Shaday


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Религия


👉 የስነ-ፆታ (sexual )
👉 ወሲባዊ ንፅህና
👉 የእጮኝነት
👉 የትዳር
👉 ወጣት ተኮር ጉዳዮች ይዳሰሳሉ
እንዲሁም ሕይወት ቀያሪ ድንቅ ትምህርቶችን ያገኙበታል

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций










እውነት ስሙት ከጥቂት ቀናት በኋላ በአዲስ ትምህርት እመጣለሁ




ሰላም እንደት ናችሁ የምወዳችሁ
ላለፉት 5 አመታት በዚህ ቻናል በትምህርትና በጹሑፍ በመድከም እና አንዳንዴም በመጥፋት እናንተ በብዙ ትግስት እና በመጠበቅ ከጎኔ ሆናችሁ እስካሁን ድረስ ቆይታችሃል በጣም አድርጌ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ተባረኩልኝ እስካሁን ከነ ድካሜ ስላመናችሁኝ ስለተቀበላችሁኝ ጌታ ዘመናችሁን ይባረክ እላለሁ

እናንተ በርካቶቼ ናችሁ እንኳንም አወኳችሁ ❤

ወንድማችሁ ቸሬ ነኝ








❓❓😟ለምን ተበሳጨች??

󾠬እውነት ነው ፤ ብዙ ጊዜ ወንዶች ሴቶቻቸው ለምን እንደሚበሳጩ ማወቅ ይሳናቸዋል፡፡
❓❓ለምን ❓❓

👉ሴቶች በፍጥረታቸው ውብ ፣ ማራኪ ፣ መስህብ ያላቸው እና ሌሎች መልካም ነገሮች ብቻ አይደሉም፡፡
ይልቁንም በአብዛኛው ውስብስብ ፍጥረቶች ናቸው ፡፡

👉አንዳንድ ጊዜ በተለይም ምንም ባልተጨበጠ ነገር ሲበሳጩ እነሱን መረዳት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

✨ወንድ ሚስቱ ወይም ፍቅረኛው ስትበሳጭ ማድረግ የሚችለው በጣም የተሻለ ነገር ከራሷ ጋር ጊዜና ቦታ አንዲኖራት መተው ነው፡፡

ይህም ሲባል ለረዥም ጊዜ ወይም ቀኑን ሙሉ መዝጋት ማለት አይደለም፡፡ በፍፁም❕
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ለብቻዋ ተዋት ከዛም ተመለስና እሷ በምትወደው መልኩ ፍቅርህን አሳያት ፡፡

ከዛም ራሷ"ምን እነደነካኝ አላውቅም ፡፡ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት ተበሳጭቼ ነበር፡፡ አሁን አንተ ስላለህልኝ ተረጋጋሁ፡፡" ልትልህ ትችላለች፡፡

👉ይሄን መንገድ መጠቀም ካልፈለግክ ፤ በቃ መፍትሔ ፍለጋ ቢያንስ 12 መፅሃፍትን📚📚 ማገላበጥህ ነው፡፡

󾠬እዚጋ አንድ ምክር ፦ አልበርት አንስታይንም ቢሆን ሁሉም ወንዶች ሴቶቻቸውን መረዳት የሚችሉበት አንድ ጥሩ ቀመር ሊያዘጋጅ አይችልም፡፡
👉አሁን አሁን ሁሉም ፈላስፎች እና ሳይንቲስቶች በዚህ በእግዚአብሔር ቃል እየተሰማው መጥተዋል፦
💥"ሚስትህን እስከ ሞት ድረስ ውደዳት እናም ቀሪ ዘመንህን በደስታ ኑር፡፡" አራት ነጥብ፡፡💯

💮" ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-26)

  


