Фильтр публикаций


#AASTU

የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ በማድረግ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው አለም አቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው እየሰራሁ ነው ያለው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፤ በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ እውቅና የማግኘት ሂደቱ ይጠናቀቃል ብሏል፡፡

ዩኒቨርስቲው በአለም አቀፍ መስፈርት ከልሼዋለሁ ባለው የትምህርት ሥርዓት ያስተማራቸው የመጀመርያ ዙር ተማሪዎችም አስመርቆ ወደ ስራ ማስገባቱንም ሰምተናል፡፡

#የአዲስ_አበባ_ሳይንስና_ቴክኖሎጂ_ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ደረጄ እንግዳ(ዶ/ር) ከ2019 ጀምሮ ዩኒቨርስቲው ይህን እውቅና ለማግኘት የሚያስችለውን ስራ ሲሰራ ነበር ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ማሳያነት ያነሱት የትምህርት ካሪኩለም ክለሳ ማድረግ አንዱ ሲሆን በዚህ ሥርዓት ያለፉ ተማሪዎች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ መመረቅ ጀምረዋል በማለት ነግረውናል፡፡

አለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ባለፈው ሳምንት ግምገማ የሚያካሄድ ቡድን መጥቶ ስራውን አከናውኗል ያሉት ደረጄ እንግዳ(ዶ/ር) በመጀሪያው ሪፖርታቸውም አብዛኛዎቹ የትምህርት ክፍሎች ይህንን እውቅና እንደሚያሟሉ ተነግሮናል ብለዋል፡፡

ነገር ግን አንዳንድ ስራዎች በአንድ ወር ውስጥ እንድናስተካክል ተነግሮናል ያሉት የአስቱ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዩኒቨርስቲው የተነሱ ችግሮችን ለማስተካከል እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

ውጤቱም ከ7 ወር በኋላ ሐምሌ ውስጥ ይታወቃል መባሉን ሰምተናል፡፡

እውቅናው ሲገኝ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የተመረቁ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የትምህርት ማስረጃቸው በየትኛውም ተቋም አለም አቀፍ ተቀባይነት ይኖረዋል ተብሏል፡፡

[ዘገባው የሸገር ራዲዮ ጣቢያ ነው]

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#DireDawaUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስዳችሁ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ ም መሆኑ ተገልጿል።

(በምስሉ የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን ይመልከቱ።)

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#BorenaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

ማሳሰቢያ

ጥሪ የተደረገላችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ስትመጡ፡-

➢ የ 8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ

➢ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያለዉን ትራንስክሪፕት ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ

➢ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ሰርትፊኬት ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ

➢ ስምንት (8) 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ

➢ አንሶላ፣ ብርድልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችዋል፡፡ ከተባለዉ ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን ይገልጻል።

የቦረና ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

━━━━━━━━━━━━━━━

Share with your friends
👇👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባዘጋጀው የ2025 #ነጻ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ለመሳተፍ ይመዝገቡ!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም በቅርቡ የተመረቁና ለስፔስ ሳይንስ ልዩ ፍላጎት ካለዎት፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ባዘጋጀው የሦስት ወራት #ነጻ የ Space Internship Program እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
እሑድ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ለሊት 6፡00

ምላሽ ኢሜይል ታህሳስ 14/2017 ዓ.ም የሚላክ ሲሆን፤ ቃለ-መጠይቅ ከታህሳስ 16-18/2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡

ለማመልከት 👇
https://telegra.ph/Space-Internship-Programme-2025-12-16

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት በሦስት ዓይነት አሠራሮች እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡

በመንግሥት ምደባ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የወጪ መጋራት ግዴታ እንደሚመለከታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አብዱ ናስር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዓይነት ተማሪዎች እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው፤ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን የሚችሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እና የወጪ መጋራት የሚመለከታቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎች ዝቅተኛው የትምህርት ቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ተማሪ የምግብ ወጪ መጋራት ሲሰላ 120,000 ብር እንደሚሆንና የሰባት ዓመት ቆይታ ያለው የሕክምና ትምህርት ደግሞ 210,000 ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት ተመን በየትምህርት ዘርፍ የዋጋ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ይህም በተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ቆይታ ስሌት መሠረት እንደሚሆን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 5,000 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን፤ 2,500 በራሳቸው ከፍለው የሚማሩና ወጪ መጋራቱ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ የተቀሩት 2,500 ተማሪዎች ደግሞ መደበኛው የመንግሥት ወጪ መጋራት የማይከመለታቸው ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 ብር እንዲሆን ተወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መላኩም ይታወቃል፡፡ #ሪፖርተር

https://t.me/fresh_handouts


#AAU

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን እና ማታ መርሐግብር የመልሶ ቅበላ (Re-admission) አመልካቾች ለ2017 ሁለተኛ ሴሚስተር የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ጊዜ የመጀመሪያ ዙር ከታህሳስ 7-11 2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የሁለተኛው ዙር የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ጊዜ ከታህሳስ 14-18/2017 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።

