጅ ካሳጣከኝ አይቀር
ላፈቀረህ ልቤ አንተ ሁነው ሚስጥር
@fkren_be_4_mesmr

Показано 20 последних публикаций.

1 480

подписчиков
Статистика канала