ጌታ እኮ መልካም ነው
በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ጌታ መልካም ነው


‎      #እንዴት_የፍቅር_ጥያቄ_ላቅርብ?
‎
‎➥ የሚለው ጥያቄ ትልቅ ጭንቀት የሚፈጥር ጉዳይ ነው። እንደ አማኝ፣ ጥያቄው ከስሜታዊነት ባለፈ "ክብርንና ቅድስናን" የተላበሰ መሆን አለበት።
‎
‎1. #ቅድመ-ዝግጅት (የመሠረት ሥራ)
‎ጥያቄውን ከማቅረብህ በፊት ልብህና ሐሳብህ የጠራ መሆን አለበት።
‎
‎✅ #ጸሎት፦ "ጌታ ሆይ፣ ይህች ልጅ ለሕይወቴ ረዳት ትሆን ዘንድ ፈቃድህ ነው?" ብለህ ጠይቅ። ስሜትህ ብቻ ሳይሆን መንፈስህም ሰላም ሊኖረው ይገባል።
‎
‎✅ #ምልከታ (Observation): ልጅቷ ለመንፈሳዊ ሕይወት ያላት ፍቅር፣ ለቤተሰብ ያላት አክብሮትና ያላችሁን መግባባት በጥንቃቄ አስተውል።
‎
‎✅ #ምሳሌ፦ እንደ አንድ አናጺ አስበው። አናጺው ወንበር ከመሥራቱ በፊት እንጨቱ ጠንካራ መሆኑንና መሣሪያዎቹ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል። አንተም "ትዳርን" አልመህ የምትጀምር ከሆነ መሠረትህ የጸና መሆን አለበት።
‎
‎2. #ቦታና_ሰዓት_መምረጥ:-የፍቅር ጥያቄ የሚቀርብበት ቦታ ግርግር የበዛበት ሳይሆን፣ ሁለታችሁም በነፃነት የምትነጋገሩበት ጸጥ ያለ ስፍራ መሆን አለበት።
‎
‎✅ #ምክሩ፦ ቤተክርስቲያን አካባቢ ያለ ግቢ፣ ጸጥ ያለ ካፌ ወይም በእግር እየተጓዛችሁ የምታወሩበት መንገድ ይመረጣል።
‎✅ #ታላቅ_ማስጠንቀቂያ፦ ጥያቄውን በቴክስት (Text) ወይም በስልክ ከማቅረብ ይልቅ፣ በአካል ተገናኝቶ መነጋገር ለልጅቷ ያለህን ክብር ይገልጻል።
‎
‎3. #አቀራረብ (ቃላትን መምረጥ)
‎ጥያቄህ ግልጽ፣ ትሑትና መንፈሳዊ ይዘት ያለው ይሁን። "እወድሻለሁ" ከሚለው ቃል በስተጀርባ "ዓላማ" እንዳለህ አሳይ።
‎
‎         #የአቀራረብ_ዘዴዎች ፦
‎
‎ሀ. #ቀጥተኛና_መንፈሳዊ_አቀራረብ፦
‎"እከሊት... ላለፉት ጊዜያት ካለን ወዳጅነትና ካየሁት በጎ ማንነትሽ የተነሳ በጣም አከብርሻለሁ። ስለ እኛ ግንኙነት ስጸልይ ቆይቻለሁ፤ ወደፊት በሕይወት መንገድ ላይ አብረን እንድንጓዝ (ለትዳር እንድንታጭ) ፍላጎቴ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ብታስቢበትና ብትጸልይበት ደስ ይለኛል።"
‎
‎ለ. "#ከጓደኝነት_ወደ_ፍቅር" አቀራረብ፦"ከአንቺ ጋር ማውራትና ጊዜ ማሳለፍ ለእኔ ትልቅ ሰላም ነው። ይህ ጓደኝነታችን ወደ ጥልቅ የፍቅር ግንኙነት ቢያድግና ለወደፊት ሕይወታችን መሠረት ቢሆን ደስ ይለኛል። ለአንቺ ያለኝ አክብሮት ትልቅ ነው፣ ያንቺ ሐሳብ ምንድነው?"
‎
‎        ➥ #ወሳኝ_ምክሮች (Tips for Success)
‎✅ ለ"#አይ" ምላሽ ተዘጋጅ፦ ልጅቷ "አልፈልግም" ወይም "ገና ነኝ" ካለችህ፣ አትቆጣ ወይም አትቀየም። "እሺ፣ ስለነገርሽኝ አመሰግናለሁ፣ ጓደኝነታችን ግን ይቀጥላል" ብለህ በክብር ተቀበል።
‎✅ #አታጣድፋት፦ ጥያቄውን እንዳቀረብክ ወዲያውኑ መልስ አትጠብቅ። "ጸልዪበትና አስቢበት" ብለህ ጊዜ ስጣት። ይህ አንተ "ብስለት" እንዳለህ ያሳያል።
‎✅ #ክብርሽን_ጠብቅ፦ ጥያቄውን ስታቀርብ የምትናገረው ቃል "የምርከኛ" ሳይሆን "የወንድ" (የመሪ) ይሁን። በራስ መተማመንህና ትሕትናህ ተደምሮ ማራኪ ያደርግሃል።
‎
‎➥ #ማጠቃለያ፦ፍቅርን መጠየቅ ኃጢአት አይደለም፤ ነገር ግን አጠያየቁ እንደ ክርስቲያን ወጣት ጨዋነትና ክብር የተሞላበት ሊሆን ይገባል። ማማዬ ጋር ያለህ ግንኙነት ላይ እንዳየነው፣ ግልጽነት ለፍቅር ሕይወት መድኃኒት ነው።
‎
‎➥ ጨርሰሃል አሁን እሰኪ #share አድርግ
‎
‎እኔን ለማግኘት የሚትፈልጉ #inbox አድርጉልኝ
‎       @Chere2013
‎👇👇 #follow_and_join_us 👇👇
‎@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday


አወይ ፈተናዬ

ቅዳሜ አመሻሽ ላይ ነው ድብርቴ ከሌላው ቀን ይልቅ እጅጉን ልቋል:: ከጊቢያችን ውስጥ ከዋናው መኖርያ ራቅ ብላ በምትገኘው ክፍሌ ከቴሌቪዥናችን ፊትለፊት ሪሞተር ጨብጬ ከስጋዬ ጋር እየታገልኩ ነው:: ብቻዬን ስሆን እንዲህ አይነት ፈተና ብዙ ጊዜ ይገጥመኛል::ለእኔ ይህ አዲስ አይደለም ብዙ ጊዜ ተሸንፌበታለሁ አምላኬንም አሳዝኜበታለሁ::በዚህ ችግሬ ምክንያት ውሎዬ እና አዳሬ በሰው የታጀበ እንዲሆን ጥብቅ መሻቴ ነው:: በእጄ ከፍርሀቴ የተነሳ የሙጥኝ ብዬ የያዝኩት የቴሌቪዥን መቆጣጠርያ ሪሞት አንደበት ኖሮት ቢናገር የእኔን ጉድ ከማንም በላይ ያወራችሁ ነበር:: ብዙ የሚስጢር  ኮዶችን  እንዳስገባሁባት ከእኔ እና ከሪሞተሯ በስተቀር ማንም የሚያውቅ የለም:: ብዙ ስጋዊ ነገሬን የሚያነሳሱ የተሌቪዥን ቻናሎችን ሞልቼበታለሁ:: ታድያ ዛሬ ቤት ማንም ስለሌለ ይህን ቻናል ከፍቼ ልመልከት አልመልከት በሚል እሰጣ ገባ ውስጥ እያለሁ ከመቅፀብት ጣቶቼ ከቁጥጥሬ ውጭ በመሆን የሪሞተሩን ቁልፎች ተጫኑ:: ወዲያው በስክሪኑ ላይ በብዥታ ምስል ፊታቸው ተሸፍኖ ልቅ የሆነ ወሲብ የሚፈፅሙ ጥንዶችን ተመለከትኩ :: ምስላቸውን መመልከት ስጀምር አንዳች ነገር ሊሰርቅ እንዳቀደ ሰው ግራ እና ቀኜን ዞር ዞር ብዬ አየሁ:: ረዘም ላለ ሰዐት መመልከት እንድችል ግን ግዴታ ወጣ ብዬ የክፍሌን ዙርያ ማየት እና ሰው እንደሌለ ማረጋገጥ አለብኝ:: ዛሬ ቤት ማንም ባይኖርም የዘውትር ቅድመ ሁኔታዬ ስለሆነ አረጋግጬ በእግሬ ጣት ቀስስ ብዬ ወደ መቀመጫዬ ተመለስኩ::ቪዲዮውን መመልከት ስጀምር ድንገት ሰውነቴ በክፋት ሲወረር ተሰማኝ:: በሰመመን የክፋትን አለም አሰስኩ::
ይህ ለእኔ ትልቅ ፈተና ነበር::ሰውነቴ በሙሉ አይን አውጥቶ የእርቃነ ስጋቸውን ምስል እየቀረፀ አዕምሮዬ ውስጥ ሲያከማች ይታወቀኛል:: ግማሹ እኔነቴ የማደርገውን ነገር ቢቃወም ግን የማቆሙን ሐይል አጣው:: ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ጨርሼ ከክፍሌ ወጣሁ::በዚች ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ግን ብዙ ምስሎችን በጭንቅላቴ ስዬ ነበር።ይህ ምስል ምስል እለት እለት ብዙ ፈተና ያመጣብኝ ነበር።የዛሬው ድርጊቴ የመጀመርያዬ አይደለም። ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስሆን ማከናወን የሚቀናኝ ይህ ነው።ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ስቀላቀል ብዙ ነፃነት ተሰማኝ የሁል ጊዜ ተግባሬ ይህን የወሲብ ፊልም ማየትና ራሴን በራሴ ማርካት(masterbation) ሆነ። በዚህ ተግባሬም በጣም ብዙ ፀፀት እሸምት ነበር።
ብዙ ጊዜ ይህን ተግባሬን ለመተው ሞከርኩ ነገር ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም ከሳምንት በኋላ ተመልሼ እዛው እገኛለሁ።የእኔ ትልቁ ችግር ፖርኖ ማየት ብቻ ሳይሆን በቪዲዮው ላይ ያሉ አክተሮች አለባበስ አሳሳቅ እና የእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ምስል ቀንቀን ት/ቤት ውስጥ የማያቸውን ሴቶች ያለማቋረጥ በመጥፎ እይታ እንድመለከታቸው ማድረጉ ጭምር ነው።አጭር ቀሚስ የለበሰች ሰውነቷን ጥብቅ አድርጎ የሚይዝ ልብስ የለበሰች ሴት ለእኔ እርቃኗን ሆና ነው የምትታየኝ።አይኖቼ ልብሷን አውልቀው መላ አካላቷን ፍንትው አድርገው ውስጤ ያስቀምጣሉ።እነዚህን እህቶች እያሰብኩ ደግሞ ማታ መጥፎ አለም ውስጥ እገባለሁ።
ፀፀት እና እራሴን መጥላት የሁልጊዜ ተግባሬ ነበር።
"ጌታ ሆይ እርዳኝ።"
"ይቅር በለኝ።"
ሁል ጊዜ እላለሁ ነገር ግን ተመልሼ እራሴን እዛው አገኛለሁ።ምክንያቱ ደግሞ ፅኑ የውሳኔ ሰው አለመሆኔ ነበር።