የመልሶ ቅበላ መጠየቂያ ቅፅ ለመሙላት፦

portalaau.edu.et ላይ መለያ ቁጥር (User name) እና ሚስጢር ቁጥር (Password) በመጠቀም Withdrawal ለመሙላት Registration > Withdrawal Request ይሙሉ።

➫ መለያ ቁጥር እና ሚስጢር ቁጥር በመጠቀም Readmission ለመሙላት Registration > Re-admission Request ይሙሉ።

የመልሶ ቅበላ ቅፅ መሙላት የሚቻለው ከላይ የተጠቀሱትን የኦንላይን ፎርም ሲሞሉ ብቻ ሲሆን፤ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ዲግሪ የመልሶ ቅበላ ቅፅ ለመሙላት ሲሔዱ ስፖንሰር ከሚያደርግዎት ተቋም በቅርብ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማያያዝ ያስፈልጋል፡፡

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን እንደሚከናወን ገለፀ፡፡

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባ በአስተዳደሩ ስር በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ በቢሮው የትምህርት ምዘናና ፈተና ማስተባበሪያ ገልጿል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከታህሳስ 7-30/2017 ዓ.ም ይከናወናል ተብሏል፡፡

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


በአማራ ክልል የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ የፊታችን ሰኞ ይጀምራል፡፡

በክልሉ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ምዝገባ ከታህሳስ 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሔድ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#HaramayaUniversity #Remedial

በ2017 ዓ.ም. በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ2017 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች በጥር 02፣ 03 እና 04፣ 2017 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ በአካል ተተኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው ገልጿል።

#ማሳሰቢያ
1ኛ. የህብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቨተርነሪ (Veterinary) ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ (Technology) ካምፓስ ሪፖርት የምታደርጉ መሆኑን እናሳውቃለን።

2ኛ. ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ትምህርት ያጠናቀቃቸሁበትን ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ከፍል ሰርትፍኬት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ 4 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ጉርድ ፎቶ እንዲሁም በማስታወቂያው የተጠቀሱ የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ይዛቹህ እንድትሄዱ ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳስቧል።

ተማሪዎች የዶርም ምደባችሁን ከዩንቨርሲቲው ዌብሳይት (www.haramaya.edu.et) ላይ በመግባት መለያ ቁጥራችሁን ተጠቅማቹህ መመልከት ትችላላቹህ።

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#WachamoUniversity #Remedial

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሸያ ትምህርት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፣

👉ለመደበኛ Remedial ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

⚡️በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

👉በግል ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

💥ለምዝገባ ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ፣ 3*4 የሆነ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፤

• የካምፓስ ምደባ በሚመለከት ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሠረት ይሆናል።


⚡️Natural Science

✓ስማቹህ A to G የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
✓ስማቹህ H to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

⚡️Social Science

✓ስማቹህ A to J የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
✓ስማቹህ K to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

(ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ)

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

"ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ለታህሳስ 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደጠራ" ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

ለጊዜው ምንም አይነት ጥሪ አለመተተላለፉን አውቃችሁ፣ በይፋ ጥሪ እስከሚደረግ ድረስ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


#MoE

በወጥነት ይተገበራል የተባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሜኑ ምን ይመስላል ?

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑም ሁሉም ጋር ወጥ እንዲሆንብ እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለጹ አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎ ፤ የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል።

የምግብ ሜኑው ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ መዘጋጀቱን የገለጸው ሚኒስቴሩ ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል እንዳለባቸው ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ለዩኒቨርሲቲዎች በተላከው የምግብ ሜኑ ከላይ የተያያዘ ሲሆን ፦

👉 ቁርስ ላይ ፦ እንጀራ ፍርፍር / ሩዝ + ዳቦ + በሻይ ፣ ቅንጬ ፣ ስልስ ፣ ማካሮኒ ተካተለዋል።

👉 ምሳ ላይ ፦ ምስር/አተር ክክ/ሽሮ / አተር / ባቄላ / ድንች / አትክልት ማለትም ጎመን ፣ድንች፣ ካሮት የመሳሰሉ / ፓስታ /  + እንጀራ / ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪም በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

👉 እራት ላይ ፦ ምስር/ክክ/ፓስታ / ሽሮ + በእንጀራ/ዳቦ ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሳምንት 1 ቀን ስጋ በምስር/በድንች/ በክክ (በዳቦ ወይም በእንጀራ) ተካተዋል።