      እንደ ዮሴፍ እንድሆን እርዳኝ!!

መፅሐፍ ቅዱስ አንብቤ አላውቅም ነበር።አንድ ቀን ታድያ በምን አይነት አጋጣሚ እንደሆነ ባላውቅም [እውነት ለመናገር ካለሁበት ስቃይ ለመላቀቅ ስል ነው] ከዘፍጥረት ጀምሮ ማንበብ ጀመርኩ።ታድያ በጥልቀት እያጠናው ባልሔድም ስለ ሰው ልጅ ክፋት እና ስለ እግዜአብሔር ምህረት አስተውያለሁ። እንደ ዮሴፍ አይነቱን ታሪክ ማንበቡ አቋሜን ማስተካከል እንዳለብኝ እረድቶኛል። ሴይጣን ደግሶ እና ሁሉንም ነገር አመቻችቶ አቅርቦለት ዮሴፍ እምቢ ብሎ መሸሹ እንደ እኔ አይነቱ ከሰይጣን ጋር አብሮ የመቀበርያውን ጉድጓድ የሚቆፍር ምንኛ ሞኝ እንደሆንን አሳየኝ።
እለት እለት ይህን የዮሴፍን ሽሽት ማሰላሰል ትልቅ ብርታት ሆኖኝ ከነበርኩበት ስቃይ ተላቅቄ አለሁ። ከምንም በላይ ከዚህ አይነት ስቃይ ሊያላቅቅ የሚችል የእግዜአብሔር ፀጋ ብቻ ነው።
           
✅                    ይቀላቀሉን          


የሰላም


" ዳግማዊ ድንግልና "

✨ ድንግልናሽን አጥተሽ ከሆነ በዚህ ነገር ተስማምተሽ እረፊ ምንም ነገር ድንግልናሽን ሊመልስልሽ አይችልም፡፡

👉 ስለዚህ ህይወትሽን ወደፊት ቀጥይ፡፡
ድንግልናሽን የወሰደው ወንድ ካቆመበት ሊቀጥል ተመልሶ ይመጣ ይሆናል ፤ ነገር ግን አትፍቀጂለት ፡፡

👉የተበታተነውን ህይወትሽ ሰብስቢና ልክ ድንግል እንደነበርሺበት ጊዜ መኖር ጀምሪ፡፡

👉sexually ንፁህ የሆነ ህይወት ምሪ በዚህም የእግዚአብሔርን ምህረትና ፀጋ በራስሽ ህይወት ፈትነሽ ታውቂያለሽ፡፡

ማንም ወንድ ከተማው ላይ  ካሉ ድንግል ሴቶች አብልጦ አንቺን ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ህይወትሽን sexually ንፁህ በማድረግ አስደስተሺዋልና ነው፡፡

⏩ መፅሀፈ ሩትን አንብቢ፡፡ እሷ በመጀመሪያ  የኑሀሚንን ልጅ አግብታ ነበር፡፡ ድንግል እንዳልነበረች መናገር አይጠበቅኝም፡፡
ግን ባሏ ሞተ ፡፡

✨ነገርግን ሩት በከተማው ውስጥ ሁሉም ደናግላን የሚመኙትን ታዋቂ ባለጠጋ ሰው ልብ ሰረቀች፡፡

👉አየሽ " #ዳግማዊ_ድንግልና " የሚባል ነገር አለ፡፡ ይኸውም ንስሃ በገባ የህይወት ምልልስ የሚመጣ ነው፡፡ 💯

የመጨረሻ ነጥብ 👇

sexually ንፁህ ህይወት የሚኖርሽ ድንግልናሽን የወሰደው ወንድ ተመልሶ ስለመጣ አይደለም፡፡

👉ከእሱ ጋርም ሆነ ያለእሱ ንፁህ የሆነ ህይወት ይኑርሽ፡፡

                      #single

👇👇👇👇👇   👇👇👇👇👇
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!


እጮኝነት የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች

🔴ቅድመ ጋብቻ የግብረ ስጋ ግንኙነትን መፈጸም

ወጣቶች በእጮኝነታቸው ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት በአካል እድገት
ለውጥ የተነሳ ከፍተኛ የሆነ የወሲብ ፍላጎት አላቸው፡፡ በዚህ ምክንያት
በእጮኝነታቸው ወቅት በፍቅር መያዝ፣ተቀጣጥሮ የሚያውቃቸው ሰው
በሌለበት ቦታ ላይ መገናኘት፣ወደ ወንዱ እጮኛ ቤትመሄድ፣አልፎ
አልፎም መተቃቀፍ፣የመራቢያአካላትን መነካካት፣የከንፈር መሳሳም;
የመሳሰሉትን ነገሮች በማድረግ የወሲብ ስሜትን ለማርካት ጥረት
ማድረግ በብዙ እጮኛሞች መካከል የሚታይ ሐቅ ነው፡ የቅድመ ግብረ
ስጋ ግንኙነት ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ወጣቶች ይፈተናሉ ብሎ
መናገር ይቻላል፡ አንዳንዶችም ይህን ከፍተኛ ፍላጎት መቋቋም
አቅቷቸው በዝሙት ፈተና ላይ ይወድቃሉ፡፡ ይህን ድርጊት ከበደ በከሬ
እንዲህ በማለት ያስቀምጠዋል፡፡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የቅድመ
ጋብቻ የወሲብ ግንኙነትም ኃጢአት ነው(የሐዋ 15፡20፣1ቆሮ6፡9፣
13፣18፣7ላ5፡19 ፣ቆላ3፡5፣1ተሶ4፡3)፡ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ወደ
ፊት እንጋባለን _ ምንም _ አይደለም ብለው ከጋብቻ በፊት ወሲብ
መፈጸማቸው ለአሁንም ሆነ በወደ ፊት የትዳር ሕይወታቸው ላይ
አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ይላል፡፡6

በዚህ ምክንያት የወደቁ እጮኛሞች ክብረ ነጽህናቸውን ከሰጡ በኋላ
በወንዶች በኩል የመጋባት ፍቅራቸው እየቀነሰ በመምጣት
የነበረው ከፍተኛ ናፍቆት ውሳኔ እየተራዘመ ወደ ፊት ይሄዳል፡፡ ይህ
ነገር የሚያሳየው የጋብቻው ሁኔታ ከፊቱ ላይ ቀይ መብራት የበራበት
መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን የሚጠቁም ነገር ነው፡፡ እንዲሁም
በመቀጠል በወንዱ ወይም በሌቷ በኩል ለማግባት ፍቃደኛ እዳሎኑ
ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ይሰማሉ።

👇👇👇👇👇   👇👇👇👇👇
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!