🔵 ለበለጠ መረዳት ከሰኞ እስከ እሁድ የተከፋፈለውን የምግብ ሜኑ ከላይ መመልከት ይቻላል።

አጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲዎች በላከው የምግብ ሜኑ መሰረት ለቁርስ ፣ ለምሳ፣ ለእራት ለአንድ ተማሪ የተመደበው 100 ብር ነው።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሽፍን ባለመቻሉ መንግሥት በፊት የነበረውን ዕለታዊ የተማሪ ምግብ ወጪ 22 ብር ወደ 100 ብር ከፍ አድርጎታል።

(በትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ሰርኩላር ከላይ ተያይዟል)

#TikvahEthiopia

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts




#MoE

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ ተጣለባቸው፡፡

ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች የሽልማትና ዕውቅና መርሐግብር በዚህ ወር መጨረሻ ይካሔዳል፡፡

መርሐግብሩ ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የሽልማት ድርጅቱ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ጫኔ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች፣ ባለተሰጥኦ ተማሪዎች፣ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስፈትነው ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ምስጉን መምህራን ዕውቅና ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡

በመርሐግብሩ ውጤታማ ተማሪዎች እንዲሁም ለትምህርት እድገት ጉልህ ሚና የተጫወቱ ግለሰቦች፣ ተቋማትና ድርጅቶችን ጨምሮ 50 ለሚሆኑ አካላት ዕውቅና ይሰጣል ተብሏል፡፡

የሽልማት ፕሮግራሙ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር  በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑን ሰመተናል።

የሽልማት ዘርፎች

- ለዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች
- ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ከፍተኛ ነጥብ ያመጣች ሴት ተማሪ እና አካል ጉዳተኛ ተማሪ
- 100% ወደ ዩኒቨርሲቲ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
- በኮሚቴው መለኪያ ያለፉ በጀነሬሽን ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች
- ምርጥ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ሦስት)
- ምስጉን መምህራን (ሦስት)
- ባለተሰጦኦ ተማሪዎች
- የፈጠራ ባለቤቶች (ሦስት)
- በትምህርት ልማት የተሳተፉ አምስት ባለሃብቶች
- ለትምህርት ዕድገት የላቀ ሚና ለተወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማት (ሦስት)
- የህይወት ዘመን ተሸላሚ በተለያዩ ዘርፎች
-  ልዩ ተሸላሚ

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


የመጀመሪያው ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ ነው ‼️

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት” (Ethiopian National Students' Award) በትምህርቱ ዘርፍ በአዋጅ የተቋቋመ በሀገራችን ብቸኛው እና የመጀመሪያው ብሔራዊ የትምህርት የሽልማት ድርጅት ነው። ድርጅታችን በትምህርት ላይ መስራት የተቋቋመለት ዋና ዓላማ ሲሆን በሀገራችን ብቸኛ እና የመጀመሪያ የሆነውን “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት” ዓመታዊ ፕሮግራም በወርሃ ታህሳስ 2017 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ብቁ ተማሪዎችን በመሸለም የሚጀመር ይሆናል፡፡

የዚህ ሽልማት ትልቁ ዓላማ ውጤታማ ተማሪዎችን እና ምስጉን መምህራንን መሸለም፣ በመማር ማስተማሩ ምሳሌ የሆኑ የመንግስትና የግል የትምህርት ተቋማትን እውቅና መስጠት፣ ለሀገራችን የትምህርት ልማት ሁለንተናዊ ለውጥ አስተዋጽኦ በማድረግ ለትውልድ አርኣያ መሆን የቻሉ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች እውቅና የሚያገኙበት ዝግጅት ነው፡፡

ስለሆነም በሚዲያው ዘርፍ ውስጥ ላላችሁ ሁሉ ዕረቡ ታህሳስ 2/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገነተ ልዑል አዳራሽ ዝግጅቱን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት ከጠዋቱ 3፡30 በምንሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ተገኝታችሁ የዜና እና የፕሮግራም ሽፋን ትሰጡልን ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ (የሽልማት ድርጅቱ)

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts


የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ተደረገ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስቴር የፃፉት ደብዳቤ 👇

< ከመ/ቤታችሁ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 1/143/150/17 በተጻፈ ደብዳቤ አሁን በስራ ላይ ያለው የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ አኳያ ተማሪዎችን ለመመገብ በቂ ባለመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት በማካሄድ የተመን ማሻሻያው እንዲፈቀድ መጠየቃችሁ ይታወሳል:: የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መስሪያ ቤታችሁ ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ዩኒቨርስቲዎች አንዲጠቀሙበት እና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ክትትል እንድታደርጉ በጥብቅ አስታውቃለሁ፡፡ >

https://t.me/fresh_handouts
https://t.me/fresh_handouts

Показано 20 последних публикаций.