👨‍⚕️👨‍⚕️የወሲብ ችግር በሴቶች ላይ 👨‍⚕️👨‍⚕️

👉የወሲብ ችግር በአብዛኛው በወንዶች ላይ ብቻ የሚከሰት ቢመስልም በሴቶችም ላይ በጣም የተለመደ ችግር ሲሆን በግልፅ የመወያየት ባህል ማጣት እርዳታ እንዳያገኙ እክል ፈጥሯል::

👉 በአጠቃላይ በወንድም ሆነ በሴት ላይ የምያጋትምን የወሲብ ችግር ከማከም አንፃር በሀገራችን በቂ ትኩረት እና የዳበረ ልምድ አለመኖሩ እርዳታ ለሚጠይቁ ሰዎች አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል እርዳታ በሴቶች ላይ የሚከሰtu የወሲብ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው

🚨በሴቶች ላይ የሚያጋጥሙ የወሲብ ችግሮች ምንድናቸው?

1ኛ በወሲብ ሰዓት የሚከሰት ህመም (Pain during sexual activities)

2ኛ የወሲብ ፍላጎት ማጣት (Loss of sexual desire)

3ኛ ፍላጎት ቢኖርም የስሜት አለመቀስቀስ (Impaired arousal)

4ኛ እርካታ ጫፍ ላይ ያለመድረስ ችግር (Inability to achieve orgasm)

🚨ምክንያቶቹ ምንድናቸው?

👉ምክንያት ላይገኝ የሚችል ሲሆን ለችግሩ ከአንድ በላይ ሰበብ ሊኖር ይችላል ::የሚከተሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ :-

👉የስነልቦና የስነ አእምሮ ችግሮች (Primarily psychological factors)
    👸ድባቴ ወይም ከመጠን ያለፈ ፍርሃት (depression, anxiety) ወይም ደሞ እነዚህን ችግሮች ለማከም የሚሰጡ አንዳንድ መድኃኒቶች
    👸ከዚህ በፊት ከወሲብ ጋር በተያያዘ ያጋጠመ ችግር ለምሳሌ ከፍተኛ ህመም:ወይም ስለወሲብ አሉታዊ የሆኑ ነገሮችን ለረጅም ጊዜ መስማት
    👸ከወሲብ ጋር የተያያዘ የስነልቦናዊ ወይም አካላዊ ጥቃት :መደፈር አጋጥሞ ከሆነ
    👸በቅርብ የተከሰተ የቤተሰብ ሞት

👉የተለያዩ ስጋቶች ለምሳሌ :ያልተፈለገ እርግዝና:የአባላዘር በሽታ ፍርሃት : ከዚህ በፊት ከነበራት ወሲባዊ ልምድ የተነሳ እርካታ አገኛለሁ ብሎ አለማመን:በአጋር ላይ ወሲባዊ ችግሮች ካጋጠመ
👉በተለያየ ምክንያት በራስ መተማመን ማጣት (Low sexual self-image)  ለምሳሌ መውለድ ባለመቻል :ያለጊዜ በማረጥ: በቀዶ ጥገና ጡት ወይም ማህፀን ወይም ሌላ አካል በመቆረጥ :
👉ከአጋር ጋር ያለ ግንኙነት መሻከር
👉የመኖሪያ ቤት አከባቢ ለወሲብ ምቹ አለመሆን (privacy )
👉 ስለወሲብ የተዛባ ባህላዊ እምነት ወይም አስተሳሰቦች

👉አካላዊ ችግሮች :ለምሳሌ ብልት አከባቢ የሚከሰቱ በሽታዎች : በወሊድ: ወይም በሌላ ችግር የሚከሰት የሆርሞን መዛባት :እፅ መጠቀም :ግርዛት :በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የብልት ጉዳት :ማጥባት :የሽንት መቆጣጠር ችግር ወዘተ
👉ለተለያዩ ችግሮች በሚታዘዙ መድኃኒቶች ምክንያት

👉ከማረጥ ጋር የሚመጡ የወሲባዊ አካላት ለውጦች :ለምሳሌ :-የብልት መሟሸሽ :የብልት መድረቅ ወይም የእርጥበት መቀነስ :ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

🚨ሕክምናዎቹ ምንድናቸው??

👉ስለወሲብ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ
👉ምክንያቶቹን በመለየት ማከም
👉የስነ ልቦና ሕክምና
👉የተለያዩ መድኃኒቶች ለምሳሌ ሆርሞኖችን መተካት ወዘተ ናቸው።

👇👇👇👇👇   👇👇👇👇👇
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!


10k followers ደርሰናል እናመሰግናለን 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

https://vm.tiktok.com/ZMSeUbqAX/


ይህ አዲሱ የሻዳይ የቲክ ቶክ አካውንት ነው ሁላችሁም follow በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ  አዳዲስ ቪዲዮችን ይመልከቱ  ለሁሉም ሼር ያድርጉ


ጥያቄ ❓❓❓❓

ለዝሙት የሚፈልግ ወንድ ሴትን ማባባያ መንገዶች እነማን ናቸው ❓

🚫 የእግዚአብሔርን ቃል የራስን ፍላጎት ለማሟላት ከአውድ ውጭ በመጠቀም እና በመተርጎም ከጋብቻ በፊት ወሲብ ለመፈጸም ይሞክራሉ ። እንዲሁም እጮኝነትን ከጋብቻ በፊት ህጋዊ ጋብቻ ለማድረግ ይጠቀማሉ ።

1.ስጡ ይሰጣችኋል ተብሎአል 🤣

2. 1ኛ ቆሮ 7:  5 "አትከልክሉ " ተብሎ ተፅፏል ።

3. መጋባታችን ስለማይቀር አሁን ብናደርግ ችግር የለውም ። ባንጋባ ነው ሀጢያት የሚሆነው።

4. ሴቶች ደግሞ እምቢ ብለው ሊተወኝ ይችላል በሚል ሀሳብ "ላጣው አልፈልግም "ብሎ ፈቃደኛ መሆን።

5.  በተዋወቁ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጥኖ ቀለበት ማሰር እና "ቀለበት ስላደረግን መጋባታችን አይቀርም " የሚል የማታለያ ቃል።

6 ሴቷ ሀጢያት ነው አይሆንም ስትል ....ወንዱ  "ካደረግን በኋላ ንስሐ እንገባለን ጌታ መሀሪ ነው " ማለት ።

7...... ከወደድሽኝ እሺ በይኝ  ። ካልሆነ እተውሻለው በማለት ማስፈራራት ።

8...... በጣም እወድሻለሁ። አልተውሽም አገባሻለሁ እስከዚያ ... በቃ ... ጣጣ የለውም

9. Normal ነው አታካብጂ

10. "ሁለት አይደሉም አንድ ስጋ ናቸው" ማቲ 19:6  ይላል ። " እኛ እኮ ከመተጫጨታችን ጀምሮ በጌታ ፊት አንድ ሆነናል "

11. “እንደምንም እኮ ልንጋባ ነው።”

12. “ፍቅርሽን አረጋግጪልኝ።”

13." እንቢ ካልሽኝ እንለያያለን "

14. “ሁሉም እጮኞች ያደርጉታል።”

15. “እግዚአብሔር ልባችንን ያውቃል።”

16. “አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ኃጢአት አይደለም።”😂

17. መኋልየ መኋልዩ ከሚባለው መፅሐፍ ውስጥ የፍቅር ጥቅስ በመጥቀስ  ለsex አላማ መጠቀም ።

18.......

🏮 ወጣት ያላገባችሁ ራሳችሁን ጠብቁ ቀዩን መስመር አትለፉ ።

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ወሲባዊ ግንኙነት ለጋብቻ ብቻ የተፈቀደ ነው (ዕብራውያን 13:4፣ 1 ቆሮንቶስ 6:18–20)።

#ሴቶች በእጮኝነት ጊዜ ወሲብ ከጠየቀ ወደ ጋብቻ ለመግባት ፍላጎት የለውም ማለት ነው።

❌ እነዚህ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም።
እውነተኛ ፍቅር ድንበርን ያከብራል፣ ወደ ኃጢአትም አይገፋፋም (1 ቆሮንቶስ 13:4–7)።

👉 እጮኝነት ቅድስናን መሠረት ያደረገ ነው።

እጮኝነት ጋብቻ አይደለም ። በእጮኝነት ወቅት ወሲብ መፈጸም ሀጢያት ነው።

“የእግዚአብሔር ፈቃድ ቅድስናችሁ ነው፤ ከዝሙት ትርቁ።” — 1 ተሰሎንቄ 4:3

👇👇👇👇👇   👇👇👇👇👇
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
@Godshaday   @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!

Показано 20 последних публикаций.